AM/Prabhupada 0212 - በሳይንሳዊ መንገድም ብናየው ከሞት በኃላ ሕይወት አለ፡፡



Garden Conversation -- June 10, 1976, Los Angeles

ፕራብሁፓድ፡ በዚህ ዘመን የሚገኙት የትምህርት ማእከሎች ይህ ተደጋግሞ መወለድ መሞት ማርጀት እና መታመም የመሳሰሉት ዋናው ችግራችን ሰለመሆኑ እውቅናው የላቸውም፡፡ ሊረደቱም ስለማይችሉ እንዴት አድርገው ሊቀበሉት ይችላሉ? መፍትሄ የለውም ብለው ሲለሚገምቱ ተቀብለውት ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህን የማቆሙ መንገድ ከተገኘ ለምንድነው የማይቀበሉት? ታድያ የዚህ ትምህርት ዋጋው ምንድነው? ትክክለኛውን ከስህተተኛው ለመለየት አቅሙ የላቸውም፡፡ ሞትን የሚወድ የለም፡፡ ነገር ግን ሞት ሁልግዜ ያለ ነው፡፡ እርጅናን የሚወድ ሰው የለም፡፡ ነገር ግን እርጅና ሁልግዜ ያለ ነው፡፡ ታድያ እነዚህን ትላልቅ ችግሮች አቁመን ለምንድነው በ ሳይንሳዊ እርምጃዎች እና እውቀት ትእቢት ውስጥ የምንገባው? ይህስ ምን ዓይነት ትምህርት ነው? ትክክለኛውን ከስህተተኛው ለይተን የማናውቀው ከሆነ ይህ ትምህርት ፋይዳው ምንድን ነው? ትምህርት ወይንም እውቀት ማለት አንድ ሰውን ትክክለኛ እና ስህተት የሆነው ለይቶ የሚያሳውቅ ከሆነ ነው፡፡ ይህን ለይተው አያውቁም፡፡ ሞትም ጥሩ መሆኑን በትክክል አልተረዱም፡፡ ለምንድን ነው ሞትን ለማቆም ጥረት የማያደርጉት? እርምጃቸው የት ነው? በሳይንስ እርምጃ ብቻ በኩራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ታድያ እርምጃው የት የት አለ? ሞትን ማቆም አይችሉም፡፡ እርጅናንም ለማቆም አይችሉም፡፡ የረቀቀ መድሀኒትም መፍጠር ይችላሉ፡፡ ታድያ ህመምን ሁሉ ለምን ከምድር ለማጥፋት አይችሉም? ይህን መድሀኒት ውሰድ፡፡ ከዚህ በኃላ ህመም የሚባል ነገር አይነካህም፡፡ ታድያ ይህ አይነቱ ሳይንስ የት አለ? ናሊካንታ: ”በሙከራ ላይ እንገኛለን ይላሉ“ ፕራብሁፓድ: ”ያ ሌላው ዓይነቱ ሞኝነት ነው፡፡ ጉራ ብቻ፡፡” ጎፓቭርንዳፓላ፡ “ልክ እኛ የክርሽና ንቃታችን ቀስ በቀስ የበለጽጋል እንደምንለው እነርሱም የሳይንሳዊ እርምጃቸው ቀስ በቀስ እየበለፀገ በመሄድ ላይ ነው ይላሉ፡፡” ፕራብሁፓድ፡ “ቀስ በቀስ? ታድያ ቀስ በቀስ ሞትን ለማቆም እንችላለን ብለው ያምናሉን?” እኛ ቀስ በቀስ ወደ ዋናው ቤታችን ወደ ክርሽና እንደምንመለስ እርግጠኛ ነን፡፡ ታድያ የእነርሱ እርግጠኝነት ሞትን እርጅናን መታመምን ለማቆም የታለ? ዶክተር ዎልፍ፡ አዲሱ ሀሳባቸው ከሞት በኃላ ህይወትን ለመፍጠር እንደሚቻል ነው፡፡ ፕራብሁፓድ፡ ህይወት አለ፡፡ ዶክተር ዎልፍ፡ ይህንንም ህይወት በሳይንስ ለመፍጠር እየሞከሩ ነው፡፡ ፕራብሁፓድ፡ ይሞክሩት፡፡ በሳይንሳዊ መንገድ እንደምንረዳው ግን ከሞት በኋላ ሕይወት አለ፡፡ ይህንንም ደጋግመን ተናግረናል፡፡ የልጅነት ገላዬ ሞቷል ሄዷል ጠፍቷል፡፡ አሁን ያለኝ ገላ የተለየ ገላ ነው፡፡ ሰለዚህ ከሞትም በኋላ ሕይወት አለ፡፡ ይህ ተግባራዊ አመለካከት ነው፡፡ ክርሽናም እንደዚህ ይላል፡፡ “ታትሀ ደሀንታራ ፕራፕቲህ” (BG ብጊ 2 13) እንደዚህም ሁሉ “ና ሀንያቴ ሃንያማኔ ሻሪሬ” (ብጊ 2 20) ይህ የአብዩ የመላእክት ጌታ ስልጣናዊ ቃል ነው፡፡ በተግባር እንደምናየው ከገላ ገላ እየቀያየርን እናያለን፡፡ ቢሆንም ግን ማንነታችን ሁል ግዜ እንደቀጠለ ነው፡፡ ታድያ ለመቃወም ምን መድረክ አለ? ሰለዚህ ከሞት በኋላ ሕይወት አለ፡፡ ሞት ማለት የገላ መፍረስ ማለት ነው፡፡ ሞት የሌለበትንም ሕይወት የምናገኝ ከሆነ ይህንን አይነት ሕይወት መፈለግ ይኖርብናል፡፡ ይህም አዋቂነት ይባላል፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ ይህን ክርሽናን ብቻ ለመረዳት ብንበቃ ወደ እርሱ ለመሄድም ብቁ ከሆንን ሞት የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም፡፡