AM/Prabhupada 0104 - የመወለድ እና የመሞትን ተደጋጋሚነት አቁሙ፡፡



Lecture on BG 9.1 -- Melbourne, April 19, 1976

ፑስታ ክርሽና:እንዴት ነው:የአውሬ ነፍስ ወደ ሰው ልጅ ገላ ገብቶ ሊወለድ የሚችለው? ፕራብሁፓድ:በእስር ቤት የታሰረ ሌባ:እንዴት ነው ነፃ ሊሆን የሚችለው? ሌባው:ለስቃይ የተፈረደበት ግዜውም እንድ አከተመ: ነፃ መውጣት ይችላል: እንደገናም ደግሞ ወሮበላ ከሆነ:ተመልሶ ወደ እስር ቤት ይገባል: ይህም በአምላክ የተሰጠን የሰው ልጅ ህይወት:ለማወቅ እና ለመበልፀግ ነው: እንዳስረዳሁትም:የህይወታችንም አላማ:ችግሩን ተረድቶ መፍትሄ ለመፈለግ ነው: መሞት አልፈልግም ነገር ግን ለመሞት ተገድጃለሁ:ለምን? ማረጅ አልፈልግም:ነገር ግን የግዴን እርጅና ውስጥ እገባለሁ:ለምን? “ጃንማ ምርትዩ ጃራ ቭያድሂ ዱክሃ ዶሳኑ ዳርሻናም” (ብጊ13 9) ልክ እንደ ሌባውም ምሳሌ: ነፃ ከወጣ በኋላ:በጭንቅላቱ እንዲህ ቢያስብ: “እንዴት ነው ለ6 ወር እዚህ ስቃይ ውስጥ ለመግባት የበቃሁት?በጣም ያለስፈለገ ፍዳ ነበር:” ቡሎ ቢያሰላስል: ልክ እንደ ቁም ነገረኛ የሰው ልጅ ሆነ ማለት ነው: እንደዚሁም ሁሉ የሰው ልጅ ፍጥረት:ከእንስሳው ሁሉ ሲወዳደር:በጣም ወደ ፊት የተራመደ የማመዛዘን ችሎታ ያለው ነው: እንዲህ ብሎም ቢያስብ “እንዴት ነው እዚህ ስቃይ ውስጥ ለመግባት የቻልኩት?” ብሎ ቢያሰላስል:ከችግር ነፃ ይሆናል: ሁላችንም በዚህ ስቃይ በተሞላበት ሁኔታ እንደአለን መቀበል አለብን:(ሞት:በሽታ:እርጅና ወዘተ) በዚህ ምድር ላይ:ደስተኛ ለመሆንም ሁል ግዜ እየጣርን ነው:ነገር ግን ደስታ አይገኝም: ታድይ ይህ ደስታ እንዴት ነው የሚገኘው? ይህ የሚገኝበት እድሉ በዚሁ በሰው ልጅነታችን ፍጥረት ነው: በተፈጥሮ ሩህሩህነት:ይህን የሰው ፍጥረት ወይንም ትውልድ አግኝተናል: ነገር ግን ለተሰጠንበት ጥሩ አላማ የማንጠቀምበት ከሆነ:ልክ እንደ ውሻ እና ድመትም ያገኘነውን ምርቃት አባክነናል ማለት ነው: ከዚያም እንደገና የእንስሳ ገላ መያዝ ሊኖርብን ነው ማለት ነው:ይህም ግዜው እስቂያልቅ መጠበቅ ሊኖርብን ነው ማለት ነው: ይህም በጣም በጣም ረጅም ግዜ ይፈጃል:ምክንያቱም የሪቮሉሽነሪ ሂደት ስለሚኖረው ነው: ከዚያም እንደገና ወደ እዚሁ ወደ ሰው ትውልድ እንመጣለን:ያም የእንስሳነት ኑሮ እድሜ እንደ አለቀ ነው: ይህም እንደ ሌባው ምሳሌ ነው:ሌባው የተፈረደበትን ግዜ እንደ አጠናቀቀ:ከእስር ቤት የመውጣት መብቱ የተከበረ ነው: ነገር ግን እንደገና ወደ ወሮበላነቱ ከተመለሰ:እንደገና ወደ እስር ቤቱ ይመለሳል: እንደዚህም የሞት እና የትውልድ:መደጋገም አለ: ይህንንም የሰው ህይወታችንን እንደ ስርአቱ ብንጠቀምበት:ከዚህ ከተደጋገመ ሞት እና ትውልድ መዳን እንችላለን: ይህን የሰው ትውልድን በስርአቱ የማንጠቀምበት ከሆነ ግን:እንደገና ወደ ሞት እና መወለድ አለም እንመለሳለን: