AM/Prabhupada 0349 - እኔ በመንፈሳዊ መምህሬ የተሰጠኝን ትምህርት በእምነት ተቀብየው እገኛለሁ፡፡



Arrival Address -- New York, July 9, 1976

አንድ አዋቂ ሰው ነኝ የሚል ሰው በዓለም ያሉ የተለያዩ ሁኔታዎችን እና የተለያዩ ሕይወቶችን መረዳት ይጠበቅበታል፡፡ ነገር ግን ይህንን አያውቁም፡፡ ባለፈው ቀን የእኛ ዶክተር ስቫሩፕ ዳሞዳር ንግግር ሲያደርግ ነበር፡፡ ይህ የሳይንቲፊክ እርምጃ እና የትምህርት መሻሻል በማድረግ ሁለት ዓይነት የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ገምግመዋል፡፡ እነዚህ በትእይንተ ዓለም ውስጥ የሚገኙት የተለያዪ ፕላኔቶች ምን እንደሆኑ እውቀቱ የላቸውም፡፡ የሚያውቁት ነገር የለም። በግምት ላይ ብቻ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ወደ ጨረቃ እና ወደ ማርስ ፕላኔቶችም ለመሄድ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ይህም የሚቻል አይደለም፡፡ ወደ አንድ ወይንም ሁለት ፕላኔቶች እንኳን ለመሄድ ቢችሉ ከእነዚህ ውጪ በብዙ ሊሚዮን የሚቆጠሩ ፕላኔቶች አሉ፡፡ ስለ እነዚህስ ምን ዓይነት እውቀት አላቸው? ሌላው የሚፈልጉት እውቀት ደግሞ የሕይወት መሰረታዊ ችግሮች ምን እንደሆኑ አያውቁትም፡፡ ሁለት ነገሮች ጐሎባቸው ይታያል፡፡ እኛ ደግሞ እነዚህን ሁለት ነገሮች እየተቋቋምናቸው ነን፡፡ ከሕይወት መሰረታዊ ችግሮች ርቀን እንገኛለን፡፡ ከክርሽና ንቃት ደግሞ ርቀን ስንገኝ ደግሞ ወደ ስቃይ ውስጥ ወድቀን እንገኛለን፡፡ የክርሽና ንቃት የምትወስዱ ከሆነ ችግሮቻችሁ ሁሉ ይፈታሉ፡፡ የፕላኔቶችንም ስርዓት ማወቅ ከፈለግንም ክርሽና እንሉን እየሰጠን ነው፡፡ ወደ ፈለግነው ፕላኔት ለመሄድ እንችላለን፡፡ ነገር ግን አዋቂ የሆነው ሰው የሚሄድበትን መምረጥ ይችላል፡፡ ”ማድ ያጂ ኖ ፒያንቲ ማም“ (ብጊ፡ 9.25) ”እነዚያ በክርሽና ንቃት የዳበሩት ሁሉ ወደ እኔ መምጣት ይችላሉ፡፡“ "ታድያ በእነዚህ ሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?" ምንም እንኳን ወደ ጨረቃ ወደ ማርስ ፕላኔት ወይንም ወደ ብራህማ ሎካ የገነት ፕላኔት ብሄድም እንኳን ክርሽና እንዳለው ”አ ብራህማ ብሁቫና ሎካሀ ፑናር አቫርቲኖ ርጁና“ (ብጊ፡ 8.16) ወደ ከፍተኛው ፕላኔት ወደ ”ብራህማ ሎካ“ ለመሄድ ትችላላችሁ፡፡ ነገርግን እንደተጠቀሰው ”ክሽኔ ፑንዬ ፑንዮ ማርትያ ሎካም ቪሻንቲ“ ወደ እዚህ ዓለም መመለሳችሁ አይቀርም፡፡ ክርሽናም እንዲህ ብሏል ”ያድ ጋትቫ ኒቫርታንቴ ታድ ድሀማ ፓራማም ማማ“ (ብጊ፡ 15.6) ማድ ያጂኖ ፒ ያንቲ ማም ሰለዚህ አሁን ይህ እድሉን አግኝታችኋል ይህም የክርሽና ንቃት ነው፡፡ ሁሉም ነገርም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ምን ምን እንደሆነ ተገልጾላችኋል፡፡ ይህም እድል እንዳያመልጣችሁ፡፡ በሳይይንቲስቶች በፈላስፋዎች እና በፖለቲከኞች በመሳሳት ሞኞች አትሁኑ፡፡ ይህንን የክርሽና ንቃት በጥሞና ተከታተሉ፡፡ ይህም የሚቻለው በ ”ጉሩ ክርሽና ክርፓያ“ ብቻ ነው፡፡ (ቼቻ፡ማድህያ 19.151) በጉሩ እና በክርሽና በረከት ሁሉም ነገር የሚሳካ ነገር ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ ሚስጢሩም ይኅው ነው፡፡ ያስያ ዴቬ ፓራ ብሀክቲር ያትሀ ዴቬ ታትሀ ጉሮ ታስያይቴ ካትሂታ ሂ አርትሀህ ፕራካሻንቴ ማሀትማናሀ (ሽኡ፡6 23) ይህም የምናደረገው የጉሩ ፑጃ ስርዓት እራስን ለማጋነን የተደረገ ነገር አይደለም፡፡ ይህ ትክክለኛ ትምህርት ነው፡፡ በየቀኑ ትዘምራላችሁ፡፡ ይህስ ምንድነው? ጉሩ ሙክሀ ፓድማ ቫክያ ..... አራና ካሪዮ አይክያ ይህ ትርጉሙ ነው፡፡ በእውነቱ ለመናገርም በክርሽና ንቃታችሁ ምንም እንኳን ትንሽ እርምጃ ብተወስዱም እኔ ሁልግዜ የማምነው በእኔ ጉሩ መሀራጅ የተነገረውን ነው፡፡ እናንተም እንዲሁ ቀጥሉበት፡፡ በዚህም ሁሉ የተሳካ ይሆንልናል፡፡ አመሰግናለሁ፡፡