AM/Prabhupada 0001 - ወደ አስር ሚሊዮን አስፋፉት፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on CC Adi-lila 1.13 -- Mayapur, April 6, 1975

ጌታ ቼይታንያ ማሃፕራብሁ ለመምህራኖቹ ሁሉ እንዲህ አለ... "ኒትያናንዳ ፕራብሁ: አድቨይታ ፕራብሁ: እና: ሽሪቫሳዲ ጐውራ ብሃክታ ቭርንዳ" እነዚህ ሁሉ የጌታ ቼይታንያ ማሃፕራብሁ ትእዛዝ ተክታዮች ናችው እና እናንተም የእነዚህ መምህሮችን ፈላግ ለመከታተል ሞክሩ በዚህም ህይወታችሁ የተሟላ ይሆናል መምህር ለመሆን በጣም አዳጋች አይዳለም በመጀመርያ ለመምህሩ ትጉህ አገልጋይ መሆን ያስፈልጋል የሚናገረዉን በትጋት መከተል ያስፈልጋል የክርሽናን ትምህርት በማስፋፋት መምህሩን ማስደስት ያስፈልጋል ይህ በጣም አዳጋች አይደለም የጉሩ ማሃራጅ (የመምህራችሁን) ትእዛዝ ለመከተል ሞክሩ ክርሽና ንቃትን አስፋፉ: ይህ የሽሪ ቼይታንያ ትእዛዝ ነው "አማራ አጋይ ጉሩ ሃሪያ ጃሬ ታራ ጃሬ ታኮ ክርሽና ኡፐዴሽ" የእኔን ትእዛዝ በመከተል ጉሩ (መምህር) መሆን ትችላላችሁ የአቻርያዎችን ህግ እና ደንብ በመከተል የክርሽናን ትእዛዝ ለማሳወቅ ሞክሩ "ጃሬ ዳኮ ታሬ ካሆ ክርሽና ኡፐዴሽ" ሁለት ዐይነት ክርሽና ኡፐዴሾች አሉ:: ኡፓዴሽ ማለት ትእዛዝ ማለት ነው በክርሽና የተስጠ ትእዛዝ: የክርሽና ኡፕዴሽ ነዉ ስለ ክርሽና የተቀበሉት ትእዛዝም ክርሽና ኡፓዴሽ ነው ክርሽና ቪሻያ ኡፕዴሸ እራሱ ክርሽና ኡፐዴሽ ነው:: ሳማሳ ሻስቲ ታት ፑሩሻ ሳማሳ ክርሽና ቪሻያ ኡፕዴሸ እራሱ ክርሽና ኡፐዴሽ ነው:: ባሁ ቭርሂ ሳማሳ የሳንስክሪት ቋንቋ ስዋስው እየተነተነ ነው:: እና ክርሽና ኡፐዴሸ ማለት ብሃገቨድ ጊታ ነው:: በእርሱም ትእዛዙን በቀጥታ ሰጥቷል:: የክርሸናን ኡፕዴሸ የሚያስፋፋ: በቀላሉ ክርሽና ያለውን ይደግ ማል ማለት ነው:: እንደዚሁም አቻርያ ይሆናል:: ሁሉም በመፅሃፉ ስለተገለጠ: ይህ ቀላል ነው ማለት ነው:: የስማነውን በቀላሉ እንደ ፓሮት መድገም አለብን ልክ እንደ ፓሮት ሳይሆን:: ፓሮት ትርጉሙን ሳይረዳ ድምፁን መድገም ብቻ ነው የሚያውቀው እናንተ ግን ትርጉሙን መረዳት አለባችሁ:: አለበለዛ እንዴት ማስረዳት ትችላላችሁ? የክርሽናን ንቃት ለማስፋፋት እንፈልጋለን የክርሽናን ንቃት ለማስፋፋት የክርሽናን ቃል ለመድገም ራሳችሁን አዘጋጁ:: ሰው ትርጉም ባልስጠው በጥሩ መንገድ እና ወደፊት: ለምሳሌ አስር ሺህ ቢኖራችሁ ከዛ ደግሞ ወደ አንድ መቶ ሺህ መስፋፋት እንችላለን ያ ያስፈልጋል:: ከዛ ደግሞ ወደ ምቶ ሺህ ሚልዮን ከሚሊዮን ወደ አስር ሚልዮን:: አገልጋዮች "ሀሪ ቦል! ጃያ!" እንዲሁም የአቻርያ እጥረት አይኖርም:: ህብረተሰቡም የክርሸናን ንቃት በቀላሉ ሊገባቸው ይችላል:: እና ይህን ህብረተሰብ ፍጠሩ በሀሰታዊው ትእቢት አትጠቁ:: የአቻርያዎቹን ትእዛዝ ተከተሉ:: እራሳችሁን የበሰለ አድርጉ:: ይህም ማያን ለመዋጋት የቀለለ እንዲሆን ያደርግላችኋል:: አቻርያዎች ማለት: በማያ ስራ ላይ ጦርነት ያወጁ ማለት ነው::