AM/Prabhupada 0290 - የጋለ ፍላጎታችንን ማሟላት ሲያቅተን ቁጠኛ መሆን እንጀምራለን፡፡



Lecture -- Seattle, September 30, 1968

ኡፔንድራ:ፕራብሁፓድ የቁጣ ተፈጥሮው ምንድን ነው?እንዴት ነው ቁጣ

ፕራብሁፓድ:ቁጣ ማለት የጋለ ፍላጎት ማለት ነው: የጋለ ፍላጎት ሲኖርህ:ፍላጎትህ ካልተሟላ:ቁጠኛ ትሆናለህ:ይኅው ነው: የጋለ ፍላጎት:ሌላው ባህሪይ ነው:”ካማ ኤሻ ክሮድሃ ኤሻ ራጆ ጉና ሳሙድብሃቫሃ“ በቅብዝብዝነት ባህርይ አንድ ሰው ሲጠቃ:የጋለ ፍላጎት ይኖረዋል: ይህ የጋለ ፍላጎት ሳይሳካ ሲቀር:ወደ የሚቀጥለው ደረጃ ወደ ቁጣ ትሄዳለህ: ከዚያም ቀጥሎ ያለው ደግሞ:መደናገር ነው: ከዚያም ቀጥሎ ያለው ደግሞ:ፕራናሻያቲ ይባላል:ከዚያም ሁሉ ይጠፋብሃል: ስለዚህ አንድ ሰው:ይህንን የጋለ ፍላጎት እና:ቁጣን መቆጣጠር አለበት: ይህም መቆጣጠር ማለት:እራሰህን በቅብዝብዝነት ባህርይ ሳይሆን:በጥሩ ረጋ ባለ ባህርይ መምራት አለብህ ማለት ነው: ሶስት አይነት ባህሪዮች ይገኛሉ:የድንቁርና ባህሪይ:የቅብዝብዝነት ባህርይ እና የጥሩ ባህርይ: የአማላክን መንፈሳዊ ሳይንስ ለመረዳት የፈለገ ሁሉ:በጥሩ ባህርይ ላይ መገኘት አለበት: አለበለዛ ግን ሊረዳ አይችልም: ስለዚህም እኛ ለተማሪዎቻችን:”እንዲህ አታርጉ:እንዲህ አታርጉ“ እያልን እንገኛለን: ምክንያቱም:እራሱን በጥሩ ባህርይ ላይ ማድረግ አለበት:አለበለዛ ትምህርቱም ሊገባው አይችልም: ክርሽና ንቃት በቅብዝብዝነት ባህርይ ላይ ሁኖ:ለመረዳት አይቻልም: መላ አለም በዚህ በቅብዝብዝነት እና:በድንቁርና ባህርይ ተሸፍኖ ይገኛል: የእኛም መመሪያ ቀላል ሁኖ ቀርቧል:አራቱን መመሪያዎቻችንን ከተከተላችሁ እና:ሀሬ ክርሽናን ከዘመራችሁ: ሁሉንም ዝቅተኛ ባህሪዮች ሁሉ አለፋችሁ ለመሄድ ትችላላችሁ: ስለሺህ ይህ ቁጣ:የቅብዝብዝነት ባህርይ መድረክ ነው: