AM/Prabhupada 1063 - የምናገኘው ደስታ እና መከራ ከምንሰራው ስራ እና ውጤቱ የተያያዘ ነው፡፡



660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

በሕይወታችን ውስጥ የምናገኘው ደስታ ሁሉ ቀድሞ ካደረግነው ስራ እና ከስራችን ውጤት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አሁን ለምሳሌ እኔ የንግድ ሰው ነኝ እንበል፡፡ በብዙም የአእምሮ ድጋፍ እና ጥረት በማድረግ ከፍ ያለ የባንክ ገነዘብ ለማከማቸት በቃሁ እንበል፡፡ በዚህም ግዜ እኔ በሀብቴ ተደሳች ልሆን እችላለሁ፡፡ ይህንንም ሀብት በመጠቅም አንድ ጥሩ አዲስ ንግድ ጀመርኩ እንበል፡፡ ንግዱንም የተሳካ ለማድረግ ካልቻልኩኝ የሰበሰብኩትን ሀብት ሁሉ በማጣት ችግር ውስጥ ለመውደቅ እችላለሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በማንኛውም ስራ ላይ ተሰማርተን በስራችን ውጤት ወይ እንደሰታለን ወይንም ችግር ውስጥ እንወድቃለን፡፡ ይህም ካለፈው ስራችን ውጤት የተያያዘ ሂደት ካርማ ተብሎ ይታወቃል፡፡ "ኢሽቫራ፡ ጂቫ፡ ፕራክርቲ" ወይንም ደግሞ አብዩ ጌታ ነዋሪ ነፍሳት እና የቁሳዊው ዓለም፡፡ ዘለዓለማዊው ግዜ እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎች፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልፀዋል፡፡ ከነዚህም ከአምስቱ መሀከል አብዩ ጌታ እንዲሁም ህያው ነፍሳት ይህ ቁሳዊ ዓለም እና ግዜ እነዚህ አራቱ ዘለአለማዊ ሆነው ይገኛሉ፡፡ የፕራክርቲ ክስተት ጊዜያዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በውን ያልተከሰተ ሀሰታዊ ዓለም አይደለም፡፡ አንዳንድ ፈላስፋዎች ይህ ቁሳዊ አለም በውን ያልተከሰተ ሀሰታዊ ወይንም ህልማዊ ዓለም ነው ብለው ይገምታሉ፡፡ ነገር ግን በብሀገቨድ ጊታ ገለጻ ወይንም በቫይሽናቫዎች የፍልስፍና ገለፃ ይህ አሰተያየት እውነትን የተመረኮዘ ሆኖ አይገኝም፡፡ የዓለም ፍጥረታት ሁሉ እንደ ሀሰታዊ ወይንም እንደ ህልም ናቸው ብለው አይገምቱም፡፡ ይህ የቁሳዊ ዓለም ጊዜያዊ ቢሆንም እውነታዊ እንደሆነ ያረጋግጣሉ፡፡ ይህም ልክ በሰማይ ላይ እንደሚከማች ደመና እና ቀጥሎም የክረምት ወቅት እንደሚጀምረው ሊመሰል ይችላል፡፡መጥቶ እንደሚሄድ ደመና ሊቆጠር ይችላል፡፡ ከዚህም የክረምት ወቅት በኋላ የተለያዩ ሰብሎች በመሬት ላይ አረንጓዴ ሆነው በቅለው እናያለን፡፡ የክረምት ወቅቱም ሲያልፍ በሰማይ የምናያቸው ደመናዎች ሁሉ ሲጠፉ ይታያሉ፡፡ ከዚህም በኋላ ቀስ በቀስ የምያቸው ሰብሎች ሁሉ መድረቅ ይጀምራሉ፡፡ መሬቱም ሁሉ ደርቆ ይታያል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ይህ ቁሳዊ የትእይንተ ዓለም ፍጥረት በተወሰነ ግዜ ላይ ይፈጠራል ለተወሰነ ግዜም ይቆያል እንደዚሁም ሁሉ በተወሰነ ግዜ ውስጥ ይደመሰሳል ወይንም ይጠፋል፡፡ ይህንንም ከብሀገቨድ ጊታ ቅዱስ መፅሀፍ ልንረዳው እንችላለን፡፡ "ብሁትቫ ብሁትቫ ፕራሊያቴ" (ብጊ፡ 8 19) ይህም ትእይንተ ዓለም በተወሰነ ግዜ ውስጥ ግዙፍ ሆኖ በውን ይታያል፡፡ ከግዜ በኋላ ደግሞ ከውን ክስተት ይጠፋል፡፡ ይህ የፕራክርቲ ስራ ነው፡፡ ይህም ክስተት እና መሰወር ለዘለዓለም የሚካሄድ ነው፡፡ ስለዚህም ዘለዓለማዊ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሀሰታዊ ግን አይደለም፡፡ ምክንያቱም አብዩ ጌታ እራሱ "ማማ ፕራክርቲ" ብሎ ገልፆታል፡፡ አፓሬያም ኢታስ ቱ ቪድሂ ሜ ፕራክርቲም ፓራም (ብጊ፡7 5) ብሂና ፕራክርቲ ብሂና ፕራክርቲ አፓራ ፕራክርቲ ይህ የቁሳዊ አለም ፍጥረት የተገነጠለ የአምላክ ሀይል እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ህያው ነፍሳትም የፈጣሪ ወገን እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን እንደ ቁሳዊው ፍጥረት የተገነጠሉ አይደሉም፡፡ ህያው ነፍሳት ሁሉ ከአምላክ ጋር ዘለዓለማዊም ግኑኝነት አላቸው፡፡ ፈጣሪ ጌታ ህያው ነፍሳት ቁሳዊው ፍጥረት እንዲሁም ግዜ በውስጣዊ ሂደት የተዛመዱ እና ዘለአለማዊ ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን ሌላው ካርማ ተብሎ ከዝርዝሩ የተጠቀሰው አንዱ ዘለዓለማዊ እንዳልሆነ ተገልጿል፡፡ የካርማ ወይንም የድርጊቶቻችን ውጤት በጣም ጥንት ከሆነ እንቅስቃሴ የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ዛሬ የምንደሰትባቸው ወይንም የምንሰቃይባቸው ክስተቶች ሁሉ ለማሰብ ከሚያዳግት ከጥንት ግዜ በፊት ካደረግናቸው እንቅስቃሴዎች የመጣ ውጤት ነው፡፡ ቢሆንም ግን ይህንን ካርማ ወይንም ያልተከሰተ የእንቅስቃሴ ውጤትን ለመለወጥ እንችላለን፡፡ ይህም ለውጥ እንደ መንፈሳዊ እውቀታችን ጥራት የሚወሰን ነው፡፡ እኛ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሰማርተን እንገኛለን፡፡ ነገር ግን የትኛው ከጥሩ ወይንም መልካም ካልሆነ ውጤት ሊያርቀን የሚችለውን እንቅሰቃሴ መምረጥ እንደሚገባን እውቀቱ ላይኖረን ይችላል፡፡ ይህ እውቀትም ሲኖረን ከስራችን የመከራ ውጤት ሊያድነን ይችላል፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ በጥልቅ ተገልጿል፡፡ የኢሽቫራ ደረጃው ወይንም ስፍራው የላቀና አብይ የንቃት ህሊና ደረጃ ላይ ነው፡፡ የኢሽቫራ ደረጃው ወይንም አብዩ ጌታ የላቀና አብይ የንቃት ህሊና ያለው ነው፡፡ የጂቫ ወይንም ነዋሪ ነፍሳት የጌታ ቅንጣፊ አካል እንደመሆናችንም የተመጣጠነ ንቃተ ህሊና አለን፡፡ ነዋሪ ነፍሳት ሁሉ ንቃት አላቸው፡፡ እንደተገለጸውም መላ ነፍሳት እና የቁሳዊው ዓለም ፕራክርቲ ተብለን እንታወቃለን፡፡ ቢሆንም ግን ከሁለቱ መሀከል እኛ መላ ነፍሳት እንደ አምላክ ንቃት ሲኖረን የቁሳዊው ዓለም ግን ሕይወት ወይንም ንቃት የለውም፡፡ የቁሳዊው አካል ፕራክርቲ ንቃት የለውም፡፡ ይህ ነው ልዩነቱ፡፡ በዚህም ምክንያት የጂቫ ፕራክርቲ (ነፍሳት) ከፍተኛው ፕራክርቲ ሆኖ ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም ጂቫ እንደ ጌታ ህያው በመሆኑ ወይንም ንቃት ስላለው ነው፡፡ ነገር ግን ጌታ ፈጣሪ የላቀ ንቃት እንደአለው ቢታወቅም ጂቫ ወይንም ነፍሳት ደግሞ የላቀ ንቃት አላቸው ማለት አይደለም፡፡ ህያው ነፍሳት እንደ ጌታ የላቀ ንቃት ወይንም የጥራት ደረጃ በማናቸውም ግዜ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ሊኖራቸው ይችላል የሚለውም ያልተጨበጠ ሀሳብ ወይንም ፍልስፍና አሳሳች የሆነ ነው፡፡ ንቃት ይኑረን እንጂ እንደ ጌታ የላቀ ወይንም የበለፀገ ንቃት በማናቸውም ግዜ ሊኖረን አይችልም፡፡