AM/Prabhupada 0097 - እኔ ልክ እንደ ተራ የፖስታ መልእክተኛ ነኝ፡፡



His Divine Grace Srila Bhaktisiddhanta Sarasvati Gosvami Prabhupada's Appearance Day, Lecture -- Los Angeles, February 7, 1969

ይህንን የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ በዓለም ላይ ለማስተማር በመገስገስ ላይ እያለን ምንም ተማሪዎች ወይንም ተከታዮች እንኳን ባይኖሩንም ክርሽና በጥረታችን እንደሚረካ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ዋናው ስራችንም ክርሽናን ለማርካት ጥረት ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ይህም "ብሀክቲ" ይባላል፡፡ ህርሺኬና ህርሺኬሻ ሴቫናም ብሀክቲር ኡችያቴ (ብጊ 4 7) "ብሀክቲ" ማለት ያለንን የስሜት የገላ አካላት ሁሉ ለክርሽና ደስታ በማገልገል ማሰማራት ማለት ነው፡፡ የዓለማዊ ህይወት ማለት ደግሞ ስሜቶቻችንን ሁሉ ለግል ጥቅም እና ደስታ ብቻ ማዋል ማለት ነው፡፡ "ይህን እወዳለሁ" "ይህን እፈልጋለሁ" "ይህን ማድረግ እፈልጋለሁ" "ይህን መዝፈን እፈልጋለሁ" "ይህን መብላት እፈልጋለሁ" "ይህን መንካት እፈልጋለሁ" "ይህን መቅመስ እፈልጋለሁ" "ይህን ነገር" ማለት የምንፈልገው ነገር ሁሉ ስሜታችንን ለማርካት ነው፡፡ ይህ የዓለማዊ ኑሮ አስተሳሰብ ነው፡፡ "የለሰለሰ ቆዳ መንካት እፈልጋለሁ፡፡" "ጣፋጭ የሆነ ምግብ ለመቅመስ እፈልጋለሁ፡፡" "እንዲህ የመሰለ ነገር ማሽተት እፈልጋለሁ፡፡" "እንዲህ ለመራመድ እፈልጋለሁ፡፡" ነገር ግን እነዚህ መራመድ መቅመስ መንካት ወይንም ማናቸውም ነገሮች ለክርሽና ደስታ መጠቀም ይኖርብናል፡፡ ይኅው ነው፡፡ ተራ የሆነ ነገርም ከመንካት ለምሳሌ የተባረከውን እና የሎተስ እፅዋት የመሰለውን የክርሽናን አገልጋይ እግር ብንነካ ይህ መንካት በረከት ይኖረዋል፡፡ ማናቸውውንም ሀጥያት የሞላባቸውን ምግቦች ከመብላት የክርሽናን "ፕራሳድ" ብንበላ አግባብ ያለው ይሆናል፡፡ ማናቸውንም ነገር ለማሽተት ከመሻት ለክርሽና የቀረበውን አበባ ብናሸት አግባብ ያለው ይሆናል፡፡ እንደዚሁም በማድረግ ምንም ነገር አይጎልብንም፡፡ በወሲብብም ለመሰማራት የፈለገ በክርሽና ንቃት የዳበሩ ልጆችን ለማሳደግ በዚህ ተግባር መሰማራት ይችላል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ማናቸውም ነገሮች አይቆሙም፡፡ ነገር ግን ስራችን ሁሉ የፀዳ ይሆኖል፡፡ ጠቅላላ ፕሮግራማችንም ይኅው ነው፡፡ ይህንን አቁሙ የሚባል ነገር አይኖርም፡፡ እንዴትስ ይህን አቁሙ ማለት ይቻላል? ለምሳሌ እኔ የሰው ፍጡር ነኝ፡፡ አንድ ሰው “መብላትን አቁም” ቢለኝ ይህ የሚቻል ነወይ? መብላት ግዴታዬ ነው፡፡ መብላትን ማቆም የሚቻል አይደለም፡፡ ዋናው ጥያቄ ግን እንዴት አድርገን የመብላት ባህርያችንን እንዲፀዳ ማድረግ እንችላለን ነው፡፡ ሌላው የምናየው ፊሎሶፊ ደግሞ በግድ የመብላት ፍላጎትን መቀነስ ነው፡፡ እነዚህ ፈላስፋዎች የሚያስተምሩትም “ፍላጎትህን ሁሉ ለማጥፋት ሞክር” በማለት ነው፡፡ እንዴትስ ፍላጎታችንን ለማጥፋት ይቻላል? ፍላጎት መኖር ያለበት ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ክርሽናን በፍላጎታችን ውስጥ ማስቀመጥ ጥሩ ስርዓት ያለው ፍላጎት ነው፡፡ ምንም እንኳን ሌሎች ይህንን ስርዓት ባይከተሉም ወይንም ይህንን ፊሎሶፊያችንን ባይከተሉም እናንተ በደንብ እንደ ስራችሁ አድርጋችሁ ከተከተላችሁት ክርሽና በደንብ እንደሚረካ መገንዘብ አለባችሁ፡፡ የበፊት መምህራኖቻችን እና ጉሩ ማሀራጅ በደስታ እንደሚረኩ የተረጋገጠ ነው፡፡ “ያስያ ፕራሳዳ ብሀገቫት” እነርሱም ሁሉ ከተደሰቱ ስራችሁም ሁሉ የተሳካ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳን ሌሎች ተደሰቱም አልተደሰቱም፡፡ በመዘመራችንም ህዝብ በደስታ ሊረካ ይችላል። ነገርግን እኛ ለዚህ ትኩረት የለንም፡፡ እነርሱም ሊደሰቱ ወይንም ላይደሰቱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እኔ በአግባቡ የምዘምር ከሆነ የቀድሞ መምህራኖቼ “አቻርያዎች” ሁሉ ደስተኞች ይሆናሉ፡፡ ይህም ስራዬ ሁሉ ተሳካ ማለት ነው፡፡ ይህም መምህርን መከተል እንጂ የእራሴን ስርዓት የማልፈጥር ከሆነ ነው፡፡ የጀመርኩትንም ሚሽን ለማሳካት ክርሽና ብዙ ጥሩ የሆኑ ልጆች እና ልጃገረዶች ስለላከልኝ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ በዚህም በተባረከ ቀን የተባረካችሁ ሁኑ፡፡ የእኔ የሆነ ምንም ነገር የለም፡፡ እኔ የመልእክቱ የፖስታ አገልጋይ ብቻ ነኝ፡፡ የማቀርብላችሁ ሁሉ ከጉሩ መሀራጅ መምህሬ የሰማሁትን ብቻ ነው፡፡ እናንተም እንደዚሁ በማድረግ ተከተሉ፡፡ በዚህም ደስተኛ ትሆናላችሁ፡፡ ይህች ዓለምም ደስተኛ ትሆናለች፡፡ ክርሽናም ደስተኛ ይሆናል፡፡