AM/Prabhupada 0425 - አንዳንድ መቀያየር አድርገው ሊሆን ይችላል፡፡



Room Conversation with Carol Cameron -- May 9, 1975, Perth

ጋኔሻ:ሽሪላ ፕራብሁፓድ እውቀት በመንፈሳዊ ንጉሶች የተላለፈ ከሆነ: ኤቫም ፓራምፓራም ፕራፕታም (ብጊ4 2)እንዴት ነው ታድያ ይህ እውቀት የጠፋው? ፕራብሁፓዳ:ይህም እወቀት በደንብ ስለአለተላለፈ ነው:በግምት ብቻ መረዳት ሲጀምሩ ነው: ወይንም እንደ አለ ሳይቀየር መተላለፍ ሲቆም ነው: ለውጥ አድረገውበት ሊሆን ይችላል: ወይንም አላስተላለፉት ይሆናል: ለምሳሌ ለአንተ ባስተላልፍልህ:አንተም ካላስተላለፍከው ሊጠፋ ይችላል: አሁን የእኛ ክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ እኔ እያለሁ እየተካሄደ ነው: እኔ ከአለፍኩም በኋላ:እናንተ እንደ አለ ካላስተላለፋችሁት ሊጠፋ ይችላል: አሁን እንደምታደርጉት ከቀጠላችሁ ግን ይህ ሊራመድ ይችላል: