AM/Prabhupada 0023 - ከመሞታችሁ በፊት በክርሽና ንቃታችሁን አዳብሩ፡፡



Sri Isopanisad Invocation Lecture -- Los Angeles, April 28, 1970

እዚህ እንደዚህ ተጽፏል: "ይህ ህዋ የራሱ ግዜ (እድሜ) አለው: ይህም የተወሰነው በሰማያት ጌታ ሃይል ነው" ህዋእ እራሱ እንደ ግዙፍ ገላ ይቆጠራል: ልክ እንደ ገላችን: ሁሉም ነገር እንደ አካባቢው ይወስነዋል: ዘመናዊው ሳይንስ የሬላቲቪቲ ህግ አለው: አተም ወይንም ትንሽ ጉንዳን እንደ ፍጥረቱ እድሜ አለው: እኛም እንደ ፍጥረታችን የተወሰነ እድሜ አለን:: እንደዚሁም ሁሉ ይህ ህዋእ (ዩኒቨርስ) ለብዙ ሚሊዮን አመት ይኑር እንጂ: ለዘልአለም የሚኖር ዩኒቨርስ አይደለም: ይህም የተረጋገጠ ነው:: በጣም ግዙፍ ስለሆነ ግን ለብዙ ሚሊዮን አመት ለመኖር ይችላል:: ቢሆንም ግን መጨረሻ ይኖረዋል:: ይህ የፍጥረት ህግ ነው:: እንደዚሁም ሁሉ ግዜው ሲደርስ: ይህ ጊዜያዊ አለማችን የሚፈራርስበት ግዜ ይመጣል:: ይህም የሚከናወነው ሙሉ ሃይል በአለው ጌታ ፈጣሪያችን ነው:: የኑሮ የተተመነልን ግዜ ሲያከትም: በገላችን ውስጥ መቆየት አንችልም: ይህንንም ማንም ሊያዘገየው ወይንም ሊያቆመው አይችልም:: ይህም አስተዳደር ሃይል ያለው ነውና: መቆየት እፈልጋለሁ ብሎ መጣር አይቻልም:: እኔ ህንድ አገር እያለሁም: ይህ ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር:: አንድ የምናውቀው በጣም ሀብታም የሆነ ጓደኛችን: ከሞት አፋፍ ላይ ነበር:: ዶክተሩንም እንዲህ ብሎ ጠየቀው: "የአራት አመት እንኳን ህይወት አትሰጠንኝምን?" "አንድ ገና ያልጨረስኩት ፕላን አለኝ" አያችሁን? "አሻ ፓሻ ሳቴይር ባድሃህ" ይህ ሴይጣናዊ አስተሳሰብ ነው:: ሁላችንም እንዲህ እያልን እናስባለን: "ይህን መስራት አለብኝ: ይህን መስራት አለብኝ" ይህ አይቻልም: ዶክተሮቹም ሆኑ አባቶች ወይንም ሳይንቲስቶቹም ቢሆኑ: ማንም ሊያቆመው የማይችለው ነው:: አይሆንም:: አራት አመተ ይቅርና: ግዜው ሲደርስ አራት ደቂቃ እንኳን አይፈቀድም:: ጊዜው እንደደረሰ: ወዲያው መሄድ ብቻ ነው:: ይህ ነው የተፈጥሮ ህግ:: ታድያ ይህ ግዜ ሳይመጣ: ሁላችንም የክርሽናን ንቃት በደንብ መከታተል አለብን:: "ቱርናም ያቴታ" ቱርናም ማለት: በጣም በፍጥነት ማለት ነው:: እንደዚህም ሁሉ በፍጥነት የክርሽናን ንቃት መከታተል አለብን:: "አኑ" ሞት ከመምጣቱ በፊትም ይህንን ስራ እና አገልግሎት በግዜ ማከናወን አለብን:: ይህ አዋቂነት ነው:: አለበለዛ ግን መሸነፍ ነው:: አመሰግናለሁ::