AM/Prabhupada 0030 - ክርሽና ሁልግዜ በመደሰት ላይ ይገኛል፡፡



Sri Isopanisad, Mantra 2-4 -- Los Angeles, May 6, 1970

አምላክ በመንፈሳዊ አለሙ ውስጥ ተወስኖ ያለ ይሁን እንጂ: ከአእምሮአችን የበለጠ ፍጥነት ያለው ሁኖ ይገኛል: በፍጥነቱ ከማንም በላይ ሁኖ ይገኛል:ትላልቅ ሃይል ያላቸው መላእክቶች እንኳን በቀላሉ ሊቀርቡት አይችሉም: በመንፈሳዊ አለም በአንድ ቦታ ተወስኖ ቢሆንም እንኳን:አየር:ውሃ የሚያቀርቡትን መላእክቶች ሁሉ ይቆጣጠራል: በባህሪው ከሁሉም በላይ እና ፍጹም ሁኖ ይገኛል: ይህም በብራህማ ሰሚታ ውስጥ ተጠቅሷል:“ጎሎካ ኤቫ ኒቫሳቲ አክሂላትማ ብሁታ” ክርሽና በጎሎካ ቭርንዳቨንም ውስጥ ይሁን እንጂ:ምንም የሚሰራው ነገር የለም: ከሚጎዳኛቸው ጋር ሁልግዜ ግዜውን በደስታ እያሳለፈ ነው: ይህም ከጎፒዎቹ ጋራ:ከእረኛ ጓደኞቹ ጋር:ከእናቱ ጋር:ከአባቱ ጋር ማለት ነው: እርሱም ሙሉ ለሙሉ ነጻ ነው:ከእርሱ ጋር ያሉትም ጓደኞቹ ደግሞ ከእርሱ በላይ ነጻ ናቸው: ይህም የሚሆንበት ምክንያት:የክርሽና ጓደኞች ለአደጋ ሲጋለጡ:ክርሽና እነሱን ለማዳን ጭንቅ ውስጥ ይገባል: ጓደኞቹ ግን ምንም ጭንቅ የላቸውም: “ክርሽና ስለአለ ምንም ችግር አይኖረንም” ብለው ያስባሉ: አያችሁት? ጓደኞቹ ምንም ጭንቀት የላቸውም: አንድ ነገር ሊከሰትባቸው ይችላል:የክርሽና መጽሃፍን ስታነቡ ብዙ አደጋዎች ተከስተው እንደነበረ ትረዳላችሁ: እረኛ ልጆቹ እና ክርሽና በቀን በቀን ላሞቹን እና ጥጃዎቹን ይዘው ወደ ጫካ ይሄዱ ነበር: በጫካው ውስጥ እና በያሙና ወንዝ ዳርም ይጫወቱ ነበር: ካምሳ ደግሞ እነርሱን ለመግደል የተለያዩ ሰይጣናሞች ይልክ ነበር: እና ይህን አይታችኋል:ስእሎችም አይታችኋል: እና ጓደኞቹ በክርሽና ብዙ እምነት ስለአላቸው: ዝም ብለው ይደሰቱ ነበር: ይህ መንፈሳዊ ኑሮ ነው:“አቫሽያ ራክሲቤ ክርሽና ቪሽቫሻ ፓላና” ይህም ጥልቅ የሆነ እምነት:“በምንም አደጋ ላይ ክርሽና ሁልግዜ ያድነኛል” ብሎ ማሰብ ለአምላክ መማረክ ነው ማለት ነው: ስድስት አይነትም የመማረክ አይነቶች አሉ: በመጀመሪያ ደረጃ:ለመንፈሳዊ አገልግሎት የሚያቀና ወይንም የሚያመቸውን ነገር ሁሉ መቀበል አለብን: ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንቅፋት የሚሆነውን ነገር ሁሉ ደግሞ ማስወገድ አለብን: ቀጥሎ ደግሞ:መንፈሳዊ ከሆኑ ሰዎች ጋር ሁሉ መቅረብ እና መጎዳንኘት ያስፈልጋል: ክርሽና:ብዙ ጓደኞች አሉት: በመንፈሳዊ አለምም ወደ ፊት ስትራመዱ:ከክርሽና ጋር ያላችሁን ግኑኝነት በደንብ ልትረዱ ትችላላችሁ: ከዚያም እራሳችሁን ከዚያ መንፈሳዊ ጓደኝነት ማስተዋወቅ አለባችሁ: ከዚያም የሚቀጥለው ደግሞ:ክርሽና ከችግር ይጠብቀኛል ብሎ ሙሉ በሙሉ መተማመን ነው: ነገር ግን እርሱ ሁሉም ከመከራ እየጠበቀ ነው:ይህም የተረጋገጠ ነው: ነገር ግን በማያ ውስጥ ሁነን:እኛ እራሳችንን እንደምንጠብቅ እና እራሳችንን እንደምንመግብ አድርገን እናምናለን:(አምላክ ሳይሆን) አይደለም: ይህ ትክክል አይደለም: