AM/Prabhupada 0004 - ስሜት ለማይሰጥ ነገር ልቦናችሁን አትስጡ፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 10.2-3 -- New York, January 1, 1967

መንገዱም እንዲህ ነው:: ይህም በብሃገቫድ ጊታ ተጠቅሷል:: "ታድ ቪድሂ ፕራኒፓቴና ፓሪስራሽኔና ሴቫያ [ብ ጊ 4 34] የመንፈሳዊውን ሳይንስ ለመረዳት ከፈለጋችሁ: ይህንን መመሪያ መከተል አለባችሁ:: ይህስ ምንድን ነው? "ታድ ቪድሂ ፕራኒፓቴና" ለአምላክ ሙሉ ልቦናችሁን መስጠት አለባችሁ:: ልክ እንደ "ናማንታ ኤቫ" ትሁት ካልሆናችሁ: ሙሉ ልቦናችሁን መስጠት ያዳግታችኋል:: ሙሉ ልቦናስ የሚሰጠውስ ለማን ነው? "ፕራኒፓታ" ያንንስ ሰው የት ነው የምታገኙት? ልቦናችንንስ የምንሰጠው ለየትኛው ሰው ነው? የት ልቦናችንንም እንደምንሰጥም ለማወቅ ትንሽ ሙከራ ማድረግ ይኖርብናል:: ያንን ያህልም የምርምር እውቀት እንዲኖረን ያስፈልጋል:: ለማንም ልቦና መስጠት አግባቢ አይደለም:: ይህንንስ እውቀት እና: አግባቢ ያልሆነውን እንዴት አርገን መለየት እንችላለን? ይህም በቅዱስ መፅሀፎች በደንብ ተገልጿል:: ይህም "በካትሃ ኡፓኒሻድ" በደንብ ተገልጿል:: ታድ ቪድሂ ፕራኒፓቴና ፓሪ [ብ ጊ 4 34] ካትሃ ኡፓኒሻድ እንዲህ ይላል:: "ታድ ቪግናናርትሃም ሳ ጉሩም ኤቫብሂጋቼት ሽሮትርያም ብራህማ ኒሸትሃም [ም ኡ 1 2 12] ይህ "ሽሮትሪያም" ማለት "ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ማለት ነው:: እና ይህ "ሲወርድ ሲዋረድ" ስለመምጣቱ ማረጋገጫው ምንድን ነው? "ብራህማ ኒሽትሃም" ብራህማ ኒሽትሃም ማለትም: ስለ መንፈሳዊው የበላይ እውነት ሙሉ በሙሉ እምነት ያለው ማለት ነው:: ስለዚህም ለአምላክ ሙሉ ልባችንን መስጠት አለብን:: "ፕራኒፓታ" ፕራኒፓታ ማለት: ፕራክርስታ ሩፔና ኒፓታም: "ያለ ምንም ጥርጣሬ" እንዲህ አይነት ሰው ከተገኘም: ሙሉ ልብን ለማገልገል መስጠት ይቻላል:: "ፕራኒፓታ" ይህንንም ሰው ለማገልገል ሞክሩ: ለማስደሰትም ሞክሩ: ጥያቄም ጠይቁት:: ሁሉም ነገር ግልጽ ሊሆንላችሁም ይቻላልና:: ይህንን የመሰለ ባለስልጣናዊ ሰው ማግኘት ያስፈልጋል:: ከዚያም ሙሉ ልቦናን ሰጥቶ ማገልገል ያስፈልጋል:: ሙሉ ልቦናንም ሰጥቶ ማገልገል: አማላክን ማገልገል እንደማለት ነው: ይህም እርሱ የአማላክ ተወካይ ስለሆነ ነውና:: ይሁንም እና: ጥያቄ መጠየቅ ትችላላችሁ:: ይህም ግዜ ለማባከን ሳይሆን: ዕውቀትን ለማግኘት በምሻት ነው:: ይህም "ፓሪፕራሽና" ይባላል:: ይሄ ነው መንገዱ:: ሁሉም ነገር በዚሁ ይገኛል:: ያለን ግዳጅ መሞከሩን ብቻ ነው:: ነገር ግን ይህንን መንገድ ሳንከተል: ግዜያችን በመጠጥ እና በስካር ብናሳልፍ: እንዲሁም በማይረባ ክርክር እና አለ አግባብ ባልሆነ ኑሮ: ግዜያችንን ብናባክን: አምላክን ልንረዳ አንችልም:: አምላክን ለመረዳት በፍጹም ያዳግተናል:: ምክንያቱም: አምላክ: መንፈሳዊ መላእክት እና ታላላቅ ቀሳውስቶች እንኳን በቀላሉ ሊረዱት አይችሉም:: ታድያ የኛ ትንሽ ጥረት ከምን ይቆጠራል? እና ይህ ነው መንገዱ:: ይህንንም ከተከተላችሁ: "አሳሙድሃህ አሳሙድሃህ" ይህንንም መመሪያ ከተከተላችሁ: ቀስ በቀስ: እና በእርግጠኝነት: "አሳሙድሃህ" እንዲሁም ያለምንም ጥርጣሬ: "ፕረትያክሻ ቫጋማም ድሃርምያም" በዚህም መንገድ ከተከተላችሁ: በደንብ ልትረዱ ትችላላችሁ:: "አሁን ልረዳ በቃሁ" ለማለትም ትበቃላችሁ:: ይህም ማለት በእውርነት ውስጥ ናችሁ ማለት አይደለም:: ወይንም እንደ እውር በመከተል ላይ ናችሁ ማለት አይደለም:: መመሪያዏቹን ብትከተሉ: በደንብ ለመረዳት ትበቃላችሁ:: ጥሩ ምግብ ስትበሉ: ሀይል እንደምታገኙ ሁሉ እና ረሃብንም እንደሚያስታግስ ሁሉ: ማንንም ሰው መጠየቅ አስፈላጊ አይደለም:: እራሳችሁ ልትረዱት ትችላላችሁ:: እንደዚሁም ሁሉ: መንገዱን ከተከተላችሁ እና: መመሪያውን ከተከተላችሁ:ሁሉን መረዳት ትችላላችሁ:: "እየተረዳሁት ነው" ለማለትም ያበቃችኋል:: "ፕራትያክሻ" በዘጠነኛው ምእራፍ እንዲህ ብሏል:: "ፕራትያክሻ ቫጋማም ድሃርምያም ሱሱክሃም" ይህም በጣም ቀላል ነው:: ይህንንም በደስታ የምታደርጉት ነው:: እና የዚህም መንገዱ ምንድን ነው? የአለን መንገድም: የሃሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም መዘመር እና የክርሽናን የተቀደሰ ምግብ መብላት ነው:: የብሃገቫድ ጊታንም ቅዱስ መጽሃፍ ማንበብ እና ጌታን የሚያወድስ መዝሙር ማዳመጥ ያስፈልጋል:: ይህ አስችጋሪ ነውን? ይህ አስችጋሪ ነውን? አስቸጋሪ አይደለም:: እንዲሁም የህን መንገድ በመከተል: "አሳሙድሃ" መሆን ትችላላችሁ:: በዚህም መንገድ ማንም ሊያታልልላችሁ አይችልም:: ለመታለል ከፈለጋuችሁ ግን: ብዙ አታላዮች ሞልተዋል:: ስለዚህም የአታላዮች እና የተታላዮች: ህብረተሰብ አትፍጠሩ:: ልክ: በቬዲክ ሲስተም እንደተደነገገው እና: በጌታ ክርሽና እንደታዘዘው: የፓራምፓራውን ሲስተም ተከተሉ:: (ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ትእዛዝ) ስልጣን ካላቸው መንፈሳውያን ትምህርቱን ተማሩ:: ትምህርቱንም በህይወታችሁ ላይ ዶግሙ:: ከዚያም "አሳሙድሃህ ሳ ማርትዬሹ" "ማርትየሹ" ማለትም "ማርትያ" ማለት "ሟቾች" ማለት ነው:: እነዚህስ ሟቾች ማን ናቸው? በዚህ ሕዋ ውስጥ: ገነት ከሚገኘው ከትልቁ "ብራህማ" ጀምሮ" እስከ ትንሿ ምድራዊ ጉንዳን ድረስ" ሁላችንም "ሟቾች" ነን:: "ማርትያ" ማለት: ሁላችንም የምንሞትበት ግዜ አለ:: ስለዚህም: "ማርቴሹ" የመንፈሳዊ መንገድ የሚከተል ግን: ከማቾች ሁሉ: በጣም አወቂ ሁኖ ይገኛል:: "አሳሙድሃህ ሳማርትዬሹ" ለምን? "ሳርቫ ፓፔይህ ፕራሙችያቴ" ይህም አዋቂነቱ: እራሱን ከሃጥያት ነፃ በማድረጉ ነው:: በዚህ ምድራዊ አለም ላይ: ሁላችንም: በእውቀትም ሆነ ባለማወቅ: ሀጥያት በመስራት ላይ እንገኛለን:: ከሃጥያትም ነፃ መውጣት አለብን:: እንዴት ነው ለመውጣትስ የምንችለው? ይሄም በብሃጋቫድ ጊታ ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ: በደንብ ተገልጿል:: ያጅናርትሃት ካርማኖ ንያትራ ሎኮ ያም ካርማ ባንድሃናሀ [ብ ጊ 3 9] ለጌታ ክርሽና ብቻ የምታገለግሉ ከሆነ: "ያግና" ማለት "ቪሽኑ" ወይንም "ክርሽና" ማለት ነው:: በሙሉ ልቦና ክርሽናን የምታገለግሉ ከሆነ: ከሃጥያት ሁሉ ነፃ ትሆናላችሁ:: "ሹብሃ ሹብሃ ፕሃሌ" በረከት ወይንም በረከት የሌለው ነገር እናደርግ ይሆናል:: ነገር ግን በሙሉ ልቦና ጌታ ክርሽናን የሚያገለግል ሰው: ስለ በረከት ወይንም በረከት ስለሌለው ነገር: ጭኝቅ የለውም:: ምክንያቱም እርሱ: ከጌታ ክርሽና የበረከት አምላክ ጋር በጣም የቀረበ ስለሆነ ነው:: ስለዚህም "ሳርቫ ፓፔህ ፕራሙችያቴ" ከማንኛቸውም ሃጥያት ሁሉ ነፃ ሁኖ ይኖራል:: ይህ ነው መንገዱ:: ይህንንም መንገድ በደንብ ከተከተልን: ከዚህ አለም አልፈን ሂደን ከጌታ ክርሽና ጋር መሆን እንችላለን:: ሕይዋታችንም የተሳካ ይሆናል:: መንገዱም በጣም ቀላል ነው:: ሁላችንም መከተል እንችላለን:: በጣም አመሰግናለሁ::