AM/Prabhupada 0005 - ስለ ፕራብሁፓድ ሕይወት በሶስት ደቂቃ ውስጥ፡፡



Interview -- September 24, 1968, Seattle

ቃለ መጠይቅ: ስለ እራስዎ የህይወት ታሪክ በአጭሩ ሊነግሩን ይችላሉ? የት ትምህርትዎን እንደተማሩ እና እንዴት የጌታ ክርሸና አገልጋይ ለመሆን እንደበቁ: ቢነግሩን:: ፕራብሁፓዳ: ትውልዴ እና ትምህርት ያጠናቀቅሁት በካልካታ ውስጥ ነው:: ካልካታ ቤቴ እና ያደግሁበት ቦታ ነው:: የተወለድሁትም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1896 ነው:: ከአባቴም በጣም ቀርቤ ያደግሁ ልጅ ነበርሁ:: ትምህርትም የጀመርሁት ትንሸ ረፈድ ካለ በኋላ ነበር:: በከፍተኛ ደረጃ ትምህርትቤትም ለ8 አመት ያህል ተማርኩ:: በፕራይመሪ ትምህርት ቤት ለ4 አመት: እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ 8 አመት ተማርኩ:: በኮሌጅ ውስጥ ደግሞ ለ4 አመት ተማርኩ:: ከዚያም በኋላ በአገ"የገራችን በነበረው "የጋንዲ" እንቅስቃሴ ውስጥ ገብቼ መሳተፍ ጀመርኩ:: ይሁን እንጂ በጥሩ አጋጣሚ ከመንፈሳዊ አስተማሪዬ ጋራ በ1922 ለመገናኘት በቃሁ:: ከዚያን ግዜ በኋላም በዚህ መስመር ለመከተል የፀና ስሜት አደረብኝ:: ቀስ በቀስ ከቤተሰብ ኑሮዬ ገለል ብዬ: ወደ እዚህ ለማተኮር በቃሁ:: ትዳር የያዝኩትም በ1918 የ3 ኛ አመት የኮሌጅ ተማሪ እያለሁ ነበር:: በዚን ግዜም ልጆች ለመያዝ በቃን:: ያን ግዜም ንግድ ጀምሬ ነበር:: በ 1954 ከትዳር እና ከቤተሰብ ኑሮዬ ገለል ብዬ ወደ መንፈሳዊ አለም ማተኮር ጀመርኩ:: ለ 4 አመት ያህልም ለብቻዬ ያለ ቤተሰቤ: ወደ እዚህ በማተኮር ኑሬአለሁ:: በ 1959 የመሎክሴ ኑሮም ለመኖር: በቤተ መቅደስ ውስጥ: ሥነ ሥርአቱን አጠናቀቅሁ:: ከዚያም ቅዱስ መጽሀፎችን ለመፃፍ ትኩረት አደረግሁ:: በመጀመሪያም የታተመው መፅሀፍም በ 1961 ነበር:: በዚያን ግዜም 3 መፅሀፍቶች ለማሳተም በቃሁ:: ከዚያም በ 1965 ለእናንተ አገር (በእንግሊዘኛ) ለማሳተም በቃሁ:: እዚህ (አሜሪካ) የገባሁትም በ1965 ነው:: ከዚያም በኋላም: የክርሸናን ንቃት ለማስተማር: በአሜሪካ: በካናዳ: እና በአውሮፓ ውስጥ: ለመዞር በቃሁ:: በዚህም መንገድ: ቅርንጫፎቻችን: ለመዳበር በቁ:: የተማሪዎቻችንም ቁጥርም እየጨመረ መጣ:: ወደፊትም ምን እንደሚከናወን ለማየት ያብቃን:: ቃለ መጠይቅ: እርስዎስ አገልጋይ ለመሆን እንዴት ለመሆን በቁ? አገልጋይ ከመሆንዎስ በፊት ምን ነበሩ: ምንስ ይከተሉ ነበር? ፕራብሁፓዳ: የምከተለውም እንደገለጽኩት የእምነት ኑሮ ነበር:: አንዱ የቅርብ ጓደኛዬም: ወደ መንፈሳዊ አስተማሪዬ: ለማስተዋወቅ: ጎትቶ ወስዶኝ ነበር:: ከመንፈሳዊ አስተማሪዬም ጋራም ለመጀመሪያ ግዜ ስተዋወቅ: በጣም እንድሳብ ለማድረግ አበቃኝ:: ከዚያም ግዜ ጀምሮ: የመንፈሳዊው ዘር መዳበር ጀመረ::