AM/Prabhupada 0703 - እራሳችሁ በክርሽና ንቃት ላይ የመሰጣችሁ ከሆነ ይህም “ሰማድሂ” ይባላል፡፡



Lecture on BG 6.46-47 -- Los Angeles, February 21, 1969

ድቮቲ፡ ፕራብሁፓድ? የሰማድሂ የስምንቱ የዮጋ ስርዓት እና የብሀክቲ ዮጋ የሰማድሂ ስርዓት አንድ ናቸውን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን “ሰማድሂ” ማለት ሀሳባችንን በቪሽኑ የአብዩ አምላክ በሰመጠ ሀሳብ ማሰማራት ማለት ነው፡፡ ይህ ሳማድሂ ይባላል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ሀሳባችሁን በክርሽና የሰመጠ አስተሳሰብ ብታሰማሩት ይህም ሰማድሂ ይባላል፡፡ ሌላ ጥያቄ? ወጣት ልጅ፡ ስዋሚጂ ባለፈው እንደጠቀስከው ብዙ ስትበሉ ትከፍላላችሁ ብለህ ነበረ፡፡ ታድያ ለድቮቲዎችስ እንዴት ነው? ድቮቲዎችስ ብዙ ፕራሳድ ሲበሉስ?

ፕራብሁፓድ፡ በተጨማሪ ለመብላት ትፈልጋለህ? ወጣት ልጅ፡ ለማወቅ ስለፈለግሁ ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ጨምረህ የምትበላ ይመስልሀል? ጨምረህ መብላት ትችላለህ፡፡ ወጣት ልጅ፡ እችላለሁ ብዬ አስቤ ነበረ

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ጨምረህ መብላት ትችላለህ፡፡ ይህም የህክምና ምክር ነበረ፡፡ ምግብን በመመገብ ሁለት ዓይነት ችግሮች አሉ፡፡ አንደኛው ከሚገባው በላይ መብላት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከሚገባው በታች መብላት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እድሜው ለገፋ ሰው ከሚገባው በላይ መብላት ጥሩ አይደለም። ለልጆች ደግሞ ከሚገባው በላይ መብላት ጥሩ ነው፡፡ ሰለዚህ ጨምረግ መብላት ትችላለህ፡፡ እኔ ግን አልችልም፡፡ ወጣት ልጅ፡ ታማላ እና ቪሽኑጃንስ? (ሳቅ)

ፕራብሁፓድ፡ እነሱ አይችሉም፡፡ አንተ ግን ትችላለህ፡፡ የፈለግኅውን ያህል መብላት ትችላለህ፡፡ ነፃ ማለፊያ ተሰጥቶሀል፡፡ (ሳቅ)