AM/Prabhupada 0007 - የክርሽና እንክብካቤ ይመጣል፡፡



Lecture on SB 1.5.22 -- Vrndavana, August 3, 1974

ብራህማናንዳ: "ብራህማና (ቄስ) ስራ መቀጠር አይገባውንምን?" ፕራብሁፓዳ: በርሃብ ይሞታታል እንጂ የስራ ቅጥረኝነትን አይቀበልም:: ይህ የብራህመና ባህርይ ነው:: ሻትርያም ሆነ ቫይሻዎች እንዲሁ ናቸው:: ሹድራ ብቻ ነው የሚቀጠረው:: ቫይሻ የራሱን ንግድ ይጀምራል:: የራሱን ንግድ ይፈልጋል:: ለዚህም አንድ ተግባራዊ ምሳሌ አለ:: ከረጅም ግዜ በፊት: በካልካታ ውስጥ: አንድ አቶ ናንዲ የሚባል: ሰው ነበረ:: ወደ ጓደኞቹም ሂዶ እንዲህ አላቸው:: "እናንተ ትንሸ ሀብት ብትሰጡኝ: አንድ ንግድ እጀምር ነበረ::" እንዲህም አለ "እናንተ ቫይሻ ናችሁን? ነጋዴዎች?" "በእርግጥ" "ገንዘብ ከእኔ እየጠየክ ነውን? ገንዘብ መንገድ ላይ ታገኛለህ:: ሂድ እና ታየዋለህ::" እና እሱም እንዲህ አለ:: " አላገኘሁም" "አላገኘሁም? ያስ ምንድን ነው?" "ያ የሞተ አይጥ ነው::" "እንግዲያው ያ ነው ያንተ ሀብት" ይኅውላችሁ: በዚንግዜ: በካልካታ ውስጥ በአይጥ የተነሳ ተላላፊ በሽታ ጀምሮ ነበረ:: የከተማው ማዘጋጃ ቤትም: አዋጅ አውጆ ነበር:: ይህም የተገደለ አይጥ ይዞ ያመጣ ሰው: ሁለት አናስ ይከፈው ነበር:: ስለዚህም ይህ ሰው: የሞተውን አይጥ ይዞ ወደ ማዘጋጃው ጽህፈት ቤት ሄደ:: እዚያም ሁለት አናስ ተከፈለው:: እርሱም ሁለት ቀኑ ያለፈ ቤትል ነትስ በሁለት አናስ ገዛ:: በደንብ ካጠበውም በኋላ: መልሶ በ4 ወይንም በ 5 አናስ ሸጠው:: እንዲህም በማድረግ በተደጋጋሚ በመሸጥ የህ ሰው በጣም ሃብታም ሰው ሆነ:: የዚህም አንዱ ቤተሰብ: አንዱ የእኛ የመንፈሳዊ ወንድማችን ነበር:: ናንዲ ቤተሰብ:: የናንዲ ቤተሰብ አሁንም ኒሆን: ከ 400 እስከ 500 የሚሆኑ ቤተሰቦችን እየመገቡ ያስተዳድራሉ:: ትልቅ የባለአባት ቤተሰቦች ናቸው:: የቤተሰቦቻቸውም መመሪያም እንዲህ ነው:: አንድ ወንድ ልጅ ወይንም ልጅአገረድ ስትወለድ: 5000 ሩፒ በባንክ ውስጥ ይቀመጥላቸዋል:: በትዳራቸውም ግዜ: ይህ 5000 ሩፒ ከወለዱ ጋራ ሁኖ ይሰጣቸዋል:: ከዚህ ሌላ ግን የጋራ የሆነ ሃብት የላቸውም:: ከቤተሰቡ ጋራ የሚኖረው ሁሉ ደግሞ: ምግብ እና መጠለያ ያገኛል:: ይህን ይመስላል ኑሮአቸው:: ዋነኛው የናንዲ ቤተሰብ መስራች ግን: ንግዱን የጀመረው ከሞተች አይጥ በመነሳት ነው:: ይህም እውነት ነው:: የሰው ልጅ በእራሱ ለመተዳደር ከፈለገ: መተዳደር ይችላል:: በካልካታ ይህንን አይቻለሁ:: በጣም ድሃ የሆኑ ቫይሻዎች እንኳን: በጥወት ተነስተው ዳል (የምስር ዘር) በየቤቱ ያዞሩ ነበር:: የከረጢት ዳል ይዘው በየቤቱ እየዞሩ ይሸጡ ነበር:: ዳል በየቤቱ ያስፈልጋል:: እንዲሁም እያደረጉ: ጥዋት ጥዋት ዳል እየሸጡ: ማታ ማታ ደግሞ የኬሮሲን ዘይት ይዘው በየቤቱ ይሸጣሉ:: ማታ ማታ ይህም ስለሚያስፈልግ ነው:: አሁንም ድረስ በህንድ አገር ይህ እየተካሄደ ነው:: ማንም ለመቀጠር ግድ የለውም:: ያለውን ትንሽ ነገር ሽጦ ያድራል:: ኦቾሎኒም ቢሆን ሌላ ነገር ሽጦ ያድራል:: አንድ ነገር ሰርቶ ያድራል:: ጌታ ክርሽና ለሁሉም መተዳደሪያ ይሰጣል:: ይህ ሰው መተዳደሪያዬን ይሰጠኛል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው:: ሻስትራ (ቅዱስ መጽሃፍ) እንዲህ ይላል:: "ኤኮ ባሁናም ቪዳድሃቲ ካማን" ማመን ያለብንም "ጌታ ክርሽና ህይወት ሰጥቶኛል: ወደዚህ አለምም አምጥቶኛል:" ስለዚህም መተዳደርያዬንም ያቀርብልኛል::" "ስለዚህም እንደ አቅሜ የቻልኩትን ላድርግ" "ይሁንእንጂ: ጌታ ክርሽና በዚህ መነሻ: መተዳደርታዬን ያቀርብልኛል::"