AM/Prabhupada 0033 - የመሀ ፕራብሁ ስም ፓቲታ ፓቫና ነው፡፡

Revision as of 06:06, 29 November 2017 by Sahadeva (talk | contribs) (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Morning Walk -- October 4, 1975, Mauritius

ፑስታ ክርሽና: “የአሁን ግዜ መንግስታት:በጣም አሰቀያሚ የሆኑትን ሃጥያታዊ ድርጊቶች እየደገፉ ይገኛሉ” እንዲህም እያለ:እንዴት ሰፊውን ህዝብ መለወጥ ይቻላል? ፕራብሁፓዳ: ታድያ መንግስት ትክክለኛ ናቸው ነው የምትለው? ፑስታ ክርሽና: አይደለም ፕራብሁፓዳ:እና? መወገድ አለባቸዋ! መንግስት በአሁን ግዜ ሁሉም ተንኮለኞች ናቸው: የተመረጡትም በተንኮለኞች ሁኖ:እራሳቸውም ተንኮለኞች ናቸው: ይህ ነው ችግሩ: በየሄድንበት ተንኮለኞችን እናገኛለን: “ማንዳ” ትንተናውም ተሰጥቷል: ማንዳ:በእኛ ካምፕ ውስጥም ብዙ ተንኮለኞች አሉ: ሪፖርቱን ማየት ትችላላችሁ:ተሻሽለው መጡ ቢባል እንኳን ተንኮላቸውን አያቆሙም: የተንኮል ፀባያቸውን ለማቆም አይችሉም: ስለዚህም በአጠቃላይ ተነግሯል:“ማንዳ” “ሁሉም መጥፎ” ልዩነቱ ግን በእኛ ካምፕ ውስጥ ተንኮለኞቹ እየተለወጡ ነው:ውጪ ያሉት ግን ምንም ለውጥ:የላቸውም በእኛ ካምፕ ውስጥ ተንኮለኞቹ ይለወጣሉ ብለን እናስባለን:ውጪ ግን ተስፋ የለም:ይህ ነው ልዩነቱ: ከዚህ ሌላ ሁሉም መጥፎ ሁኖ ይገኛል: ምንም ሳታለያይ እንዲህ ማለት ትችላለህ “ማንዳ ሱማንዳ ማታዮ” (ሽ ብ 1 1 10) ታድያ መንግስት እንዴት ጥሩ ሊሆን ይችላል? እነሱም በመጥፎ ደረጃ ናቸው: የጌታ ማሃብራብሁ ስም:“ፓቲታ ፓቫና” ነው:እርሱም ነፃነት የሚሰጠው ለመጥፎ ሰዎችም ጭምር ነው: በዚህ ካሊ ዩጋ በሚባለው ዘመን ውስጥ:ምንም ጥሩ ሰው አይገኝም:ሁሉም በመጥፎ ደረጃ ነው: እነዚህንም በጥሩ ደረጃ ያልሆኑ ሰዎችን ለመቋቋም፡ በጣም ጠናካራ መሆን ይገባችኋል፡፡