AM/Prabhupada 0609 - እናንተ እያንዳንዳችሁ የሀሬ ክርሽናን መዝሙር ስትዘምሩ ትገኛላችሁ፡፡ የእኔ ስራ መሳካት ማለት ይህ ነው፡፡



Arrival Lecture -- Los Angeles, May 18, 1972

ውድ ልጆቼ ከስድስት ዓመት በፊት ወደ አገራችሁ መጣሁ፡፡ ይህም ብቻዬን ከካርታሎቼ ጋር ነበር፡፡ አሁን እናንተ ብዙ ሆናችሁ ሀሬ ክርሽናን ስትዘምሩ ትገኛላችሁ፡፡ የእኔም ተልእኮ መሳካት ማለት ይህ ነው፡፡ ይህም የቼታንያ መሀፕራብሁ ትንቢት ነበረ፡፡ ፕርትሂቪቴ ዓቼ ያታ ናጋራዲ ግራም ሳርቫትራ ፕራቻራ ሆይቤ ሞራ ናም (ቸብ፡ አንትያ ክሀንዳ 4 126) ጌታ ቼታንያ ይህንን የቅዱስ ስም ዝመራ የፈለገው በየከተማው እንዲካሄድ ነው፡፡ “በምድር ላይ በሚገኙት ብዙ ከተሞች እና ሰፈሮች ስሜ እየተዘመረ ይገኛል፡፡” እርሱም ክርሽና ራሱ ነው፡፡ “ስቫያም ክርሽና ክርሽና ቼይታንያ ናሚኔ” ስሙን ብቻ ነው ወደ ክርሽና ቼይታንያ የቀየረው፡፡ ስለዚህ የእርሱ ትንቢት በከንቱ ሊቀር አይችልም፡፡ ይህም የተረጋገጠ ነው፡፡ ፕላኔም ወደ አሜሪካ ለመሄድ ነበረ፡፡ “አሜሪካ ዓለምን በመምራት ላይ ያለ አገር ነው፡፡” “የአሜሪካንም የወጣት ትውልድ ማሳመን ከቻልኩኝ እነርሱም ይህንን ሊቀጥሉ እና እንደሚያስፋፉት ባለ ሙሉ ተስፋ ነበርኩ፡፡” እኔም እድሜዬ የገፋ ነው፡፡ እዚህም ስመጣ እድሜዬ 70 ነበረ፡፡ አሁን ግን እድሜዬ 76 ገብቷል፡፡ ስለዚህ ማስጠንቀቂያዬ ተሰጥቶን ነበረ፡፡ በ 1971 ከፍተኛ የልብ ድካም ተሰምቶኝ ነበረ፡፡ ይህንንም ሁላችሁ ታቁታላችሁ፡፡ የቼይታንያ መሀፕራብሁም ተልእኮ አሁን በእናንተ እጅ ውስጥ ነው ያለው፡፡ እናንተ አሜሪካዊ ልጆች በጣም አዋቂ እና በክርሽና በረከቱን ያገኛችሁ ናችሁ፡፡ ድህነት ያጠቃችሁም አይደላችሁም፡፡ በቂ የሆነ ሀብት እና የገነነ ኑሮ ያላችሁ ናችሁ፡፡ የሚያስፈልግም ቁሳዊ ነገር ሁሉ በእጃችሁ ያለ ነው፡፡ ይህንንም የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ ኮስተር ብላችሁ ብትወስዱት አገራችሁ ልትድን ትችላለች፡፡ በዚህም መላ ዓለምም ሊድን ይችላል፡፡