AM/Prabhupada 0020 - ክርሽናን በትክክል መረዳት ቀላል ነገር አይደለም፡፡



Arrival Lecture -- Miami, February 25, 1975

የጌታ ክርሽናን ማንነት ለመረዳት ቀላል አደለም: “ማኑስያናም ሳሃሽሬሹ ካሽቺድ ያያቲ ሲድሃዬ ያታታም አፒ ሲድሃናም ካሽቺድ ቬቲ ማም ታትቫታሃ (ብ ጊ 7 3) ከብዙ ሚሊዮን ህዝቦች መሃከል:አንዱ መንፈሳዊ ህይወቱን በደንብ ለማስተካከል ትሁት ልቦና ይኖረዋል: አለበላዛ ግን ሌሎች ምንም ፍላጎቱ የላቸውም: እንዲያውም የህይወታችን መሳካት በምን እንደተመሰረተም አያውቁም: በዚ በአሁኑ አለማዊ ስልጣኔ: ሁሉም እንዲህ ብሎ ያስባል: ”እኔ ጥሩ ሚስት ካገኘሁ:ጥሩመኪና ካገኘሁ እና ጥሩ ቤት ካገኘሁ:ህይወቴ የተሳካ ይሆናል“ ብሎ ያስባል: ይህ የህይወታችን መሳካት አይደለም: ይህ ግዜያዊ ነገር ነው: ትክክለኛው የህይወት መሳካት ግን:ከ ”ማያ“ (ዐለማዊ ኑሮ)ሠንሠለት መፈታት ነው: ይህም ከዚህ ዐለማዊ ኑሮ እስር:ከመወለድ:ከመሞት:ከማርጀት እና ከመታመም: መፈታት ማለት ነው: እኛ (ነፍሳችን) በተለያየ ህይወት እያለፍን እንገኛለን: ይህ የሰው ትውልዳችን ደግሞ: ከዚህ እስር ቤት እንድንወጣ የሚረዳን ጥሩ አጋጣሚ የሚሰጠን ህይወት ነው: ከእነዚህ ሁሉ የተለያየ ፍጥረት ኑሮአችን (ከትውልድ በፊት)የተለየ ነው ማለት ነው: ነፍስ ዘለአለማዊ እና ደስተኛ ናት: ይህም ምክንያቱ የአማላክ ቅንጣፊ አካል በመሆንዋ ነው: ”ሳት ቺት አናንዳ“ ነፍስ ዘለአለማዊ: ደስታኛ እና ሙሉ እውቀት ያላት ናት: ነገር ግን በዚህ አለማዊ ምድር ውስጥ ገብታ:የተለያየ ገላ ይዛ መኖር ጀምራለች: በዚህም ምክንያት መወለድ እና መሞት የሌለበት መንፈሳዊ ዐለም ውስጥ አይደለም ያለነው: ይህ ዐለም ድንቁርና ያለበት ነው: ከዚህ ቀደም አንድ ሳይካያትሪስት ሊያየኝ መጥቶ ነበር: ስለ ነፍስ ትምህርቱን እና ስለ ነፍስ ዋና መዋቅሩን ተንትኖ የተረዳው እንዴት ነው? እንደዚሁም መላ አለም በመንፈሳዊ አለም ድንቁርና ውስጥ ይገኛል: መላ የገለም ህዝብ ትኩረቱ:ለዚች ለ 50 ወይንም 60 ወይንም 100 አመት ርዝመት ላላት ህይወት ነው: ነገር ግን ነፍስ ዘላለማዊ መሆንዋን:ደስታኛ እና ዕውቀት የሞላት መሆንዋን ዘንግተዋል ይህን መወለድ መሞት ማርጀት እና መታመምን የምናየው:ነፍ ጊዝያዊ ገላ ውስጥ ገብታ በመወለዷ ብቻ ነው: ይህም ተደጋግሞ የሚከሰት ነው: በዚህም ምክንያት ጌታ ቼይታንያ በርህራሄው ይህንን ለማስተማር ወደዚህ አለም ላይ መጣ: ክርሽናም ወደ እዚህ አለም ይመጣል:ነገር ግን ወደ አገልጋዮቹ ያዘነብላል: ክርሽና መጀመሪያ ልቦናህን ስጠኝ:ከዚያም እኔ እደግፍሃለሁ ይላል: ነገር ግን:ጌታ ቼይታንያ እና ክርሽና አንድ ይሁኑ እንጂ:ጌታ ቼይታንያ ለሁሉም ርህራሄ ያለው ነው:(ለሃጥያተኛውም) ስለዚህም በጌታ ቼይታንያ በረከት ምክንያት:ጌታ ክርሽናን በደንብ ለመረዳት በቅተናል: ጌታ ቼይታንያ እዚህ በተመቅደስ ውስጥ አለ: ሰገዱለት: ምንም የሚያዳግት አይደለም: “ያግያ ሳንኪርታና ፕራዬር ያጃንቲ ሂ ሱ ሜድሃሳሃ” “ክርሽና ቫርናም ትቪሻ ክርሽናም ሳንጎፓንጋስትራ ፓርሳዳም:ያግና ሳንኪርታናም” (ሽ ብ 11 5 32) በቀላሉ የ “ሀሬ ክርሽናን” ቅዱስ ስም ዘምሩ: የቻላችሁትን ያህልም ለጌታ ቼይታንያ አቅርቡ: በጣም ርህሩህ ነው:ሃጥያታችንን ብቻ አይመለከትም ራድሃ ክርሽና ስግደት ግን ትንሽ ሊከብድ ይችላል: በትልቅ ክብር እና ሞገስ መስገድ ያስፈልገናል: ጌታ ቼይታንያ በዚህ አለም ላይ በፍቃዱ እኛን ለማዳን ነበር የመጣው: ትንሽም አገልግሎት ስንሰጠው በጣም ይደሰታል: ነገር ግን ማገልገሉን እንዳታቋርጡ: ገና ለገና አዛኝ እና ትሁት ስለሆነ: ማንነቱን መዘንጋት አለብን ማለት አይደለም: እርሱ ታላቁ ጌታ ፈጣርያችን ነው: እንደዚሁም ሁሉ ያለንን ሁሉ ትልቅ ክብር ለእርሱ መስጠት ይገባናል: ዋናው ጥቅማችን ጌታ ቼይታንያ ሃጥያታችንን አይቶ አይርቀንም: እርሱን ለማስደሰትም መስገዱ እና ማገልገሉ: ቀላል ነው: “ያግና ሳንኪርታናህ ፕራዬር ያጃንቲ ሂ ሱ ሜድሃሳሃ” በቀላሉ የ “ሀሬ ክርሽናን” ቅዱስ ስም በመዘመር ብቻ:ልታስደስቱት ትችላላችሁ: እርሱም ይህንን መዘመር እና መደነስን አስተምሮናል: ይህም አማላክን ለመረዳት እንድንችል የሚያደርግ ቀላሉ መንገድ ነው: በተቻለ መጠን መዘመር ነው: ከተቻለም 24 ሰዓት: ያ የማይቻል ከሆነ ደግሞ:ቢያንስ 4 ግዜ ወይንም 6 ግዜ: በጌታ ቼይታንያ ፊት ለፊትም ብትዘምሩ: ህይወታችሁ የተሳካ ይሆናል: ይህም የተረጋገጠ ነው: