AM/Prabhupada 0572 - “በእኔ ቤተመቅደስ ውስጥ መጥተህ ለመናገር አልፈቅድልህም” ለምን ትላላችሁ



Press Interview -- December 30, 1968, Los Angeles

ጋዜጠኛ፡ ተግባራዊ በሆነ መንገድ እንዲህ ታስባለህን? እንደምታስበው ይህ እንቅስቃሴህ በአሜሪካው ውስጥ ተቀባይነት አግኝቶ የሚስፋፋ ይመስልሀልን?

ፕራብሁፓድ፡ እስከ አሁን እንደአየነው ትልቅ እድል እንዳለ ነው፡፡

ጋዜጠኛ፡ የአንተም መልእክት ከሞሰስ ከእየሱስ ወይንም ከሌሎች ታላላቅ የሀይማኖት መሪዎች የተለየ አይደለምን? ሰዎችም የአስሩን ትእዛዛት የሚከተሉ ከሆነ ይህ በቂ አይደለም ወይ?

ፕራብሁፓድ፡ እኛ ሰዎችን እንጠይቃለን... እንዲህ ግን አንላቸውም “ይህንን ሀይማኖታችሁን ትታችሁ ወደ እኛ ኑ” የምንላቸው ግን በሀይማኖታችሁ የተደነገገውን መመሪያዎች ተከተሉ ነው፡፡ ልክ ትምህርቱን እንደጨረሰ ተማሪ፡፡ አንዳንድ ግዜም በህንድ ውስጥ ይህንን እናያለን፡፡ ምንም እንኳን ተማሪው ማስተርሱን በህንድ ዩንቨርስቲ ቢጨርስም ወደ ሌላ ሀገር ሂዶ ትምህርቱን ይቀጥላል፡፡ ለምን ይህን ያደረጋል? ይህም የበለጠ እውቀት ለማግኘት ነው፡፡ እንደዚህም ሁሉ ማናቸውምንም የሀይማኖት ስርዓት መከተል ትችላለህ፡፡ ነገር ግን በዚህ በክርሽና ንቃታችን የበለጠ በመንፈሳዊ እርምጃ የምትዳብር ከሆነ ለምን አትቀበለውም? ሰለ አብዩ አምላክ ኮስተር ብለህ መከታተል ከፈለግህ ይህ አስፈላጊ ነው፡፡ ለምን እኔ ክርስትያን ነኝ እኔ ይሁዳ ነኝ እያልክ የንቃት ትምህርታችንን ትሸሻለህ? ለምንስ እንዲህ ትላለህ “ኦ እኔ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ንግግር እንድታደርግ አልፈቅድልህም፡፡” እኔም ሰለ አብዩ አምላክ የምናገር ከሆነ ለምን ልከለከል ይገባኛል?

ጋዜጠኛ፡ እውነት ነው ከዚህ በላይ መስማማትም አያስፈልገኝም፡፡ በእርግጥ አንተም ታውቃለህ እኔም እንደማውቀው አሁን በቅርብ ግዜ ውስጥ አንድ ካቶሊክ እዚህ እንዲመጣ አልተፈቀደለትም ነበር፡፡ ይህም በሌላ ቤተክርስትያን ምክንያት ነበረ፡፡