AM/Prabhupada 0011 - ክርሽናን በሀሳብ ለማምለክ ይቻላል፡፡



Lecture on BG 4.28 -- Bombay, April 17, 1974

በ "ብሃክቲ ራሳ አምርታ ሲንዱ" አንድ ታሪክ አለ:: ታሪክ ብቻ ሳይሆንም የእውነት ታሪክ ነው:: እንዲህም ተገልፆ ነበር:: አንድ በጣም ትጉህ: የአምላክ አገልጋይ ብራህመና (ቄስ) ነበረ:: በቤተመቅደስ ውስጥም በጣም ጥሩ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ፈለገ:: ነገር ግን ገንዘብ አልነበረውም:: አንድ ቀንም በ "ብሃገቨድ ጊታ" የቅዱስ መጽሃፍ የትምህርት ሰበካ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ ነበር:: በዚህም ትምህርት ላይም እንዳለ: ጌታ ክርሸናን በአእምሮም ለማምለክ እና ለማገልገል እንደሚቻል ተረዳ:: ይህንንም ለረጅም ግዜ ያስብ ስለነበረ: ይህን እድል ለመጠቀም አሰበ:: ጌታ ክርሽናንም በከፍተኛ እና በውድ መንገድ ለማገልገል ተመኘ: ነገር ግን ገንዘብ አለነበረውም:: ጌታ ክርሽናም በአእምሮ እንደሚመለክም ሲሰማ: በቅዱስ ጎዳቨሪ ወንዝ ውስጥ ተጠምቆ: በዛፍ ስር ቁጭ አለ:: ከዚህም ቦታ ሁኖ: በአእምሮው: ውስጥ: በጣም የሚያምር እና ውድ የሆነ "ሲምሃሳና" ዙፋን መገንባት ጀመረ:: ይህንንም ዙፋን በወርቅ እና ጌጣ ጌጥ አሸብርቆ: እና የጌታ ክርሽናን ምስል አስቀምጦ: በአእምሮው የጌታ ክርሽናን ገላ ማጠብ ጀመረ:: የሚጠቀውም ውሃ ከተቀደሱት ወንዞች: ከጋንጀስ: ከጀሙና: ከጎዳቨሪ: ከካቬሪ: በመውሰድ ነበረ:: ከዚያም የጌታ ክርሽናን ገላ በጥሩ ሁኔታ ማልበስ እና በአበባ የተሰሩ ጋርላንዶችን ማቅረብ ጀመረ:: ከዚያም ለጌታ ክርሽና: በጣም ጥሩ የሆነ ምግብ: ማዘጋጀት ጀመረ:: የፓራማና የተባለውን የጣፋጭ ሩዝም ማዘጋጀት ጀመረ:: ይህንንም ጣፋጭ ሩዝ ትኩስ ስለመሆኑ መቅመስ ፈለገ:: መቅመስም የፈለገው: ፓራማና ጣፋጭ ሩዝ: በቀዝቃዛ እንጂ: ትኩስ ሆኖ ስለማይቀርብ ነው:: ለሙከራም ጣቱን ሲነክርበት: ጣቱ ወዲያው ተቃጠለ:: በዚህን ግዜ የአእምሮው ሜዲቴሽን ተደናቀፈ: ምንም ነገር በአጠገቡም እንደሌለ ተረዳ:: ይህን ሁሉ ያደርግ የነበረው በአእምሮው ነበረ:: ነገር ግን: ጣቱ ተቃጥሎ በማግኘቱ በጣም ተደነቀ:: በዚህም ምክንያት: ጌታ ናራያና ከቫይኩንታ: ሁኖ መሳቅ ጀመረ:: ላክሽሚ: (ባለቤቱ) ለምን ትስቃለህም ብላ ጠየቀችው:: አንዱ የእኔ አጋልጋይ እንዲህ አድርጎ በፍቅር አገለገለኝ ብሎም አጫወታት:: ለእርሱ አገልጋዮችም ወደ ቫይኩንታ ይዘውት እንዲመጡም ትእዛዝ ሰጠ:: እንዲሁም ሁሉ "የብሃክቲ ዮጋ" (የጌታ ፍቅር አገልግሎት) በጣም ደስ የሚል ነው:: ጌታን በብዙ ሃብት ለማገልገል አቅም ባይኖረንም: በአእምሮአችን እንኳን አምላክን በፍቅር ማገልገል እንችላለን::