AM/Prabhupada 0115 - የእኔ ስራ የክርሽናን መልእክት ማስተላለፍ ብቻ ነው፡፡



Lecture -- Los Angeles, July 11, 1971

እነዚህ ልጆች እኔን በማገዝ ላይ በመሆናቸው በጣም ተደስቼአለሁ: ይህም የክርሽናን ንቃት በማስፋፋታቸው ነው:ክርሽናም ምርቃቱን ያወርድላቸዋል: እኔ ያልገነንኩኝ እና ሃይል የሌለኝ ሰው ነኝ: የኔ ሃላፊነት: የክርሽናን መልእክት ማስተላለፍ ብቻ ነው: ልክ እንደ ደብዳቤ አቅራቢ እርግብ:ሃላፊነቱ ደብዳቤውን ማቅረብ ብቻ ነው: ስለ ደብዳቤው ሃላፊነት የለውም: ደብዳቤ ተቀባዩም ደብዳቤውን አንብቦ:የሚሰማው ነገር ሊኖር ይችላል: ነገር ግን የህ ሃላፊነት የእርግቡ አይደለም: እንደዚሁም ሁሉ:የእኔ ሃላፊነት:ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የመንፈሳዊ አባቶች ትምህርት: ምንም ሳልቀይረው:እንዳለ ማቅረብ ብቻ ነው: ይህ ነው የእኔ ሰራ:ይህ ነው የእኔ ሃላፊነት: ማቅረብ ያለብኝ:ልክ ክርሽና እንደ አቀረበልን ነው: ልክ አርጁና እንደአቀረበው:ልክ የእኛ አርአያዊ መምህራን እንደ አቀረቡት እና ልክ ጌታ ቼይታንያ እንደአቀረበው መሆን አለበት: በመጨረሻም:ልክ የእኔ መንፈሳዊ መምህር “ብሃክቲሲድሃንታ ሳራስቨቲ ጎስዋሚ ማሃራጅ” እንደአቀረበው መሆን አለበት: እንደዚሁም ሁሉ የክርሽና ንቃትን እንቅስቃሴ በዚሁ መንፈስ ከተቀበላችሁት: ለአገራችሁም ህዝብ የምታከፋፍሉት ከሆነ: ምንም ስለአልተበረዘ:ውጤታማ ይሆናል: ጉራ የለውም:የማታለል መልእክትም የለውም: ንጹህ የመንፈሳዊ ንቃት ይሆናል: የእናንተም ሃላፊነት መከተሉን እና ማከፋፈሉን ነው:ህይወታችሁም የተሳካ ይሆናል: