AM/Prabhupada 0127 - ታላቅ ድርጅት የተወሰነ ስርዓት ከሌለው ሊፈርስ ይችላል፡፡



Lecture on SB 1.2.11 -- Vrndavana, October 22, 1972

የእኔም ጉሩ ማሃራጅ እንዲህ ይለን ነበረ:”ክርሽናን ለማየት አትሞክሩ“ ”ክርሽና እንዲያያችሁ ግን:አገልግሎት ለመስጠት ሞክሩ“ ይህ ነው የሚያስፈልገው: የክርሽናን ሃሳብም በትንሹ ለመሳብ ከቻላችሁ: ”ያት ካሩንያ ካታክሳ ቫይብሃቫቫታም ካታክሻ ቫይብሃቫታም“ ፕራብሆድሃናንዳ ሳራስቫቲ እንዲህ ብሏል:”የክርሽናን ሃሳብ ወይንም ትኩረት በትንሹ እንኳን ለመሳብ ከቻላችሁ:ህይወታችሁ የተሳካ ይሆናል“ ወዲያውኑ:ታድያ እንዴት ነው መሳብ የምትችሉት? “ብሃክትያ ማም አብሂጃናቲ” (ብጊ 18 55) ይህም ክርሽናን በማገልገል ብቻ ነው: የመንፈሳዊ አባታችሁን ትእዛዝ ተከትላችሁ:ክርሽናን ለማገልገል ሞክሩ: ምክንያቱም የመንፈሳዊ አባት: የክርሽና ተወካይ ነው:ክርሽናን በቀጥታ መቅረብ አንችልም: “ያስያ ፕራሳዶ ብሃጋቫት ፕራሳዳህ” ክርሽናን የሚወክል:ትክክለኛ መንፈሳዊ አባትም ካላችሁ:ክርሽናን መቅረብ ቀላል ይሆንላችኋል: ማነም ሰው የክርሽና ተወካይ:መሆን ይችላል: እንዴት:ይህስ ሊሆን ይችላል? የክርሽናን መልእክት:ሳትቀይሩ ማቅረብ ከቻላችሁ ነው: ቼታንያ ማሃፕራብሁም እንዲህ ብሏል:“አማራ አግናያ ጉሩ ሃና” (ቼቻ ማድህያ 7 128) “በእኔ ትእዛዝ ጉሩ ሁኑ” የቼይታንያ ማሃፕራብሁንም ትእዛዝ የምትከተሉ ከኖነ:ጉሩ መሆን ትችላላችሁ: “አማራ አግያና ጉሩ ሃና” ነገር ግን ችግሩ የመምህሮቻችንን ትእዛዝ የመከተል ምኞት የለንም: የራሳችንንም መንገድ እንፈጥራለን: ተግባራዊ በሆነም መንገድ እንዴት ትልቅ ድርጅቶች ሁሉ እንደጠፉ አይተናል: የመንፈሳዊ አባታቸውን ሳይከተሉ:የራሳቸውን አመራር መፍጠር ሲጀምሩ:ሁሉም ነገር መፍረስ ይጀምራል: ስለዚህም ቪሽቫናት ቻክራቫርትሂ:የመንፈሳዊ አባቶቻችን ቃላቶች እንዲከበሩ ትኩረት አድርጓል: ቭያቫሳያትሚካ ቡድሂር ኤኬ ሃ ኩሩ ናንዳና:(ብጊ 2 41) ወደ መንፈሳዊ አባታችሁ ትእዛዝ ላይ ትኩረት ካደረጋችሁ: ሰለ ራሳችሁ ምቾት እና አለመመቸት ሳታስቡ ብታገለግሉ:ህይወታችሁ የተሳካ ሊሆን ይችላል: “ያስያ ደቬ ፓራ ብሃክቲር ያትሃ ዴቬ ታትሃ ጉሮ ታስያይቴ ካትሂታ ሂ አርትሃ ፕራካሻንቴ ማሃትማናሃ” (ሽብ6 23) ይህ በሁሉም ባለስልጣኖች የፀደቀ ነው: የፀደቀንም የክርሽናን ተወካይ ትእዛዝ:በሙሉ ልቦናችን አምነን መከተል አለብን:በዚህም መንገድ ህይወታችህ የተሳካ ይሆናል: ክርሽናንም በእውነተኛ መንገድ ልርነዳው እንችላለን:“ቫዳንቲ ታት ታትቫ ቪዳስ ታትቫም” (ሽብ 1 2 11) መስማት ያለብንም ከታትቫ ቪት (እውነትን የሚያውቅ)መሆን አለበት:ከምሁራን እና ከፖለቲከኞች ግን መሆን የለበትም: መስማት ያለባችሁም:እውነትን ከሚያውቅ መንፈሳዊ አባት:መሆን አለበት: ይህንንም መመሪያ በጥብቅ ከተከተላችሁ:ሁሉንም ነገር በትክክል ለመረዳት ትችላላችሁ: አመሰግናለሁ: