AM/Prabhupada 0021 - በዚህ አገር ለምን የትዳር መፋታት ይበዛል?



Lecture on SB 6.1.26 -- Honolulu, May 26, 1976

የዚህ አለም ኑሮ ይህን ይመስላል: ሁሉም ሰው በአለማዊ ኑሮ ላይተመስጦ ይገኛል: ዋናው የዚህ አለም ኑሮ መሰረቱ ደግሞ: ”የግርሃስታ“ (የትዳር)ኑሮ ነው: የቤተሰብ ኑሮ:በቬዲክም ባህል ይሁን በሌላ ባህል: ሃላፊነቱ ባለቤትን እና ልጆችን መንካባከብ ነው: ሁሉም በዚህ ላይ ተሰማርቷል: ስራቸውም ይኅው ብቻ ይመስላቸዋል: “ቤተሰቤን መንከባከብ:ይህ ነው ሃላፊነቴ” በደንብ እንዲመቻቸው አድርጌ መንከባከብ ሃላፊነቴ ነው:ብለው ያስባሉ: ነገር ግን ይህ ሃላፊነት በእንስሶች እንኳን እንደሚወጣ አርረዱም: እንስሶችም ልጆች አሏቸው: ይመግባሉ:ታድያ ልዩነቱ ምንድን ነው? ስለዚህም እዚህ ጥቅስ ላይ ያለው ቃል “ሙድሃ” ነው :”ሙድሃ“ ማለት አህያ ማለት ነው: በዚህ ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ”ብሁጃና ፕራፒባን ክሃዳን ፕራፒባን“ ”ፕራፕባን“ ማለት መጠጣት ማለት ነው:”ብሁንጃናሃ“ ማለት ደግሞ መብላት ማለት ነው: በመብላት ላይ: በመጠጣት ላይ:”ክሃዳን“ በማኘክ ላይ ”ቻርቫ ቻስያ ራጃ ፕሬያ“ አራት አይነት የምግብ አይነቶች አሉ: አንዳንድ ግዜ እናኝካለን:አንዳንድ ግዜ እንልሳለን: አንዳንድ ግዜ እንውጣለን:አንዳንድ ግዜ ደግሞ እንጠጣለን: እንደዚሁም ሁሉ አራት አይነት ምግቦች አሉ: ስለዚህም እንዲህ እያልን እንዘምራለን “ቻቱር ቪድሃ ሽሪ ብሃገቨት ፕራሳዶ” “ቻቱር ቪድሃ” ማለት አራት አይነት ማለት ነው: በቤተ መቅደስ ውስጥም ለዲቲዎቹ በእነዚህ በአራቱ የተከፈለ የተለያየ ምግብ እናቀርባለን: አንዳንዱ የሚታኘክ ይሆናል: አንዳንዱም የሚላስ ሲሆን ሌላው ደግሞ የሚዋጥ ይሆናል: እንድዚሁም ሁሉ “ብሁንጃና ፓራፒባን ክሃዳን ባላካም ስኔሃ ያንትሪታሃ” እናት እና አባትም ምን አይነት ምግብ መቅረብ እንዳለበት አስበው ልጆቹን ይንከባከቧቸዋል: እናት ያሾዳ ክርሽናን እንዴት አድርጋ እንደምትመግበው አይተናል: ይህም እንደ ተጠቀሰው አንድ አይነት ሁኖ: ልዩነቱ ግን: እኛ የምንመግበው ተራ የሰው ዘር ሲሆን: ይህም ድመቶች እና ውሾችም የሚያደርጉት ነው: እናት ያሾዳ ግን የምትመግበው:ክርሽናን ነበር: የአመጋገብ መንገዱ አንድ ነው: መንገዱ ልዩነት የለውም:ነገር ግን አንዱ ለክርሽና ሲሆን ሌላው ደግሞ ለተራ ሰው ነው: ያ ነው ለውጡ: እንቅስቃሴያችን ሁሉ ክርሽናን መሃከል ካደረገ መንፈሳዊ ነው ማለት ነው: እንቅስቃሴያችን ሁሉ ተራ የሆነ ነገርን መሃከል ካደረገ: ይህ አለማዊ ነው ማለት ነው: የአለማዊ ኑሮ ሌላ ልዩነት የለውም: ይህ ብቻ ነው ልዩ ነቱ: ልክ እንደ ጠንካራ ስሜታዊ ፍላጎት እና ፍቅር ወይንም ንጹህ ፍቅር: ከጠንካራ ስሜታዊ ፍላጎት እና ከንጹህ ፍቅር መሃከል ያለው ልንኙነት ምንድን ነው? በዚህ አለም ወንድ እና ሴት በጠነከረ ስሜታዊ ፍላጎት ሲገናኙ እናያለን እንዲሁም ክርሽና ከጎፒዎቹ ጋር ሲቀላቀል እንሰማለን ከውጭ ሲታይ ሁለቱም አንድ ይመስላሉ: ነገር ግን ልዩነቱ ምንድን ነው? ይህም ልዩነት በ ቼይታንያ ቻሪታምሪታ ደራሲ ተገልጿል: በአለማዊ ስሜታዊ ፍላጎት እና በንጹህ ፍቅር ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ይህም ተገልጿል: እንዲህም አለ “አትሜንድሪያ ፕሪቲ ቫንቻ ታሬ ባሊ ካማ (ቼ ቻ አዲ 4 165) ”የእራሴን ስሜቶች ለማስደሰት ስፈልግ: ይህ “ካማ” ይባላል (አለማዊ ስሜታዊ መንካራ ፍላጎት) ነገር ግን: “ክርስኔንድሪያ ፕሪቲ ኢቻ ድሃሬ ፕሬናማ” እና የክርሽናን ስሜቶች ለማርካት ስንጥር ደግሞ: ይህም “ፕሬማ” ወይንም ንጹህ ፍቅር ይባላል: ይህ ነው ልዩነቱ: በዚህ አለማዊ ምድር ላይ ንጹህ ፍቅር አይገኝም: ወንድ እና ሴት ያለ ብዙ ሃሳብ ይገናኛሉ "እራሱን ለማስደሰት የመጣ ሰው: ከእኔ ጋር ለመሆን ተመኘ" አይደለም: “የእኔን ስሜት ማስደሰት አለብኝ” ይህ ነው ዋና መሰረቱ: ወንድ ልጅ እንዲህ ያስባል “ከዚች ሴት ጋር ብገናኝ ስሜቴ በደንብ ይረካል” ሴትም እንዲህ ታስባለች “ከዚህ ወንድ ጋር ብገናኝ: የኔ ፍላጎት ሊረካ ይችላል” ይህም ስለሆነ: በምእራብ አገሮች ውስጥ: ልክ በስሜታዊ ደስታቸው ትንሽ ችግር ሲመጣባቸው:ወዲያው መፋታትን ያስባሉ: ይህም ሳይኮሎጂካል ነው:ለምን በዚህ አገር ውስጥ ብዙ መፋታት አለ? ከስር ያለው መነሾውም እንዲህ በማለት ነው “ደስታ የማገኝበት መንገዱ ሲቆም:ከዚያ ወድያ አያስፈልገኝም” ይህም በሽሪማድ ብሃጋቨታም ተገልጿል: “ዳም ፓትያም ታቲም ኤቫሂ” በዚህ ዘመን:ባል እና ሚስት ማለት:በግብረ ስጋ መደሰት እና ለግል ደስታ ነው: ይህም ለእኛ ጥያቄ የለውም “በአንድነት እንኖራለን” ክርሽናን እንዴት እንደምናስደስት ተምረን:ክርሽናን ለማስደሰት እንጥራለን: ይህም የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ነው: