AM/Prabhupada 0029 - ቡድሀ ከሀድያንን አታለላቸው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Sri Isopanisad, Mantra 1 -- Los Angeles, May 3, 1970

ጌታ ቡድሃ ሰይጣናሞቹን ሁሉ አታለላቸው: ለምንድን ነው ግን ያታለላቸው?“ሳዳያ ህርዳያ ዳርሺታ ፓሹ ግሃታም” እርሱም በጣም ለሌሎች የሚያዝን ስለነበረ ነው: አምላክ ሁልግዜ ለስነፍጥረቶች ሁሉ ያዝናል:ምክንያቱም ሁሉም ልጆቹ ስለሆኑ ነው: እነዚህም ተንኮለኞች ምንም ገደብ በሌለው መንገድ እንስሶችን በመግደል ላይ ይገኙ ነበር: ለምን ትገላላችሁ ብላችሁ ብትጠይቋቸው ደግሞ ወዲያውኑ በቬዳ ውስጥ ለመግደል ተፈቅዷል ብለው ይመልሳሉ:“ፓሻቮ ቫድሃያ ስርስታ” እንስሳ መግደል በቬዳ ውስጥ በእርግጥ ተጠቅሷል: ነገር ግን አላማው ምንድን ነው? ይህም አላማ የቬዲክን ማንትራ (የፀሎት ቃላቶች) ለመሞከር ነበር: እንስሳው በእሳት ውስጥ ከተቀመጠ በኋላ: በቬዲክ ማንትራ ህይወት እንዲሰጠው ይደረግ ነበር: ይህም ለመስዋእት የሚቀርበው ለዚህ አላማ ነው እንጂ ገድሎ ለመብላት አልነበረም: ስለዚህም በዚህ “ካሊ” በተባለው ዘመናችን ውስጥ: ጌታ ቼይታንያ ይህ እንዳይደረግ ከልክሏል: ምክንያቱም በአሁኑ ግዜ ይህንን የእንስሳን መስዋእት በደንብ አድሮጎ የሚያከናውን ብራህመና አይገኝም: ይህም የቬዲክ ማንትራውን ለመለማመድ ማለት ነው: ያግያ (መስዋእቱን) ከማከናወናቸው በፊት ማንትራው ምን ያህል ሃይል እንዳለ ለማየት ፕላን ያደርጋሉ: ይህም የሚሞከረው እንስሶችን በመሰዋት ነው:ከዚያም ለእንሰሶቹ ህይወት ይሰጥዋቸው ነበር: ህይወትም ከአገኙም በኋላ ቄሶቹ ማንትራው በደንብ እንደሰራላቸው ይረዱ ነበር: ይህም መስዋእት ይህን ማንትራ ለመሞከር ነው እንጂ:እንስሳውን ገድሎ ለመብላት አልነበረም: እነዚህ ተንኮለኞች ግን:እንሰሳ ገድሎ ለመብላት ብለው “በቬዳ ውስጥ እንስሳ መግደል ተፈቅዷል” ብለው ይናገራሉ: ልክ እንደ ካልካታ:ካልካታ ሂዳችሁ ነበር? አንድ ኮሌጅ መንገድ የሚባል ነበረ:አሁን ስሙን ቀርረውታል: አሁን “ቪድሃን ራያ” ሳይሉት አይቀሩም: እዚያም እንስሳ ማረጃ ቦታ ይገኛል: ህንዶቹም ከዚህ እንስሳ ማረጃ ቦታ አይገበዩም: ስጋ ከእስላም ስጋ መሸጯ ቦታ ሂደው አይገዙም: ያም ንጹህ ስለአልሆነ ነው:ብለው ያስባሉ ነገር ግን ያም ይህም ሰገራ ያው ነው ሁለቱም ስጋ እየበሉ የሂንዱ ንጹህ እና የእስላሙ ንጹህ ያልሆነ ብለው ያስባሉ ይህ የጭንቅላታቸው ግምታዊ ሃሳብ ነው: በሃይማኖት ስም ይህ እየተካሄደ ነው: በዚህም ምክንያት:እኔ ሂንዱ: እኔ እስላም: እኔ ክርስቲያን እያሉ ይጣላሉ: ማንም ሰው ሃይማኖትን በትክክል የሚረዳ አይመስልም: እነዚህ ተንኮለኞች ሃይማኖትን ትተዋል: ሀይማኖታቸው ጠፍቷል: የክርሽና ንቃት አማላክን እንዴት እንደምንወድ ያስተምረናል:ይህ ትክክለኛ ሃይማኖት ነው: ይህ ነው ሃይማኖት ማለት: ማንኛውም ሃይማኖት የሂንዱም ሆነ:የእስልምና:ወይንም የክርስትና: የአምላክ ፍቅር እንዲኖረን ማድረግ ከተቻለ:ሃይማኖታችሁን በትክክል ይዛችኋል ማለት ነው: