AM/Prabhupada 0034 - እያንዳንዱ ሰው እውቀት የሚያገኘው ከባለሥልጣን ነው፡፡



Lecture on BG 7.1 -- Durban, October 9, 1975

ምእራፍ ሰባት:“ፍጹም የሆነ እውቀት” ሁለት አይነቶች እውቀት ይገኛሉ:ፍጹም የሆነ እውቀት እና አሻሚ የሆኑ እውቀቶች ይገኛሉ: ይህ አለም አሻሚ የሆነ እውቀት የሞላበት ነው:እዚህ አለም ላይም:አንዱን ነገር በደንብ ሳንረዳ ሌላውን ለመረዳት አንችልም: ”ይህ ልጅ ነው“ ብለን ስንል:አባትም እንደ አለ መረዳት አለብን: ”ይህ ባል ነው“ ብለንም ስንል:ሚስት መኖሯን መረዳት አለብን: ”ይህ ሰራተኛ ነው“ ብለንም ስንል: አለቃ መኖሩን መረዳት አለብን: ”እዚህ ብርሃን አለ“ ስንልም: ጨለማ እንደ አለ መረዳት አለብን: ይህም ብዙ የሚያሻሙ ነገሮች እንዳሉ ያሳየናል: አንዳንድ ነገሮችን ልንረዳችው የምንችው ከሚሻሙ ሃሳቦች ጋራ ነው: ቢሆ ንም ግን ሌላ ፍጹም የሆነ አለም አለ: እዚህም ፍጹም በሆነው መንፈሳዊ አለም ላይ:አገልጋዩ እና አለቃው በአንድ ደረጃ ላይ ይገኛሉ: ምንም እንኳን አነዱ የበላይ (ፈጣሪ)ሌላው አገልጋይ ቢሆንም:ደረጃቸው በአንድ መስመር ላይ ሁኖ ይሰማል የብሃጋቫድ ጊታም ሰባተኛ ምእራፍ: ሰለዚህ ሰለ ፍጹም ስለሆነ መፍፈሳዊ አለም:ትንሽ ትንተና ይሰጠናል: ይህ እውቀትም እንዴት እንደሚገኝ:ፍጹም በሆነው በጌታ ክርሽና ተነግሯል: ጌታ ክርሽና ፍጹም የሆነ የበላይ ሰው ነው: “ኢስቫራ ፓራማ ክርሽና ሳት ቺት አናንዳ ቭግረሃ:አናዲር አዲር ጎቪንዳ ሳርቫ ካራና ካራናም” (ብሰ 5 1) ይህም ስለ ክርሽና ገለጻ የተሰጠው: በጌታ ብራህማ በተጻፈው መጽሃፍ “ብራህማ ሰሚታ” በሚባለው ነው: ይህ መጽሃፍ የተገኘው: ከደቡብ ህንድ: በጌታ ቼይታንያ ነው: ከደቡብ ህንድም ጉዞው ሲመለስ: ለአገልጋዮቹ አቀረበላቸው: ስለዚህም ይህንን መጽሃፍ እንደ ዋና ስልጣን እንዳለው ተረድተን እንመራበታለን: ይህ ነው የእኛ የእውቀት መሰብሰቢያ ስልት: ስልጣን ያላቸውን ቅዱስ መፃህፍቶች እንከተላለን: ሁሉም ሰው እውቀት የሚያገኘው:ስልጣን ካለው ነው: ይህም ጠቅላይ ከሆነ ባለስልጣን ነው: የኛ ባለስልጣን አቀባበል ግን ትንሽ ለየት ይላል: በእኛ መመሪያ መሰረት: እኛ አንድ ባለስልጣን ከተቀበልን: የተቀበልነውም ባለስልጣን ደግሞ:ሌላ የራሱ ባለስልጣን ይኖረዋል: በእራስ የተሾመ ባለስልጣን አይኖረንም:: ይህም መሆን አይችልም:: ከሆነም እንከን የጎደለው ባለስልጣን ይሆናል:: ይህን ምሳሌ ብዙ ግዜ ሰጥቻለሁ:: ልጅ ከአባቱ ይማራል:: ልጅ አባቱን ይጠይቃል:: "አባቴ ይህ ማሽን ምንድን ነው?" አባቱም እንዲህ ይላል "ውድ ልጄ: ይህ ማይክራፎን ይባላል" እንደዚህም ሁሉ ልጅ ከአባቱ እውቀት ይወስዳል:: "ይህ ማይክራፎን ነው" እንደዚሁም ልጁ ለሌላ ሰው "ይህ ማይክራፎን ነው" ብሎ ከነታገረ: መልእክቱ ትክክል ነው:: ምንም እንኳን ትንሽ ልጅ ቢሆንም: የተቀበለው እውቀት ስልጣን ካለው ሰው ስለሆነ: የሚሰጠው ገለፃ ትክክል ነው:: እንደዚህም ሁሉ: የምንቀበለው እውቀት: ከትክክለኛ ባለ ስልጣን ከሆነ: ምንም እንደ ልጅ ብንሆንም: የምንሰጠው ገለፃ ትክክል ይሆናል:: ይህ ነው የእኛ እውቀት መሰብሰቢያ መንገድ: እኛ እውቀትን እራሳችን አንፈጥርም: ይህ ነው በ4 ኛ ምእራፍ ብሃጋቫድ ጊታ ውስጥ የተሰጠው መመሪያ: “ኤቫም ፓራምፓራም ፕራፕታም ኢማም ራጃርሻዮ ቪድሁ” (ብጊ 4 2) ይህ የፓራምፓራ ሲስተም ይባላል: “ኢማም ቪቫሽቫቴ ዮጋም ፕሮክታቫን አሃም አቭያያም ቪቫስቫን ማናቬ ፕራሃ ማኑር ኢክስቫካቬ ብራቪት” (ብጊ 4 1 ) “ኢቫም ፓራምፓራ” ስለዚህ ፍጹም የሆነ እውቀት ሊገኝ የሚችለው ግን: ፍጹም ከሆነ ሰው ስንሰማ ብቻ ነው: ከዚህ አለም ላይ ማንም ሰው ስለ ፍጹም ሰለሆነው እውቀት ከእራሱ አንደበት ፈጥሮ ሊነግረን አይችልም: ይህ የማይቻል ነው: እና እዚህ ስለ ፍጹም ስለሆነው አለም እንማራለን: ፍጹም የሆነ እውቀት:የፈለቀውም ፍጹም ከሆነው ከፍተኛው አምላክ: ፍጹም ከሆነው ሰው:ነው ፍጹም ሰው ማለትL ”አናዲር አዲር ጎቪንዳሃ“(ብሰ 5 1 ) እርሱም ዋራ የመጀመሪያ ሰው ነው:ሌላ መነሻ የለውም:ስለዚህም ፍጹም ይባላል: ፈጣሪ ማለትም በሌላ ሰው ወይንም ፍጥረት ያልተፈጠረ ማለት ነው: ይህም ፈጣሪ አምላክ ነው: ስለዚህም በዚህ ምእራፍ: እንዲህ ብሎ ተገልጿል:”ሽሪ ብሃገቫን ኡቫቻ“ ፍጹም የሆነ ሰው: ”ብሃጋቫን“ ማለት: በሌላ ሰው የማይተማመን ፍጹም ሰው ማለት ነው: