AM/Prabhupada 0014 - የአምላክ ትሁት አገልጋዮች በክብር የገነኑ ናቸው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


The Nectar of Devotion -- Calcutta, January 30, 1973

ለድቮቲዎች (አገልጋዮች) ክርሽና በእጃቸው መዳፍ ውስጥ ነው:: "አጂታ ጂቶ ፒ አሶ" ክርሽና በማንም ለመሽነፍ ባይችለም: በፈቃዱ ግን: በአገልጋዮቹ ይሸነፋል: ይህ ነው የሱ ፈቃድ: ልክ በፈቃዱ በእናቱ በያሾዳ እንደተሽነፈም ሁሉ: በፈቃዱም በራድሃራኒ እና በጓደኞቹም ይሸነፋል: አንድ ግዜ በጨዋታም ክርሽና ተሸንፎም: ጓደኛውን በተክሻው ተሽክሟል: አንዳንድ ግዜም ንጉስ ቀልደኛ ሰው አጠገቡ ያስቀምጣል: ይህም ቀልደኛ ሰው:ንጉሱን ይቀልድበታል:ንጉሱም በዚህ ቀልድ ደሰታል: ቀልደኛውም አንድ አንድ ግዜ በቤንጋል ውስጥ አንድ ”ጎፓላ ቦን“ ይባል የነበረ ቀልደኛ ነበረ: አንድ ቀንም ንጉሱ እንዲህ ብሎ ጠየቀው: “ጎፓላ” ከአንተና ከአህያ ልዩነታችሁ ምንድን ነው ብሎ ጠየቀው: ቀልደኛውም ወዲያው ከንጉሱ እና ከእርሱ መሃከል ያለውን ርዝመት መለካት ጀመረ: ከዚያም 3 ፊት ይሆናል ጌታዬ ብሎ መለሰለት: ልዩነቱ 3 ፊት ብቻ ነው ይህንንም ሰምተው ሁሉም መሳቅ ጀመሩ:ንጉሱም ይህንን ስድብ ሰምቶ በመሳቅ ተደሰተ: ይህም አንዳንድ ግዜ ያስፈልጋል: ክርሽናም እንዲሁ ነው: ሁሉም በከፍተኛ ደረጃ አማላክን ያወድሳል: ይህም የክርሽና ደረጃ ነው:ታላቁ ጌታ: በቫይኩንታ መንፈሳዊ አለም አማላክን ማወደስ ብቻ ነው የሚታየው: ሌላ ነገር የለም: በቭርንዳቫን ውስጥ ግን: ክርሽና ከአገልጋዮቹ ነቀፌታ ይቀበላል: ሰዎች የቭርንዳቫን ኑሮ እንዴት እንደሆነ አይረዱም: የክርሽና አገልጋዮች በከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ ናቸው: ራድሃራኒ አንዳንድ ግዜ ትእዛዝ ትሰጣለች:“ክርሽና ወደ እዚህ እንዳይመጣ:ክርሽና መግባት አይችልም” ክርሽናም ጎፒዎቹን “እባካችሁ እንድገባ ፍቀዱልኝ” ብሎ ይለምናቸዋል: እነርሱም “ትእዛዝ እንድትገባ አልተሰጠንም እና: መግባት አይፈቀድልህም” ብለው ይከለክሉታል: ክርሽናም ይህን አቀራረባቸውን ይወደዋል: