AM/Prabhupada 0022 - ክርሽና አልተራበም፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on SB 1.8.18 -- Chicago, July 4, 1974

ክርሽና እንዲህ አለ "የእኔ አገልጋዮች በፍቅር" ዮሜ ባሃክትያ ፕራያቻቲ ክርሽና የተራበ አይደለም: ክርሽና ወደ እናንተ የምታቀርቡለትን ሊበላ የሚመጣው ስለራበው አይደለም: አይደለyም: እርሱ የተራበ አይደለም: እርሱ ሙሉ በሙሉ የተሟላ ነው: በመንፈሳዊ አለም ውስጥም: እየተስተናገደ ነው: "ላክሽሚ ሳሃስራ ሻታ ሳምብህራማ ሴቭያማናም" እርሱም በ100 እና በ1000 የሚሆ ኑ የሃብት ማላእክቶች: እየተስተናገደ ነው: ክርሽና በጣም ሩህሩህ ነው: ምክንያቱም ክርሽናን በጣም የምታፈቅሩ ከሆነ: እዚህ ድረስ መጥቶ ያቀረበላችሁትን ሊቀበል ይችላል: "ፓትራም ፑሽፓም" የመጨረሻ የድሃ ደሃ ብንሆን እንኳን : ክርሽና በፍቅርና በአቅማችን የሰበሰብንለትን ይቀበላል: ትንሽ ቅጠላ ቅጠል: ትንሽ ውሃ: ትንሽ አበባ: በፍቅር ያቀረብንለትን: ይቀበለናል: ከየትም አለም ሆነን: የሚቀርብ ነገር አዘጋጅተን ለክርሽና ማቅረብ እንችላለን: "ክርሽና: በድህነቴ: ምንም ጥሩ ተገር እማቀርብለህ የለም: ስለዚህ ይህንን በርኁሩህነትህ ተቅበለኝ" ክርሽናም ይቀበላል: ክርሽናም እንዲህ ብሏል: "ታድ አሃም አሸናሚ" "እበላለሁ" ስለዚህ ዋናው ነገር "ብሃክቲ" ወይንም በፍቅር የቀረበ መሆን አለበት: እዚህም እንዲህ ተብሏል: "አላክስያም" ክርሽና በአይናችን በቀላሉ ሊታየን አይችልም: አማላክ በቀላሉ አይታይም: ነገር ግን በርኅሩኁነቱ: እዚህ አለም ላይ: በአያናቸን እንድናየው መጥቶ ነበር:: አለበለዛ ግን ክርሽና በዚህ ምድር ላይ በቀላሉ አይታየንም: እኛ የክርሽና ወገን እና ቅንጣፊ ነን: የክርሽና ወገንና ቅንጣፊ ሁሉም በምድር ላይ ያሉ ነዋሪ ነፍሶች ሁሉ: እርስ በእርስ ግን አንተያይም: እናንተ እኔን ልታዩ አትችሉም: እኔም እናንተን ለማየት አልችልም: "አይ አያሃለሁ" ልትሉ ትችላላችሁ: ነገር ግን ምንድን ነው የምታዩት? የምታዩትም ገላዬን ነው እንጂ ነፍሴን አይደለም: ታድያ ነፍስ ከገላ ስትወጣ: ለምንድነው አባቴ ሄደ ብለን የምናለቅሰው? አባታችንስ ወዴት ሄደ? እዚያው ተጋድሞስ እያየነው አይደለምን? እና ያያችሁትስ ምንድን ነው? ያያችሁት የአባታችሁን የሞተ ገላ ነው እንጂ አባታችሁን አይደለም:: እንደዚሁም በአጠገባችሁ ያለውን የክርሽናን ወገን (የሰውን ነፍስ) ለማየት ካልቻላችሁ: እንዴትስ ክርሽናን ለማየት ትችላላችሁ? ስለዚህም ሻስትራ እንዲህ ይላል "አታህ ሽሪ ክርሽና ናማዲና ብሃቬድ ግራህያም ኢንድሪያህ" (ቼ ቻ ማድህያ 17 136) እንዚህ አለማዊ አይናችን: ክርሽናን ማየት አይችልም: የክርሽናንም ቅዱስ ስም ለመስማት አንችልም "ናማዲ" “ናማ” ማለት ስም ማለት ነው:“ናማ” ማለት ስም: ፎርም: አይነት እና ያለፉ ታሪኮችን ያጠቃልላል: እነዚህ ነገሮች በዚህ በአለማዊ አይኖቻችን አይተን ልንረዳቸው የምንችል አይደለም: ነገር ግን በመንፈሳዊነት ንጹሕ ከሆኑ: “ሴቮኑኬ ሂ ጂህቫዱ” በፍቅር አጋልግሎታችን የጠሩ አይኖች ከሆኑ ግን: ክርሽናን ሁል ግዜ እና የትም ቦታ ለማየት ትችላላችሁ: ነገር ግን ለተራ ሰው “አላክሻም” በቀላሉ ሊታይ አይችልም: ክርሽና ሁሉም ቦታ አለ: አማላክ ሁሉ ቦታ አለ: “አንዳንታራ ስትሃ ፓራማኑ ቻያንታራ ስትሃም: ሶአላክሻም ሳርቫ ብሁታናም” ክርሽና ከውስጥም ከውጪም ይሁን እንጂ: ክርሽናን ለማየት የሚችል መንፈሳዊ አይን ከሌለ:ክርሽናን ለማየት አንችልም: እንደዚሁም ሁሉ ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበር: የተቋቋመው አይናችሁን ከፍቶ እንዴት ክርሽናን ለማየት ለመቻል እንድትበቁ ነው: እንዲሁም ክርሽናን ለማየት ከበቃችሁ “አናንታ ባሂህ” ህይዋታችሁ የተሳካ ሁኗል ማለት ነው: ስለዚህም ሻስትራ እንዲህ ይላል "አንታር ባሂር" "አንታር ባሂር ያዲ ሃሪስ ታፓሳ ታታህ ኪም ናንታር ባሂር ያዲ ሃሪስ ታፓሳ ታታህ ኪም" ሁሉም ሰው ፍጹም እና እንከን የሌለው መሆን ይፈልጋል: ነገር ግን ሰው እንከን የለሽ ሆነ ለማለት የምንችለው: ክርሽናን ከውስጣችንም ሆነ ከውጪ:የማየት ችሎታ ሲኖረን:እንከን የለሽ ሆንን ማለት ነው: