AM/Prabhupada 0179 - መስራት ያለብን ለክርሽና ደስታ መሆነ አለበት፡፡



Lecture on SB 1.16.6 -- Los Angeles, January 3, 1974

እነዚህ ማያቫዲ ፈላስፋዎች:በእውቅት እና በግምታዊ ፍልስፍና የበለፀጉ ይመስላሉ:ነገር ግን ዞረው ዞረው መውደቃቸው አይቀርም: ለምን?“አናድርታ ዩስማድ አንግህራያህ” “ያንተን ሎተሳዊ የእግር ከለላ:ሰለአልተጠለሉ:መውደቃቸው አይቀርም” የእነርሱ መንገድ አረጋጋጭ አይደለም:ምክንያቱም እንደ እነርሱ ፍልስፍና: የሰው ልጅ ያለ ስራ እና ያለ ፍላጎት ለመኖር አይችልም: ይህ የማይቻል ነው:የሰው ልጅ:እንስሳ:እና ተባይ እንኳን አንድ የሆነ ስራ ይሰራል: እኔም ተግባራዊ ልምድ አለኝ: አንዱ ልጄ በወጣትነቴ ግዜ: አስቸጋሪ ነበር: አንዳንድ ግዜም የእቃ መደርደርያ ላይ እናስቀምጠው ነበረ:መውረድም አይችልም ነበር: እርሱም አይመቸውም ነበር:ይህም የሚሰራው ስራ መደርደሪያው ላይ ሁኖ ስለቆመበት ነው: ስለዚህ ስራን ማቆም አይቻልም:ይህ የማይቻል ነገር ነው: የተሻለ ስራ የሰው ልጅ ከተሰጠው ያለአግባብ የሚሰራውን ስራ ማቆም ይችላል:“ፓራም ድርስትቫ ኒቫርታቴ” (ብጊ 2 59) ስለዚህም ይህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ:የተሻለ ስራን ለሰው ልጅ እያቀረበ ነው: እንደዚሁም ሁሉ የረከሰ ስራ መቆም ይችላል: አለበለዛ ግን በመቃወም ብቻ:ዝቅ ያለ ስራን ማቆም አይቻልም: መስራት አለብን:ይህም ስራ ክርሽናን ለማስደሰት መሆን አለበት: ወደ ክርሽና ቤተ መቅደስ መሄድ ይቻላል:የክርሽናን መፃህፍቶች ለማደል መሄድ ይቻላል:ወይንም ወደ ክርሽና ደቮቲዎች ጋ ሂዶ መሰባሰብ ይቻላል: ይህ ቆንጆ ነው:ነገር ግን ስራን ማቆም አይቻልም:ይህ የማይቻል ነው: አለበለዛ ግን: ይህ የስራፈት አእምሮዋችሁ የሰይጣን ጎጆ መስሪያ ይሆናል በዚህም ልትወድቁ ትችላላችሁ:“እንዴት ወደ እዛች ሴት ልሂድ?” “እንዴት ወደ እዛ ወንድ ልሂድ?” መስራት ካቆማችሁ:አእምሮአችሁ ወደ ስሜታዊ ደስታ ፍለጋ መጓዝ ይጀምራል:ይኅው ነው: እንደዚሁም ሁሉ:ማናቸውንም ስሜቶቻችን:ለማቆም አንችልም:ነገር ግን በመንፈሳዊ አገልግሎት ማሰራት እንችላለን:ይህ የክርሽና ንቃት ነው: