AM/Prabhupada 0035 - በዚህ ገላችን ውስጥ ሁለት ዓይነት ዓብይ ነዋሪ ነፍሳቶች አሉ፡፡



Lecture on BG 2.1-11 -- Johannesburg, October 17, 1975

አሁን ክርሽና የጉሩን (መንፈሳዊ መምህር) ደረጃ ይዞ: ማስተማር እና መምራት ጀመረ:: "ታም ኡቫቻ ርሺኬሻ" ርሺኬሻ: ሌላው የክርሽና ስም "ርሺኬሻ" ይባላል:: ርሺኬሻ ማለት: "ርሺካ ኢሻ" ርሺካ ማለት ስሜቶች ማለት ነው:: "ኢሻ" ማለት ነግሞ: ጌታ ወይንም የበላይ ማለት ነው:: ስለዚህ ክርሽና የስሜቶቻችን ሁሉ ጌታ ነው:: የሁላችንም ሰሜቶች ሁሉ የበላይ ተቆጣጣሪ:: ይህም በ13ኛ ምዕራፍ ተገልጿል:: "ሼትራ ግናም ቻፒ ማም ቪድሂ ሳርቫ ሼትሩ ብሃራታ (ብጊ 13 3 ) በዚህ በገላችን ውስጥ: ሁለት አይነት ነፍሶች አሉ:: አንዱ እኔ ራሴ ነኝ: የእኔ የራሴ ነፍስ ማለት ነው:: "አትማ" ይባላል:: ሌላው ደግሞ ክርሽና ወይንም "ፓራም አትማ" ይባላል:: "ኢሽቫራ ሳርቫ ብሁታናም ህርዴሼ አርጁና ቲስትሃቲ" (ብጊ 18 61) የዚህ ገላ ዋናው ባለቤት ግን "ፓራም አትማ" (ፈጣሪ) ነው:: ይህንን ገላ በአምላክ እንድገለገልበት ነው የተሰጠኝ: አለኝ ብዬ የማስባቸው ስሜቶች ሁሉ ደግሞ የእኔ ስሜቶች አይደሉም:: እጄን የፈጠርኩት እኔ አይደለሁም:: እጄ የተፈጠረው በአማላክ ወይንም በክርሽና ነው:: የተፈጠረውም በተፈጥሮ የአምላክ አገልጋዮች ነው:: እጄም የተሰጠኝ ለራሴ ለሚሆን ነገር እንድጠቀምበት ነው:: ይህም እንድበላበት: እንለቅምበት ነው:: ቢሆንም ግን የእኔ እጅ አይደለም:: ይህ እጃችን ፓራላይዝድ ከሆነ በኋላ ሁሉ: "እጄ" እንላለን:: ነገር ግን ልንጠቀምበት አንችልም:: ምክንያቱም ለመጠቀም የምንችልበትን ሃይል ባለቤቱ ወስዶታል (ፓራሊሲስ) ልክ ኪራይ ከፍላችሁ እንደምትኖሩበት ቤት ማለት ነው:: የቤቱ ባለቤት ከአባረባችሁ: ለመኖር አትችሉም: ቤቱን ልትጠቀሙበት አትችሉም:: እንደዚሁም ሁሉ: ይህንን ገላ ልንጠቀምበት የምንችለው: ዋናው ባለቤቱ ፈጣሪ ጌታ "ህርሺኬሻ" እስከፈቀደልን ግዜ ብቻ ነው:: ስለዚህ የክርሽና ስም "ርሺኬሻ" ተብሎ ይታወቃል:: ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር ማለት: ስሜታችንን ከክርሽና ተቀብለናል ማለት ነው: እነዚህም ስሜቶች ክርሽናን ለማገልገል እንጠቀምባቸዋለን: በአለማዊ ኑሮ ግን: ስሜታችንን ለክርሽና አገልግሎት ከመጠቀም ለራሳችን ጥቅም እናውለዋለን ማለት ነው: ይህ ነው የእኛ የስቃይ ኑሮ: ልክ የቤት ኪራይ እንደምትከፍሉበት ቤት ማለት ነው: ኪራይ የማትከፍሉ እና ይህ የእኔ ቤት ነው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ: ችግር ይመጣባችኋል: እንደዚሁም ሁሉ “ርሺኬሻ” ማለት ትክክለኛው ባለቤት ክርሽና ነው ማለት ነው: ይህን ንብረት ተሰጥቶኛል ብለን ማሰብ አለብን:ይህም በብሃጋቨድ ጊታ ተገልጿል: “ኢሽቫራ ሳርቫ ብሁታኒ ህርዴሼ አርጁና ቲስትሃቲ ብህራማያን ሳርቫ ብሁታኒ ያንትራሩድሃኒ ማያያ (ብጊ 18 61) ያንትራ ማለት ማሽን ማለት ነው:ይህ ማሽን ለእኔ በክርሽና ተሰጥቶኛል ይህንንም ያገኘሁት እንዲህ አይነት ማሽን ቢኖረኝ: እንዲህ አድርጌ መደሰት እችላለሁ ብዬ አስብ ስለነበረ ነው: ስለዚህም ክርሽና እንደ ፍላጎታችን ያሰብነውን ያሟላልናል: እንዲህም ካሰብን ደግሞ: ”ከሌላ እንስሳ ደም የምመጥበትን ገላ እፈልጋለሁ“ ካለን ደግሞ: ክርሽና እንዲህ ይለናል :”አሁን የነብር ገላ ውሰድ እና ተጠቀምበት“ ይለናል: እና ይህ ሁሉ እየተካሄደ ነው:ስለዚህም የክርሽና ስም ”ርሺኬሻ“ ይባላል: እንደዚህም ብለን መረዳት አለብን :”እኔ የዚህ ገላ ባለቤት አይደለሁም“ ክርሽና የገላችን ባለቤት ነው:እኔ ግን ስሜቴን የማስደስትበትን ገላ ለማግኘት እሻለሁ: ገላውን ሰጥቶናል ነገር ግን ደስታኛ ላንሆን እንችላለን: ስለዚህ ይህን ገላ ለባለቤቱ እንድንጠቀምበት ያስፈልጋል:ይህም ”ብሃክቲ“ ወይንም በፍቅር የሚሰራ የአማላክ አገልግሎት ይባላል: ”ህሪሺኬሻ ርሺኬሻ ሴቫናም ብሃክቲር ኡቻቴ“ (ቼቻ ማድህያ 19 170) ስሜቶቻችን ለማገልገል መጠቀም ነው:ምክንያቱም ክርሽና የስሜቶቻችን ሁሉ ባለቤት ነው: የገላችንም ባለቤት ነው: ይህም ገላ ለባለቤቱ ለአማላካችን ስንገለገልበት ይህ የህይወታችን መሳካት ነው ማለት ነው: