AM/Prabhupada 0150 - መዘመርን ማቆም አይገባንም፡



Lecture on SB 6.1.15 -- Denver, June 28, 1975

“አትሃፒ ቴ ዴቫ ፓዳምፑጃ ድቫያም ፕራሳዳ ሌሻኑግርሂታ ኤቫ ሂ ጃናቲ ታትቫም ና ቻንያ ኤኮ ፒ ቪቺቫን” (ሽብ 10 14 29) እነዚያ በክርሽና በረከት የተመረቁ:ክርሽናን ለማወቅ ይችላሉ: ሌሎች ግን:“ና ቻንያ ኤኮ ፒ ቺራም ቪቺንቫን” ቺራም ማለት ለረጅም ግዜ ማለት ነው:ክርሽና ማን እንደሆነ ግምት ውስጥ ቢገቡ ብዙ አመትም አይበቃቸውም: ይህም ክርሽናን ለመረዳት ነው:የግምት ሂደት አይጠቅመንም: እንደዚህም ብዙ የቬዲክ ጥቅሶች አሉ: “አታህ ሽሪ ክርሽና ናማዲ ና ብሃቬድ ግራሃያም ኢንድሪያኒ ሴቮን ሙክሄ ሂ ጂቫዶ ስቫያም ኤቫ ስፑራትሂ አዳሃ” :(ቼቻ ማድህያ 17 136) ክርሽና:ስሙ:ዝናው:አንደበቱ:ስራው: “ሽሪ ክርሽና ናማዲ ና ብሃቬድ” ናማዲ ማለት:“ከቅዱስ ስሙ ጀምሮ ማለት ነው” ምንድን ነው የማይቻለው?“እራሳችንን በአለማዊ መድረክ ካስቀመጥን” ለአንድ ሺህ አመት ያህልም ብንዘምር:ለመራመድ አስቸጋሪ ይሆናል:ይህም “ናማ አፐራድ” ይባላል: ቢሆንም ግን:ቅዱስ ስም ሃይል ስለ አለው:በመዘመር ብቻ:ቀስ በቀስ አንድ ሰው ንጹህ ሊሆን ይችላል: ስለዚህም መዘመርን ማቆም የለብንም:በተገኘንበት ሁኔታ:ሀሬ ክርሽና መዘመር አለብን: ነገር ግን እራሳችንን በአለማዊ መድረክ ላይ ካስቀመጥን:ክርሽናን ሙሉ በሙሉ ለማወቅ እና መረዳት ያዳግተናል: ቅዱስ ስሙን:አንደበቱን:ፎርሙን:ስራውን:መረዳት አዳጋች ይሆናል: ለዚህም ስርአቱ ብሃክቲ ነው: ክርሽናን ደግሞ ለመራዳት ስትበቁ: ወዲያውኑ ወደ መንፈሳዊ አለም ለመሄድ:ብቁ ትሆናላችሁ: ክርሽናም ይህንን በብሃገቨድ ጊታ ጠቅሶታል: “ትያክትቫ ዴሀም ፑናር ጃንማ ናይቲ ማም ኢቲ”(ብጊ 4 9).