AM/Prabhupada 0002 - የእብድ ስልጣኔ፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on SB 6.1.49 -- New Orleans Farm, August 1, 1975

ሀሪ ኬሽ: ትርጉም "ህልም የሚያልም ስው: በህልሙ በሚታየው ገላ እንደሚቀሳቀስ ሁሉ"፣ "ወይንም የሚያየውን ገላ የእኔ ገላ ብሎ እንደሚቀበለው ሁሉ", እንደዚሁም በተመሳሳይ:አሁን ያለውን ገላ የኔ ነው ብሎ ያስባል: ይህም ገላ የተመሰረተው: ከትውልድ በፊት በነበረን ሀይማኖታዊ ወይም ፀረ ሃይማኖታዊ ኑሮ ነው: ያለፈውንም ቢሆን የወደፊቱን ገላ ለማወቅም ያዳግተዋል: ፕራብሁፓዳ (ሽ:ባ: 6.1.49): ያትሃግናስ ታማሳ (ዩክታ) ኡፓስቴ ቭያክታም ኤቫ ና ቬዳ ፑርቫም አፓራም ናስታ ጃንማ ስምርቲስ ታትሃ ይህ የእኛ ስፍራ ነው:: ይህ የእኛ "የሳይንስ እርምጃ" ብለን የምናወራው ነው ከመወለዳችን በፊት: ምን እንደነበርን እንኳን አናውቅም:: ከሞትም በኋላም ምን እንደምንሆን አናውቅም:: ሕይወት የምትቀጥል ናት:: ይህ የመንፈሳዊ ትምህርት ነው:: ሳይንቲስቶች ህይወት እንደምትቀጥል እንኳን አይረዱም:: እንዲያው "በእድል" ይህንን ሕይወት ያገኙ እና ከሞትበኋላ የሚያከትም ይመስላቸዋል:: ከትውልድ በፊት: የአሁን ግዜ: ወይንም የወደፊት ብሎ ነገር የለም እና: አሁን መጨፈር ብቻ ነው: ብለው ያስባሉ:: ይሄ ድንቁርና ይባላል:: "ታማሳ" ሀላፊነት የማይስማው ኑሮ ነው:: እና "አግያ" አግያ ማለት: ዕውቀት የሌለው ስው ማለት ነው:: እና ማነው ዕውቀት የሌለው? "ታማሳ" ማለት ድንቁርና ውስጥ ያሉ ስዎች ማለት ነው:: በአለም ላይ ሶስት አይነት ፍጥረቶች አሉ: "ሳትቫ" "ራጃ" "ታማስ" "ሳትቫ ጉን" ማለት: ሁለ ንጹህ ማለት ነው:: "ፕራካሽ" አሁን እንደምናየው ስማዩ በደመና ተሸፍኗል:: ፀሀይ ግልጽ አደለችም:: ከደመናው በላይ ግን: ፀሀይ በግልፅ አለች:: ሁሉ ነገር ግልፅ ነው:: በደመናው ውስጥ ግን: ሁሉም ግልፅ አይደለም:: እንደዚሁም ሁሉ: የ "ሳትቫ ጉን" ፍጥረት ያላቸው: ለነሱ ሁሉም ነገር ግልፅ ነው:: የ "ታማ ጉን" ፍጥረት ያላቸው ደግሞ: በድንቁርና ውስጥ ናቸው:: ከሁለቱም ደግሞ ሳይሆኑ: የተደባለቁ: ወይ ከ "ሳትቫ ጉን" ወይ "ታማ ጉን" ሳይሆኑ: ማእከለኛዎች: "ራጃ ጉን" ይባላሉ:: ሶስት "ጉናዎች" "ታማስ" ምኞታቸው ሁሉ: ይህንን የያዙትን ገላ መደሰት ብቻ ነው:: ለወደፊት ምን ስለሚመጣ: ምንም ግድ አይሰጣቸውም:: ከትውልድም በፊት ምን እንደነበሩ ምንም እውቀት የላቸውም:: ከዚህ አለም ሌላ እንዳለ ግን በደንብ አድርጎ ተገልጿል:: "ኑናም ፕራማታህ ኩሩቴ ቪካርማ" (ሽ:ባ: 5.5.4) "ፕራማታህ" ልክ እንደ እብድ ሰው:: ለምን እብድ እንደሆነ አያውቅም:: ረስቶታል:: ለሚሰራው ስራ ሁሉ: ከሞት በኋላ ምን እንደሚገጥመው ሁሉ: ምንም አያውቅም:: "እብድ" እና ይሄ ያሁኑ ዘመናችን ስልጣኔ የምንለው: "የእብድ: ስልጣኔ ነው:: ከትውልድ በፊት ስለነበረው ኑሮ ምንም እውቀት የላቸውም:: ከሞት በኋላ ስለአለውም ኑሮ ምንም ግድ አይሰጣቸውም:: "ኑናም ፕራማታህ ኩሩቴ ቪካርማ (ሽ:ባ: 5.5.4) ከትውልድ በፊት ስለነበረው ኑሮ እውቀት ስለሌላቸውም: አሁን ሃጥያት በተሞላ ኑሮ ውስጥ ተሳትፈው ይገኛሉ:: ልክ እንደ ውሻ:: ውሻ ለምን ውሻ እንደሆነ ምንም እውቀት የለውም:: ከሞት በኋላም ምን እንደሚሆን አያውቅም:: ከትውልዱ በፊት: ውሻ: ጠቅላይ ሚኒስቴር ሁኖ ሊሆን ይችላል:: ነገር ግን: ውሻ: ሁኖ ሲወለድ: ምን እንደነበረ ይረሳል:: ይህ "ማያ" የሚባለው የአምላክ ሽፋን ነው:: "ፕራክሴፓትሚካ ሻክቲ: አቫራናትሚካ ሻክቲ" "ማያ" ሁለት አይነት ኅይል አላት:: አንድ ሰው: ከትውልድ በፊት በነበረው የሃጥያት ስራ ምክንያት: ውሻ ሁኖ ቢወለድ: ውሻም ሁኖ ተወልዶ: ከዚህ በፊት ጠቅላይ ሚኒስቴር መሆኑን ቢያስታውስ ይህን እውቀት ይዞ ለመኖር በጣም ያዳግተዋል:: በዚህም ምክንያት: የአምላክ "ማያ" እውቀቱን ትሸፍነዋለች:: "ምርትዩ" ምርትዩ ማለት (ሞት) ሁሉንም ነገር መርሳት ማለት ነው:: ያም "ምርትዩ" (ሞት) ይባላል:: ስለዚህም: ቀንና ሌሊት የማየት ብዙ ልምድ አለን:: ማታ ማታ: በህልማችን የተለየ ቦታ እና የተለየ ህይወት አለን:: በህልም ግዜ ስለ አሁኑ ገላችን ፈጽሞ እንረሳለን:: ለእንቅልፍ መጋደማችንም እንረሳለን:: ገላችን እንደተጋደመ እና ጥሩ አፓርታማ ውስጥ እንዳለን እና ጥሩ የአልጋ ሽፋን እንዳለን እንረሳለን ለምሳሌ በህልሙ መንገድ ላይ ሊራመድ ወይንም ኮረብታ ላይ ሁኖ ሊሆን ይችላል:: በህልሙ የፈለገውን ይዋስዳል: ይዋስዳል:: ሁላችንም: ይህ የህልም ገላ በጣም ይስበናል:: ቀድሞ የነበረንን ገላ እንረሳለን:: እና ይህም ማለት: ድንቁርና ማለት ነው:: "ድንቁርና ማለት ነው" ከዚህ ድንቁርና ደግሞ ከፍ ብለን በእውቀት ከወጣን: ህይዋታችን በለፀገ ማለት ነው:: እራሳችንን በድንቁርና ካስቀረነው: ያም ውድቀት ማለት ነው:: ህይወታችንንም ማበላሸት ማለት ነው:: ይህ የእኛ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ: የሰው ልጅን ከድንቁርና ወደ እውቀት ለማሸጋገር የሚጥር ድርጅት ነው:: የ "ቬዲክም" ስነፅሁፍም አላማ ይኅው ነው:: የሰው ልጅን ለማዳን:: ጌታ ክርሽናም በ "ብሃገቨድ ጊታ" ቅዱስ መፅሃፍ ስለሁሉም ሳይሆን ስለ አገልጋዮቹ ተናግሯል:: "ቴሻም አሃም ሳሙድሃርታ ምርትዩ ሳምሳራ ሳጋራት" (ብ ጊ 12.7) ሌላው: (ብ ጊ 10.11) "ቴሻም ኤቫኑ ካምፓርትሃም አሃም አግናና ጃም ታማሃ: ናሻያሚ አትማ ባሃቫ ስትሆ ግናና ዲፔና ብሃስቫታ:: ክርሽና: በሁሉም ልብ ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል:: ክርሽናን ለማወቅ የሚጥር አገልጋይ: ክርሽና ሁልግዜ ይራዳዋል:: እሱ ይረዳዋል: አጋልጋይ ያልሆኑት ደግሞ: ምንም ግድ አይሰጣቸውም:: ምኞታቸው ሁሉ: እንደ እንስሳ: መብላት: መተኛት: በግብረ ስጋ መገናኘት እና እራሳቸውን መከላከል ብቻ ነው:: ስለ ፈጣሪ ለማዋቅም ሆነ: ወይንም ከፈጣሪ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ለማወቅ: ምንም ግድ አይሰጣቸውም:: እንዲያውም ፈጣሪ የለም ብለው ያስባሉ:: ስለዚህም: ክርሽና: ፈጣሪ እንደሌለ አርገው እንዲያስቡ እና እንዲተኙ: ያደርጋቸዋል:: ስለዚህም "ሳት ሳንጋ" ያስፈልጋል:: ይህ "ሳት ሳንጋ ሳታም ፕራሳንጋት" ከአጋልጋዮች ጋር በመጎዳኘት: ስለ አምላክ ያለንን የመየጠየቅ ጉጉት ለማነቃቃት ያበቃንል:: ስለዚህም የቅርንጫፎቹ መኖር: አስፈላጊ ነው:: ብዙ ቅርንጫፎች የምንከፍተው: አላስፈላጊ ሁኖ እያለ አይደለም:: ቅርንጫፎቹ ለሰው ልጅ ህብረተሰብ: በጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው::