AM/Prabhupada 0089 - የክርሽና ነፀብራቅ የሁሉም ነገር መነሻ ነው፡፡



Lecture on BG 4.24 -- August 4, 1976, New Mayapur (French farm)

ፈረንሳዊ ድቮቲ:ክርሽና እኔ እነርሱ ውስጥ አይደለሁም ሲል ምን ማለቱ ነው? ፕራብሁፓድ:“ምን አልክ?” "እኔ በእነርሱ የለሁም" ምክንያቱም አንተ ለማየት ስለማትችል ነው: ክርሽና እዛ አለ:ነገር ግን:አንተ ልታየው አትችልም:ይህም በመንፈስ የበለፀግህ ስላልሆንክ ነው: ሌላው ምሳሌ ደግሞ:የፀሃይ ሙቀቱ እዚህ አለ: ሁሉም ሰው ሙቀቱ ይሰማዋል:ነገር ግን ፀሃይ እዚህ አለች ማለት አይደለም: ግልጽ ነው?ፀሃይ እዚህ አለች ማለት: ፀሃይ እዚህ አለች ማለት ነው: ፀሃይ ላይ ተቀምጠህ ከሆነ:ፀሃይን ይዣታለሁ ማለት አትችልም: ፀሃይ የፀሃይ ብርሃን አለው:ነገር ግን የፀሃይ ብርሃን ሙሉ ፀሃይ የለውም: ያለ ፀሃይ የፀሃይ ብርሃን ሊኖር አይችልም:ይህም ማለት ብርሃን ፀሃይ ነው ማለት አይደለም: ነገር ግን ብርሃንን ፀሃይ ማለት ይቻላል: ይህ “አቺንትያ ብሄዳ ብሄዳ ” ይባላል:በአንድ ግዜ አንድም ልዩም: ፀሀይ ስታንፀባርቅ:የፀሀይን መውጣት ታረጋግጣላችሁ: እንደዚሁም ሁሉ:ወደ ፀሀይ ፕላኔት መግባት የምትችሉም ከሆነ:የፀሀይን አምላክ ማግኘትም ትችላላችሁ: የፀሀይ ጨረርም: የሚመጣው ከዚሁ በፀሀይ ውስጥ ከሚኖረው ነዋሪ አምላክ የገላ ጨረር ነው: ይህም በብራህማ ሰሚታ ተገልጿል:“ያስያ ፕራብሃ ፕራብሃቫቶ ጃጋድ አንዳ ኮቲ” (ብሰ 5 40) ይህም በክርሽና ተወካይነት ነው: የክርሽናንም ነፀብራቅ አይታችኋል:እርሱም የሁሉም መነሾ ነው: ከዚህም ትስፋፍቶ የሚገው ነፀብራቅ:ብራህማጆይቲ ይባላል:በዚህም ብራህማጆይቲ: የተለያዩ መንፈሳዊ ፕላኔቶች እና አለማዊ ፕላኔቶች ተፈጥረዋል: እያንዳንዱም ፕላኔቶች የተለያዩ ፍጥረታት አሏቸው: እነዚህ ፍጥረቶች ከዚህ ነፀብራቅ ተፈጥረዋል:የነፀብራቁ መነሻ ደግሞ ክርሽና ነው: