AM/Prabhupada 0044 - አገልግሎት ማለት የጌታውን ትእዛዝ በትክክል ተከተሉ ማለት ነው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 4.1 -- Montreal, August 24, 1968

ይህም ማለት:አጋልጋዩ:ክርሽናን የሚያሳየውን መንገድ እየተከተለ ማለት ነው:ይኅው ነው: አገልጋይ:ክርሽና እንደ እኔ ጠላት እንኳን ሁን ቢለው:በፍቅር ለማገልገል ሲል:ቅር አይለውም: ዋናው የፍቅር አገልግሎት ማለት የክርሽናን መመሪያ መከተል ነው: ክርሽና ”ጠላቴ ሁን“ ቢለኝ:ጠላቱ እሆናለሁ:ይህ በፍቅር የሚደረግ ትእዛዝን መከተል ነው: ይህም ክርሽናን ለማስደሰት የሚደረግ ነው:(ትእዛዝን በማክበር) ልክ አንዳንድ ግዜ:አለቃው አገልጋዩን ”እዚህ ጋ ምታኝ“ ሊለው ይችላል: እርሱም እዛው ጋ ቢመታው:ቃሉን አክብሮ አገለገለው ማለት ነው: ሌሎች ይህን ያዩ ግን:”ወይ ጉድ:አለቃውን እየመታው የሚያገለግል ይመስለዋል:ይህ ምን ጉድ ነው?“ ብለው ሊያስቡ ይችላሉ: ነገር ግን አለቃው እንዲመታው አዞታል: ይህም ማገልገል ነው: ማገልገል ማለት የአለቃውን ትእዛዝ ተከትሎ መፈፀም ማለት ነው: ምንም አይነት ስራ ቢሆንም: በጌታ ቼይታንያም ህይወት ላይ:አንድ ጥሩ ያየነው ምሳሌ አለ:ይህም ስለ አገልጋዩ ጎቪንዳ ስለሚባለው ነው: ጌታ ቼይታንያ ምሳውን ከጨረሰም በኃላም:ጎቪንዳ ምሳውን ይበላ ነበር: አንድ ቀንም:ጌታ ቼይታንያ ምሳውን ከበላ በኋላ:በበሩ መግቢያው ላይ ሸለብ እንዲለው ጋደም አለ: ምንድን ነው የሚባለው? በር? መግቢያ? ጎቪንዳም በላዩ ላይ ተራምዶ ገባ: ይህም ከምሳ በኋላ: ሁልግዜ ጎቪንዳ ማሳጅ ስለሚያደርገው ነው: ስለዚህም ጎቪንዳ: ተኝቶ የነበረውን ጌታ ቼታንያን በላዩ ተራምዶ:ማሳጅ ለድረግ ክፍሉ ውስጥ ገባ: ጌታ ቼታንያም ተኝቶ ነበር እና ከግማሽ ሰአት በኋላ ነቃ: ከእንቅልፍም ሲነሳ:ጎቪንዳ ክፍሉ ውስጥ ተቀምጦ አየው:እንዲህም አለው:”ጎቪንዳ እስከ አሁን ፕራሳዳም (ምሳ)አልበላህምን?“ እርሱም አልበላሁም አለ:ጌታ ቼይታንያም ለምን ብሎ ጠየቀው:እርሱም እንዲህ መለሰ:”አንተ ጋደም ብለህ ስለሆነ:መሻገር ጠልቼ ነው“ አለው: ”ታድያ እንዴት አድርገ ገባህ?“ ብሎም ጠየቀው:እርሱም ”ተሻግሬ ገባሁ“ ብሎ መለሰ: ”ታድያ ተሻግረህ እንደገባኅው ለምን ተሻግረህ አትወጣም ነበረ?“ ብሎ ጠየቀው: እርሱም እንዲህ አለ:“መጀመሪያ የተሻገርኩት አንተን ለማለልገል ነበር:አሁን ግን ለግል ጥቅሜ ምሳ ለመብላት:አንተን ተሻግሬ ለመሄድ አልችልም” ብሎ መለሰለት: ይህንንም ማድረግ አይገባኝም:ይህም ለአንተ ሳይሆን ለእኔ ጥቅም ስለሆነ ነው: እንደዚህም ሁሉ ለክርሽና ደስታ ብላችሁ:ጠላቱም:ጓደኛውም:ወይንም የተፈለገውን መሆን ትችላላችሁ: ይህም “ብሃክቲ ዮጋ” ይባላል: ምክንያቱም አላማችሁ ክርሽናን ለማስደሰት ብቻ ስለሆነ ነው: ልክ የእራሳችሁን ስሜቶች ማገልገል ስትጀምሩ ደግሞ:ወደ አለማዊ ኑሮ ወዲያውኑ ተመለሳችሁ ማለት ነው: “ክርሽና ባሂርሙክሃ ሃና ብሆጋ ቫንቻ ካሬ ኒካታ ስትሃ ማያ ታሬ ጃፓቲያ ድሃሬ (ፕሬማ ቪቫርታ) ክርሽናን ረስተን:የግላችንን ስሜቶች ለማስደሰት ስንጀምር:ይህ ”ማያ“ ይባላል: ይህንንም የራሳችንን ሰሜት ለማስደሰት የምንጥረውን መንገድ አቁመን: ሁሉንም ነገር ለክርሽና ስናደርግ ደግሞ: ይህም ነፃነት ይባላል: