AM/Prabhupada 0015 - እኔ ይህ ገላ አይደለሁም፡፡



Lecture on BG 9.34 -- New York, December 26, 1966

ነፍስ በገላችን ውስጥ ስለመኖሯ: ስድስት አይነት ምልክቶች አሉ: እድገት ዋናው ምልክት ነው: ነፍስ ከገላ እንደወጣች: እድገት ወዲያውኑ ይቆማል: ልጅ ሞቶ ከተወለደ: ምንም እድገት ሊኖረው አይችልም: ወላጆቹም የሞተ ህጻን ፋይዳ እንደሌለው ስለሚረዱ: ያስወግዱታል: እንደዚሁም ሁሉ ጌታ ክርሽና: ለአርጁና ምሳሌ ሰጥቶታል: በገላችን የምትገኘው የመንፈሳዊ ቅንጣፊ: በገላችን በመኖርዋ: ገላችን ከልጅነት ወደ ወጣትነት ለማደግ በቅቷል: ከልጅነት ወደ ወጣትነት: ከወጣትነት ደግሞ: ወደ እርጅና: ወደፊት ገላችን ጥቅም የለሽ ሲሆን ደግሞ: ነፍሳችን የደከመ ገላችንን ጥላ ትወጣለች: "ቫሳምሲ ጂርናኒ ያትሃ ቪሃያ" (ባ ጊ 2 22) ልክ እኛም የአረጀውን ልብሳችንን ጥለን: አዲስ ልብስ እንደምንለብስ ሁሉ: እንደዚህም ሁሉ: የወጣችው ነፍስ: አዲስ ገላ ትቀበላለች: አዲስ ገላ የምንቀበለውም በእኛ ምርጫ አይደለም: ይህ የገላ ምርጫ የሚወሰነው በተፈጥሮ ህግ አማካኝነት ነው: ይህ የገላ ምርጫ የሚወሰነው በተፈጥሮ ህግ አማካኝነት ነው: ሞት ሲመጣ የሚቀጥለውን ገላ መምረጥ ባይቻለም: በሃሳባችን ግን መመኘቱ ይቻላል መመኘት እና ምን ገላ እንደምንፈልግ መምረጥ ይቻላል: "ያም ያም ቫፒ ስማራን ሎኬ ትያጃቲ አንቴ ካሌቫራም" (ባ ጊ 8 6) በሞት ላይ ያለ ሰው: ያለው አስተሳሰቡ እና አንደበቱ: ለሚቀጥለው ገላው ወሳኝ ነው: በሞት ግዜ ያለን አስተሳሰብ: ለሚቀጥለው ትውልዳችን ወሳኝ ነው: እንደ አስተሳሰባችንም: ገላችን የተወሰነ ይሆናል: እብድ ያልሆነ አዋቂ ሰውም: ይህ ገላ እራሳችን ወይንም ነፍሳችን እንዳልሆነ መረዳት አለበት: በመጀመሪያ ደረጃ: እኛ ይህ ገላ አለመሆናችንን መረዳት አለብን: ይህንን በደንብ ስንረዳም: በዚህ አለም ላይ ተግባራችን ምን እንደሆነ ለመረዳት እንችላለን: ነፍሳት ስለሆንን ተግባራችን ምንድን ነው? ይህም ተግባራችንን: ጌታ ክርሽና በብሃገቨድ ጊታ ውስጥ ጠቅሶታል: በዘጠነኛው ምእራፍ ወደ መጨረሻ ያለው ጥቅስ ላይም ይህ ተገልጿል: "ማን ማና ብሃቫ" ሁላችንም በየሴኮንዱ: የተለያየ ሃሳብ ላይ እንገኛለን: እኛ ገላ ያለን ፍጥረቶች: ሁሉ ግዜ በማሰብ ላይ እንገኛለን: ለሴኮንድ ያህል ግዜ እንኳን ያለ ማሰብ መኖር አንችለም: ይህ አይቻልም: ሰለዚህም ተግባራችን: እንደዚህ ይሆናል: ጌታ ክርሽናን ሁልግዜ ማሰብ አለብን: ሃሳብ ማሰባችን የማይቀር ነው: ስለዚህም ክርሽናን እናስብ: ስለክርሽና ማሰብ ጉዳቱ ምንድን ነው? ክርሽና በምድር ላይ ብዙ ነገር አድርጓል: ብዙ መፃህፍትም ተጽፈዋል: ብዙ ነገር አለ:: ክርሽና ምድር ላይ መጥቶ ነበር:: ብዙ ቮልዩም መጽሃፎችም ተጽፈዋል:: ስለ ክርሽናም ለማሰብ ከወሰናችሁ: ብዙ መፃህፍት ልናቀርብላችሁ እንችላለን:: ስለ ክርሽና: 24 ሰአት እያነበባችሁ: እድሜልክ ብታነቡ: ልትጨርሱት አትችሉም:: እና በቂ የሆኑ ስለክርሽና የሚያስረዱ ነገሮች አሉ:: ክርሽናን ሁሉ ግዜ አስቡ: "ማን ማና ብሃቫ" አስታውስሃለሁ! ልክ አለቃውን እንደሚያስታውስ ሰው: አለቃውን ሁሉ ግዜ እንዳስታወሰ ነው:: ቢሮ በ 9 ሰዓት መግባት አለብኝ:: አለቃዬ ቅር ሳይሰኘው አይቀርም:: ስለ አንድ አላማም ሁል ግዜ እንደአሰበ ነው:: ሁል ግዜ ይህን አይነት ሃሳብ ማሰብ ግን አይበጅም:: ጌታ ክርሽናም ከዚያ በኋላ እንዲህ አለ: “ብሃቫ ማድ ብሃክታ” “በፍቅር ስለእኔ አስቡ” አለቃውም: ማለቴም: ሰራተኛው ስለአለቃው ሲያስብ: ፍቅር በአንደበቱ የለም: የሚያስበውም ደሞዙን እና ገንዘቡን ነው: “ቢሮ በሰአቱ በ 9 ሰአት ባልደርስ: በማርፈዴ: ሁለት ዶላር ሊቆረጥብኝ ይችላል: ስለዚህም: የሚያስበው ስለ እራሱ እንጂ ስለ አለቃው አይደለም: የሚያስበውም ሰለ ገንዘቡ ነው: እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ በመንፈሳዊ አለም ውስጥ: ሊያድናችሁ አይችልም: ስለዚህም ጌታ ክርሽና: እንዲህ ይላል ”ብሃቫ ማድ ብሃክታ“ ”በመጀመሪያ የእኔ አገልጋይ ሁን“ ”ከዚያም ስለኔ በፍቅር አስብ: ያ በቂነው“ እና ይህስ ”ብሃክቲ“ ምንድን ነው” “ማድ ብሃክታ” ይህም በፍቅር የተሰራ ስራ ነው: “ማድ ያጂ” ለጌታ ፈጣሪያችን በፍቅር ማገልገል አለብን: ልክ በምድር ላይ ሁሉ ግዜ ሰው በስራ ላይ እንደሚገኝ ሁሉ: ወደ እኛም በመጣችሁ ግዜ ሁሉ: ቡል ግዜ በስራ ላይ ታገኙናላችሁ: እኛም እንደዚሁ ስራ ፈጥረናል: ይህም ክርሽናን ለማስታወስ የተፈጠረ ስራ ነው: