AM/Prabhupada 0356 - የምንናገረው ሁሉ በሀሳባዊ ግምታችን የተፈጠረ ሳይሆን ስልጣን ካላቸው ሻስትራዎች ወይንም ስነፅሁፎች ነው፡



Lecture at World Health Organization -- Geneva, June 6, 1974

ፕራብሁፓድ፡ አንዱ የመንግስት ሀላፊነት ማንም ሰው ስራፈት እንዳይሆን ነው፡፡ ይህም ጥሩ መንግስት ነው፡፡ ማንም ሰው ስራ ፈት መሆን የለበትም፡፡ የቬዲክ ስርዓት እንዲህ ነበረ፡፡ በዚያን ግዜ ህብረተሰቡ በአራት ተከፍሎ ነበረ፡፡ ብራህማና ክሻትርያ ቫይሽያ እና ሱድራ፡፡ የመንግስትም ሀላፊነት እያንዳንዳቸው ከተመደበላቸው ሀላፊነት አንፃር ስራቸውን መስራት እንዲችሉ ነበረ፡፡ ይህም ብራህማናው የብራህማናን ስራ በትክክል እንዲያከናውን፡፡ እንዲሁም ክሻትርያው የክሻትርያን ሀላፊነት በትክክል እንዲወጣ፡፡ በተመሳሳይም ቫይሻዎች እንዲሁ፡፡ በዚህም ስርዓት የመንግስት ሀላፊነት ለምን ሰዎች ስራ ፈት እንደነበሩ መከታተል ነበረ፡፡ በዚህም መንገድ ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ሊኖራቸው ይችላሉ፡፡

እንግዳ፡ ነገር ግን በመንግስትም ውስጥ ሰዎች አሉ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ምን አልክ?

እንግዳ፡ እነዚህ የመንግስት አባላት ጠንካራ ሀይል ያላቸው ሀብት ያላቸው የመሬት ግዛት ያላቸው በመንግስትም ተሰሚ ድምፅ ያላቸው ናቸው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አይደለም፡፡ ያ ማለት እማ መጥፎ መንግስት ማለት ነው፡፡

እንድዳ፡ አዎን ይህ እውነት ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ያማ መጥፎ መንግስት ማለት ነው፡፡ አለበለዛ ግን የመንግስት ሀላፊነት እያንዳንዱ ሰው ስራ ፈት እንዳይሆን ማድረግን ነው፡፡

እንግዳ፡ ይህንን ነው እኔ ወደፊት በተስፋ የምጠብቀው ነገር ቢኖር፡፡ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ተስፋፍቶ ይህም ትክክለኛ እና አብዮታዊ እንቅስቃሴ በመሆን የሕብረተሰቡን ገፅ ለበጎ መቀየር፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን እኔም እንደሚሰማኝ ይህ ትልቅ እንደሚያመጣ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ አሜሪካኖች እና አውሮፓውያን ወጣቶች ይህንን ያሰተማርኳቸውን እንቅስቃሴ ተቀብለውት በማስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ተስፋም ያለኝ እነዚህ አሜሪካዊ እና አውሮፓውያን አእምሮአቸው የላቀ ሆኖ ይህንን እንቅስቃሴ ኮስተር ብለው እንዲዋስዱት ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ ይህንን እንቅስቃሴ ለአምስት ወይንም ስድስት ዓመት ስንገፋ እንገኛለን፡፡ በዚህም አጭር ግዜ ውስጥ ይህንን እንቅስቃሴ በዓለም ላይ በማስፋፋት ላይ እንገኛለን፡፡ እኔም የምጠይቃችሁ ነገር ቢኖር እኔ እንሜዬ ገፍቷል በቅርቡም ሕይወቴ ማለፉ አይቀርም እና ሁላችሁም ይህንን እንቅስቃሴ ኮስተር ብላችሁ ከወሰዳችሁት እንደሚቀጥል ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡ ምክንያቱም የምናደረገው ነገር ሁሉ በቀለለ ልቦና እና በድንገታዊ አስተሳሰብ የተመሰረተ አይደለም፡፡ እውቀቱን የምንወስደውም ስልጣን ካለው የተቀደሱ ስነፅሁፎች ነው፡፡ (ሻስትራ) ፕሮግራማችንም እንደዚህ የመሰሉትን በመቶ የሚቆጠሩ መፃህፍቶች ለማተም ነው፡፡ በእነዚህም መፃህፍቶች ብዙ መረጃዎች ይገኟሉ፡፡ እነዚህን መጻህፍቶችን መማንበብ ብዙ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡ እኛም በዚሁ አቀራረባችን ተቀባይነትን በማግኘት ላይ እንገኛለን፡፡ በተለይ በአሜሪካ ውስጥ ከፍተኛ ማእረግ ያላቸው ሁሉ በኮሌጆች እና በዩኒቨርስቲዎች እነዚህን መፃህፍቶች በማንበብ ላይ ይገኛሉ አንብበውም ምስጋናቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህም መንገድ የተቻለንን ያህል በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህም እነዚህን ስነፅሁፎች በማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህም ሌት ተቀን በመስራት እና መመሪያዎችን ወደ ተቻለን ርቀት በመሄድ እና በማስተማር ነው፡፡ እንደምናስበውም እነዚህ ወጣቶች ይህንን ኮስተር ብለው የሚወስዱት ከሆነ በዓለም ትልቅ እንቅስቃሴ እንደሚያመጣ ባለ ሙሉ ተስፋ ነን፡፡