AM/Prabhupada 0850 - ገንዘብ የምታገኙ ከሆነ መፃህፍትን አትሙ፡፡



750620d - Lecture Arrival - Los Angeles

ሌላ አዲስ ነገር መፍጠር አያስፈልግም፡፡ (ሳቅ) ሌላ ማምረት የሚገባን ነገር የለም፡፡ የምንከተለው ስርዓት ግን ይኅው ነው፡፡ መከተል የሚገባን ቀድሞ በአርአያ ያስተማሩንን መምህራን ብቻ ነው፡፡ የእኛም እንቅስቃሴ በጣም ቀላል ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ሌላ ነገር መፍጠር ስለማያስፈልገን ነው፡፡ የሚጠበቅብን ነገር ቢኖር፤ የቀድሞ መምህራን ያስተማሩትን ቃላቶች እና ትእዛዞችን መድገም ብቻ ነው፡፡ ክርሽና ብራህማን አስተማረ፡፡ ብራህማ ናራዳን አስተማረ፡፡ ናራዳ ቭያሳዴቭን አስተማረ፡፡ ቭያሳዴቭ ማድሀቫ አቻርያን አስተማረ፡፡ በዚህም መንገድ፤ ማድሃቬንድራ ፑሪ፣ ኢሽቫራ ፑሪ፣ ቼታንያ ማሀፕራብሁ፣ ከዚያም ስድስቱ ጐስዋሚዎች፣ ከዚያም ሽሪኒቫስ አቻርያ፣ ካቪራጅ ጎስዋሚ፣ ናሮታማ ዳስ ታኩር፣ ቪሽቫናት ቻክራቫርቲ፣ ጃጋናት ዳስ ባባጂ፣ ብሀክቲቪኖድ ታኩር፣ ጎውራኪሾር ዳስ ባባጂ፣ ብሀክቲሲድሀንታ ሳራስቫቲ፣ ከዚያም ቀጥሎ እኛም የእነሱን ፈለግ ተከትለን ያስተማሩትን በመድገም ላይ እንገኛለን፡፡ ሌላ የተለየ ስራ የለንም፡፡ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴም ስርዓት ይህንኑ ተከትሎ የሚሄድ ነው፡፡ በየቀኑም እንዲህ እያላችሁ በመዘመር ላይ ትገኛላችሁ፡፡ “ጉሩ ሙክሀ ፓድማ ቫክያ ሲቴቴ ኮሪያ አይካ አራና ኮሪሆ ማኔ አሳ” ይህም ቀላል ስርዓት ነው፡፡ የምንቀበለውም የመንፈሳዊ ትምህርት ሁሉ የሚመጣው በጉሩ ፓራምፓራ ወይንም በድቁና ስርዓት ተተላልፎ የሚመጣ ነው፡፡ ስለዚህ ስራችን የጉሩን ወይንም የመንፈሳዊ መምህራችንን ትእዛዞችን መቀበል ብቻ ነው፡፡ ይህንንም ስርዓት እና ትእዛዝ ከልባችን ተቀብለን የምንከተለው ከሆነ ሕይወታችን ስኬታማ ሆነ ማለት ነው፡፡ ይህም በተግባር ሊታይ የሚችል ነው፡፡ እኔ በግሌ ምንም ዓይነት ምጠና ወይም ሙያ የለኝም፡፡ ቢሆንም ግን ጥረቴ ሁሉ ጉሩዬን ወይንም መምህሬን ለማስደሰት ብቻ ነው፡፡ ይኅው ነው፡፡ የእኔም ጉሩ መሀራጅ የጠየቀኝ ነገር ቢኖር፤ “ምንም ዓይነት ገንዘብ ስታገኝ መፃህፍትን አትም፡፡” በዚያን ግዜ የግል ስብሰባ እየተካሄደ ነበረ፡፡ አንዳዶቹ የመንፈሳዊ ወንድሞቼ እዚያው ነበሩ፡፡ ይህም ራድሀ ኩንድ በተባለችው ኩሬ አጠገብ ነበረ፡፡ በዚያም ግዜ ጉሩ መሀራጄ እንዲህ ብሎ ያነጋግረኝ ነበር፡፡ “ይህን የብሀግባዛር የእብነ በረድ ቤተ መቅደስ ከገነባን ጀምሮ ብዙ ብጥብጥ በመሀከል ሲታይ ቆይቷል፡፡“ ”እያንዳንዱም ሲያስብ የነበረው ማን ይህን ክፍል ይይዛል፣ ማንስ ያንኛውን ክፍል ይይዛል በማለት ነበር፡፡“ ”አንዳንድ ግዜ ሳስበው ይህንን ቤተ መቅደስ እና እብነ በረድ ሽጬ መፅሀፍ ባተምኩበት ኖሮ እያልኩ አስባለሁ፡፡“ ታድያም በዚህን ግዜ መፅሀፍትን ለማተም በጣም ፍላጎት እንዳለው ከአፉ ለማዳመጥ በቃሁ፡፡ እርሱም በግሉ እንዲህ አለኝ፡፡ ”ገንዘብ የምታገኝ ከሆነ መፃህፍትን አትም፡፡“ በዚህም ምክንያት ይህንን መልእክት አተኩርበታለሁ፡፡ “መፃህፍቶቹ የታሉ? መፃህፍቶቹ የታሉ? መፃህፍቶቹ የታሉ?" ስለዚህ እባካችሁ ይህንን ምኞት ለሟሟላት እርዱኝ፡፡ የምጠይቀውም ነገር ቢኖር ይኅው ነው፡፡ ”የተለያዩ ብዙ መፃህፍቶችን በተቻለ መንገድ በተለያዩ ቋንቋዎች በማተም በመላው ዓለም ለማከፋፈል ሞክሩ፡፡“ በዚህም እንቅስቃሴ የክርሽና ንቃት በቀልጣፋ መንገድ ሊስፋፋ እና ሊያድግ ይችላል፡፡ በአሁኑ ግዜ እንደምናየው የተማሩት ስኮላሮች እና መምህራን የእኛን የንቃት እንቅስቃሴ በአክብሮት እያዩት እና እያመሰገኑት ነው፡፡ ይህም መፃህፍቶቻችንን በማንበብ እና ተግባራዊ የሆነ ውጤትንም በማየታቸው ነው፡፡ ዶክተር ስቲልሰን ጁድሀ የተባለውም አንድ መፅሀፍ ፅፎ ይገኛል፡፡ ይህንንም መፅሀፍ ሳታውቁት አትቀሩም፡፡ ይህም ”ሀሬ ክርሽና እና የባህል ለውጥ“ የተሰኘ ነበር፡፡ ይህም ስለኛ እንቅስቃሴ የሚያወራ በጣም ጥሩ የሆነ መፅሀፍ ነው፡፡ ስለ እንቅስቃሴያችንም አስፈላጊነት በትንተና ገልጿል፡፡ የተቀበለውም ”ስዋሚጂ ያደረከው ነገር በጣም የሚያረካ ነው፡፡“ በማለት ነው፡፡ ”ምክንያቱም እነዚህን ኪኒን እና በሀሺሽ ሱስ የተያዙትን “ሂፒዎች” ወደ ሽሪ ክርሽና አገልጋይነት ቀየርካቸው፡፡“ በዚህም ምክንያት የሰው ልጅ ሕብረተሰብን ለማገልገል ዝግጁ ሆነው ተነስተዋል፡፡