AM/Prabhupada 0028 - ቡድሀ አብዩ አምላክ ነው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on Sri Isopanisad, Mantra 1 -- Los Angeles, May 3, 1970

ጋርጋ ሙኒ (ንባብ): "ቨጂቴርያን (አትክትልት ብቻ የሚበላ ሰው) በመሆንም ብቻ" "ከተፈጥር ህግጋት በላይ መሆን እንችላለን ማሰብ ትክክል አይደለም" አትክልቶችም ህይወት አላቸው:: በተፈጥሮ ህግ: አንዱ ህይወት በሌላው ህይወት ላይ ነው ተመግቦ የሚኖረው:፡ ገና ለገና ቨጅተሪያን ነን ብለን ትእቢት እንዲሰማን አያስፈልግም:: ዋናው ነጥብ አማላክን ለመረዳት ማቻል ነው:: እንስሶች አማላክን የመረዳት ስጦታ የላቸውም: የሰው ልጅ ግን ይህ ስጦታ አለው:: ፕራብሁፓዳ: ይህ ነው ዋናው ነጥብ መረዳት የሚኖርብን:: ቡዲስቶችም ቨጅቴሪያን ሁነው እናገኛቸዋለን:: ከቡዲስቶችም መመሪያ አንፃር ስናየው: አሁን አሁን ሁሉም ነገር እየረከሰ መጥቷል: ነገር ግን ጌታ ቡድሃ ለማስተማር የመጣበት አላማ: እነዚህ ተንኮለኞች እንስሳዎችን መግደል እንዲያቆሙ ነበር:: "አሂምሳ ፓራሞ ድሃርማ" የጌታ ቡድሃ ወደ እዚህ አለም ላይ ስለመምጣት በሽሪማድ ብሃጋቫታም እና በብዙ ቬዲክ መጻህፍቶች ውስጥ ተገልጿል:: "ሹራ ድቪሻም" የመጣበትም አላማ ሰይጣናዊ አቀራረብ ያላቸውን ለማታለል ነው:: "ሰይጣኖች" እነዚህንም ለማታለል ጥሩ መመሪያ ፈጥሮ ነበር:: እንዴትስ ሊያታልላቸው በቃ? ሰይጣኖች ማለት አማላክን ተቃዋሚዎች ማለት ነው:: በአማላክ አያምኑም:: ጌታ ቡድሃም እንዲህ ብሎ አስተማረ: "በእርግጥ አማላክ የለም ነገር ግን እኔ የምላችሁን ተከተሉ" "እሺ ጌታዬ" ብለውም ተቀበሉ:: እራሱ ግን አምላክ ነበረ:: እንዲህ አድርጎም አታለላቸው:: እነዚህም ሰዎች በአማላክ አያምኑም ነበር: ነገር ግን በቡድሃ ያምኑ ነበር: ቡድሃ ደግሞ እራሱ አምላክ ነበር:: "ኬሻቫ ድህርታ ቡድሃ ሻሪራ ጃያ ጃጋድ ኢሻ ሀሬ" ስለዚህ የሰይጣን እና የአማላክ አገልጋይ ልዩነታቸው ይህ ነው:: የክርሽና አገልጋይ እነዚህ ተንኮለኞችን እንዴት ክርሽና ኬሻቫ እንዳታለላቸው ይረዳል: አገልጋይ ይህንን በደንብ ይረዳል: እነዚህ የሰይጣን መንፈስ ያላቸው ደግሞ “ጥሩ መሪ አለን ብለው ያስባሉ” መሪያችንም በአማላክ አያምንም ብለው ያስባሉ: “ሳቅ” አያችሁን? “ሳሞ ሃያ ሱራ ድቪሻም (ሽብ 1 3 24 )የዚህ ትክክለኛ ጥቅስም በሳንስክሪት ቋንቋ ተመዝግቧል: ይህንንም አይታችኋል:እንዲህም ታነባላችሁ:”ሳሞሃያ“ ለማዋከብ ”ሱራ ድቪሻም“ ”ሱራ ድቪሻም“ ማለት የአማላክ አገልጋይ ምቀኞች ማለት ነው: በአማላክ የማያምኑ ሁሉ:ሁልግዜ በአማላክ አገልጋዮች እንደተመቀኙ ነው: ይህም የተፈጥሮ ህግ ነው: ይህም በአባት አይተነዋል:”አባት ለ5 አመት ልጁ ጠላት ሁኖ ነበር“ የልጁ ስህተት ምንድን ነበር?ልጁም የአምላክ አገልጋይ ነበር: ልጁም በጣም ጨዋ ነበር:ፍላጎቱም ሁሉ የአምላክን ስም “ሃሬ ክርሽናን ማንትራ” ለመዘመር ብቻ ነበር: አባቱ ግን የልጁ ሃይለኛ ጠላት ሁኖ ተገኘ:“ልጁንም ግደሉት ብሎ ትእዛዝ ሰጠ” እና አባት እንደዚህ ጠላት ሁኖ የሚገኝ ከሆነ:ሌሎቹስ ሰይጣኖች እንዴት ሁነው ይገኛሉ? እና:የአማላክ አገልጋይ መሆን ስትጀምሩ በአለም ላይ ብዙ ጠላቶች እንደምታፈሩ መረዳት አለባችሁ: ነገር ግን የአማላክ አገልጋዮች ናችሁና ይህን መታገል ሃላፊነታችሁ ነው: ሚሽናችሁም እነሱ እንዲረዱ እና እንዲበለጽጉ ነው: ልክ እንደ ጌታ ኒትያናንዳ: ሲያስተምር ሰይጣኖች ጎድተውት ነበረ: ቢሆንም ግን የጎዱትን ጃጋይ እና ማድሃይ ከሃጥያት ነፃ ሊያወጣቸው በቃ: ይህ ነው መመሪያችን ሊሆን የሚገባው: አንዳንድ ግዜ ማታለል ወይንም መጎዳት ሊያስፈልገን ይችል ይሆናል: ዋናው አላማ ግን እንዴት የሰው ልጅ የክርሽና ንቃቱን ለማዳበር እንደሚችል መጣሩ ነው: ይህ ነው የእኛ ሚሽን ወይንም አላማ: እንደምንም ብለን እነዚህ ተንኮለኞች እንዴት የክርሽናን ንቃት እንደሚከተሉ ለማድረግ ነው ጥረታችን: