AM/Prabhupada 0421 - የመሀ ማንትራን ስትዘምሩ ማስወገድ የሚኖርባችሁ ሀጥያቶች ከ1 እስከ 5



Lecture & Initiation -- Seattle, October 20, 1968

ማድሁቪሳ፡ ሽሪላ ፕራብሁፓድ? አስሩን በመዘመር ግዜ የተከለከሉትን ህግጋት ላንባቸው ወይ?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን

ማድሁቪሳ፡ እዚህ አጠገባችን ናቸው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ተመልከቱ አንተም አንብብ ቀጥል

ማድሁቪሳ፡ የመሀ ማንትራን ቅዱስ ስም ስንዘመር አስሩ የተከለከሉ ነገሮች፡፡ አንደኛ “የአብዩ አምላክን ትሁት አገልጋዮች መሰደብ ወይንም ማንቋሸሽ”

ፕራብሁፓድ፡ አሁን ይህንን ለመረዳት ሞክሩ፡፡ ማንም የአብዩ አምላክ አገልጋይ መሰደብ የለበትም፡፡ ይህም የትም አገር ቢሆን ነው፡፡ ለምሳሌ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ትልቅ ትሁት አገልጋይ ነው፡፡ ሙሀመድም ቢሆን ትሁት አገልጋይ ነው፡፡ ገና ለገና እኛ አገልጋዮች ነን እና እነርሱ አገልጋዮች አይደሉም ማለት አይደለም፡፡ የአብዩ ጌታን መልእክት የሚሰብክ ሁሉ አገልጋይ ነው፡፡ እርሱም በሰደብ ወይንም መንቋሸሽ የለበትም፡፡ መጠንቀቅም ያስፈልጋችኋል፡፡ ቀጥል

ማድሁቪሳ፡ “ሁለተኛ፡ አብዩ የመላእክት ጌታን እና መላእክቶችን በአንድ ደረጃ ላይ አድርጎ ማየት ወይም ብዙ አብይ አምላኮች አሉ ብሎ ማሰብ፡፡”

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ለምሳሌ ብዙ ሰሜት የማይሰጥ ንግግሮች እንሰማለን፡፡ ለምሳሌ ሰለመላእክት.... በእርግጥ ከመላእክቶች ጋር ብዙ ጉዳዮች የሉንም በቬዲክ ስነፅሁፎች እንደተጠቀሰው በመቶ እና በሺህ የሚቆጠሩ መላእክቶች አሉ፡፡ በተለይ በአሁኑ ግዜ ክርሽናንም ሆነ ጌታ ሺቫን ወይንም ካሊን ብታመልኩ ሁሉም አንድ ነው የሚባል ነገር አለ፡፡ ይህ ስሜት የማይሰጥ ፍልስፍና ነው፡፡ ይህም መሆን የለበትም፡፡ ማለትም መላእክቶችን ከአብዩ የመላእክት ጌታ ጋር እኩል ማድረግ የማይገባ ነው፡፡ ከአብዩ የመላእክት ጌታ በላይ ማንም የለም፡፡ ከአብዩ የመላእክት ጌታ ጋርም እኩል የሚሆን የለም፡፡ ሰለዚህ ይህ መላእክቶች ከአብዩ ጌታ ጋር እኩል ናቸው የሚለው ፍልስፍና መወገድ አለበት፡፡ ቀጥል

ማድሁቪሳ፡ “ሶስተኛ፡ የመንፈሳዊ አባታችንን ትእዛዝ አለመቀበል፡፡”

ፕራብሁፓድ፡ አዎን የመንፈሳዊ አባት ትእዛዝ ልክ እንደ ነፍስ እና ሕይወት ተደርጎ መታየት ይገባዋል፡፡ ከዚያም ሁሉ ነገር ግልጽ ሊሆን ይችላል፡፡ ቀጥል

ማድሁቪሳ፡ “አራተኛ፡ የቬዲክ ስነፅሁፎችን ባለስልጣንነት ማቅለል፡፡”

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ማንም ሰው የቬዲክ ስነጽሁፎችን ባለስልጣንነት ማቅለል አይገባውም፡፡ ይህም መገለል የሚገባው ነው፡፡ ቀጥል

ማድሁቪሳ፡ “አምስተኛ፡ የአብዩ አምላክን ቅዱስ ስም ያለአግባብ መተርጐም፡፡“

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ለምሳሌ አሁን የሀሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም ስንዘምር እንገኝ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ቀን አንድ ልጅ እንዲህ ብሎ ነበር ”ሲምቦሊክ“ ይህም ሲምቦሊክ አይደለም፡፡ “ክርሽና” ብለን ስንዘምር ክርሽናን በቀጥታ እየተገናኘን ነው፡፡ ሀሬ ማለት የክርሽና ሀይል ማለት ነው፡፡ የምንፀልየውም እንዲህ በማለት ነው ”በአገልግሎትህ እንድሰማራ አድረገኝ“ ይህ ሀሬ ክርሽና ማለት ነው፡፡ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ “ሀሬ ክርሽና ሀሬ ክርሽና ክርሽና ክርሽና ሀሬ ሀሬ ሀሬ ራማ ሀሬ ራማ ራማ ራማ ሀሬ ሀሬ” ይህም ፀሎት ትርጉሙ ”ኦ የጌታ ሀይል ሆይ ኦ ጌታ ክርሽና ኦ ጌታ ራም“ “እባክህ በአገልግሎትህ ላይ እንድሰማራ አድረገኝ” ይኅው ነው፡፡ ሌላ ሁለተኛ ትርጉም የለውም፡፡