AM/Prabhupada 0135 - የቬዳን እድሜ ለመገመት አይቻልም፡፡



Morning Walk -- October 5, 1975, Mauritius

ህንዳዊ ሰው:ስዋሚጂ:በባይብል ላይ የተጠቀሰው አደም:ብራህማ ነው ብለህ ታስባለህን? ይህም ከህንድ ፍልስፍና ተቀድቶ:ባይብል ውስጥ በሌላ ስም የተጻፈ ይመስላል:

ፕራብሁፓድ: ከታሪክ አንጻር የተቀዳ እንደሆነ እንረዳለን: ምክንያቱም:ቬዳዎች የተፈጠሩት በብራህማ: ከበጣም ረጅም እና ከብዙ ሚልዮን አመታት በፊት ነው: ባይብልም የተፈጠረው:ከ2000 አመት በፊት ነው: ስለዚህ እኛ የምንወስደው ዋናውን ወይንም ኦሪጂናሉን ነው: ሁሉም የአለም ሃይማኖቶች:የተወሰዱት ከቬዳዎች ነው:ይህም ከተለያየ ወገኖች ነው: ስለዚህ የተሟሉ አየደሉም: የባይብል እድሜ ከ2000 አመታት አይበልጥም: የቬዳዎች እድሜ ግን ሊተመን አይችልም:ምክንያቱም ከሚልዮን እና ሚሊዮን አመታት በላይ ስለሆነ ነው: