AM/Prabhupada 1069 - ሀይማኖት የእምነትን አመለካከት የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ እምነትም ሊቀያየር የሚችል ነው፡፡ ነገር ግን ዘለዓለማዊው መንፈሳዊ አገልግሎት ወይን



660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

ስለዚህ ቀድሞ እንደተጠቀሰው “ሳናታን ድሀርማ” እና ዓብዩ ጌታ ሳናታን ወይንም ዘለዓለማዊ ናቸው፡፡ እንደዚህም ሁሉ የዓብዩ ጌታ መኖርያ መንፈሳዊ ዓለምም ሳናታና ወይንም ዘለዓለማዊ ነው፡፡ ነፍሳትም ሁሉ ሳናታና ወይንም ዘለዓለማዊ ናቸው፡፡ ስለዚህ የነፍስ ከሳናታን ወይንም ዘለዓለማዊ ከሆነው ዓብዩ ጌታ ጋር መሆን እና ዘለዓለማዊ ከሆነው የመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ለመኖር መብቃት የሰው ልጅ ሕይወት መድረሻው ነው፡፡ ዓብዩ ጌታ ለፍጥረታት ሁሉ በጣም ሩህሩህ ነው፡፡ ምክንያቱም እያንዳዳቸው ነፍሳት የዓብዩ ጌታ ልጆች ሰለሆኑ ነው፡፡ ዓብዩ ጌታም እንዲህ ብሏል “ሳርቫ ዮኒሹ ኮንቴያ ሳምብሀቫንቲ ሙርታዮ ያህ” (ብጊ 14.4) እያንዳንዱ ዓይነት ህያው ፍጥረታት ባላቸው ካርማ ወይንም ቀድሞ ካደረጉት እንቅስቃሴያቸው አንፃር የተፈጠሩ የተለያዩ ፍጥረታት ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን ዓብዩ ጌታ የሁሉም አባት እንደሆነ አውጇል፡፡ ስለዚህም ዓብዩ ጌታ እነዚህን የተዘነጉ ውስን ነፍሳት ወደ መንፈሳዊ ደረጃቸው ለመመለስ በምድር ላይ ወርዶ ለማስተማር ይመጣል፡፡ ይህም ወደ ሳናታን ድሀርማ ወይንም ወደ ሳናታን መንፈሳዊው ሰማይ ለመመለስ ነው፡፡ ይህም ዘለዓለማዊው ነፍስ ወደ ዘለዓለማዊው ህይወቱ እንዲመለስ እና ከዓብዩ ጌታ ጋር በፍቅር ዘለዓለማዊ ኑሮ እንዲኖር ነው፡፡ አብዩ ጌታም የተለያዩ ወልዶችን ተመስሎ ወደ ምድር ይመጣል፡፡ አልፎ አልፎም የታመኑትን አገልጋዮቹን እና ልጆቹን ወይንም አቻርያዎችን (መምህራንን) ወደ ምድር ይልካል፡፡ ይህም እነዚህን ውስን ነፍሳት ወደ መንፈሳዊ ዓለም ለመመለስ ነው፡፡ ስለዚህ ሳናታን ድሀርማ ማለት ሌላ የተለየ የሀይማኖት ስርዓት አይደለም፡፡ ይህ ዓብዩ ጌታን ለማገልገል ዘለዓለማዊ የሆነ የነፍሳት የአገልግሎት ስርዓት ነው፡፡ ስለዚህ “ሳናታን ድሀርማ” ማለት ነፍሳት ለዓብዩ ጌታ ለዘለዓለም መስጠት የሚገባቸው አገልግሎት ማለት ነው፡፡ መምህር ሽሪፓድ ራማኑጃ አቻርያ ”ሳናታን“ የሚለውን ቃል እንዲህ ብሎ ገልጾታል፡፡ ”መጀመሪያ እና መጨረሻ የሌለው ነገር፡፡“ ስለዚህ ”ሳናታን ድሀርማ“ ስንል በቀላሉ መውሰድ ይገባናል፡፡ ስልጣን ያለውን የመምህር ሽሪፓድ ራማኑጃ አቻርያን ትምህርት በመቀበል ሳናታን ድሀርማ መጀመሪያ እና መጨረሻ እንደሌለው መረዳት ይገባናል፡፡ ሀይማኖት የሚለው ቃል ከሳናታን ድሀርማ ትንሽ የተለየ ነው፡፡ ሀይማኖት የእምነትን ይዘት የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ እምነት ደግሞ ሊቀያየር የሚችል ነው፡፡ አንድ ሰው የአንድ ሀይማኖትን ስርዓት ሊከተል ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን ይህንን የሀይማኖት ስርዓት ቀይሮ ወደ ሌላ ያሀይማኖት ስርዓት ሊያተኩር ይችላል፡፡ ሳናታን ድሀርማ ማለት ግን ሊቀየር የማይችል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ውሀ እና የውሀ ፈሳሽነት ሊነጣጠሉ የማይችሉ ናቸው፡፡ ሙቀት እና እሳት ሊነጣጠሉ የማይችሉ ናቸው፡፡ ከእሳት ውስጥ ሙቀትን ለማውጣት አይቻልም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ሳናታን ድሀርማ ተብሎ የሚታወቀው ዘለዓለማዊው የዓብዩ ጌታ አገልግሎት ከነፍስ ሊነጠል አይችልም፡፡ ይህንን ለመቀየር አይቻልም፡፡ ስለዚህ የእኛ ሀላፊነት ይህንን የማይቀየረው ዘለዓለማዊው የነፍስ ስራ ምን እንደሆነ በትክክል መረዳቱን ነው፡፡ ስለዚህ ስለ ሳናታን ድሀርማ ስናወራ በቀላሉ መውስድ ይገባናል፡፡ መምህር ሽሪፓድ ራማኑጃ አቻርያ እንደገለፀው መጀመሪያ እና መጨረሻ እንደሌለው መሆኑን መረዳት ይገባናል፡፡ ይህ መጀመሪያ እና መጨረሻ የሌለውም ነገር ምንም ገደብ የሌለው እና በሀይማኖታዊ ወይንም በአካባቢ ወሰን የተቆጠበ አይደለም፡፡ ስለ ሳናታን ድሀርማም የኮንፍረንስ ንግግር ስናደርግ በአንዳንድ የሀይማኖት ስርዓት የተሰማሩ ሰዎች ይህንን በተሳሳተ መንገድ ሊያዩት ይችላሉ፡፡ ወደተወሰነ ሀይማኖትም ልንስባቸው እየሞከርን እያለን ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ነገሩን ጠለቅ ብለን ብንመረምር እና በሳይንሳዊ መንገድ ብናጠናው ሳናተን ድሀርማ ትርጉም ያለው ፈለግ መሆኑን በቀላሉ ለመረዳት እንችላለን፡፡ ይህም ትርጉም የሚኖረው ለምድር ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለመላ የትእይንተ ዓለም ፍጥረታት ሁሉ ነው፡፡ ከሳናታን ድሀርማ የተለየ አዲስ የሀይማኖት እምነት በሰው ልጅ ህብረተሰብ ውስጥ እንደ አዲስ ሊመሰረት ይችላል፡፡ ሳናታን ድሀርማ ግን ምንም ዓይነት የተጀመረበት ታሪክ አይኖረውም፡፡ ምክንያቱም ከነፍስ ጋር ለዘለዓለም የሚኖር ሰለሆነ ነው፡፡ ነፍሳትንም ብንወስድ ከሻስትራ ወይንም ከቬዲክ ቅዱስ መፃህፍት እንደምንማረው ነፍሳት ሊወለዱም ወይንም ሊሞቱም አይችሉም፡፡ በብሀገቨድ ጊታም ይህ በግልፅ ተተንትኖ ተብራርቷል፡፡ ይህም ነፍሳት እንደማይወለዱ እና ወደፊትም ሊሞቱ እንደማይችሉ ነው፡፡ ነፍስ ዘለዓለማዊ ናት፣ ልትፈርስ አትችልም፣ ይህም ጊዜያዊ ገላ ከፈረሰ በኋላ ነፍስ ህይወቷን ለመቀጠል የምትችል ናት፡፡