AM/Prabhupada 0046 - እንደ እንስሳ አትሁኑ፡፡ ይህንንም ተቋቋሙት፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Morning Walk -- May 28, 1974, Rome

ዮጌሽቫራም:“ብሃገቫን ከመሄዱ በፊት:ጥያቄዎች ትቶልኝ ሂዶ ነበር : ከነዚህ ጥያቄዎች ልጠይቅህን?” ፕራብሁፓዳም “አዎን” አለ: ዮጌሽቫራ:“አሁን በቅርብ ግዜ ቶሎ ቶሎ የምናየው ችግር:የሽብርተኞች ቁጥር እየጨመረ መገኘቱ ነው” እነዚህም ሽብርተኞች በብዛት በፖሎቲካ አቅዋማቸው የተገፋፉ ናቸው: ፕራብሁፓዳ: “አዎን: ከዚህም በፊትም መሰረታዊ መመሪያውን እንዳስረዳሁት:ይህ የሚሆነው እንደ እንስሳ ስለሆኑ ነው:” አንዳንድ ግዜም ልክ እንደ ጨካኝ እንስሳዎች ስለሚሆኑ ነው: በአለም ላይ የተለያዩ እንስሳዎች አሉ: ነብር እና አንበሳ:ጨካኝ እንስሳዎች ናቸው: ቢሆንም የምንኖረው በእንስሳ ህብረተሰብ ነው: በእንስሳ ህብረተሰብም እየኖርን: አንዱ እንስሳ በጣም ጨካኝ ሁኖ ቢገኝ:ይህ የሚያስገርም ሊሆን አይችልም: ይህም በእንስሳ ህብረተሰብ ውስጥም ስለምንኖር ነው: ስለዚህም እንከን የሌለው የሰው ልጅ መሆን አለብን: ይህ ብቻ ነው መፍትሄው: እኛ ይህ የእንስሳ ህብረተሰብ ነው ብለን በይፋ ተናግረናል:አንድ ጨካኝ እንስሳ ከህብረተሰቡ ቢወጣም: ይህ ሊያስገርመን አይገባም:የወጣበትም ህብረተሰብ የእንሰሳ ህብረተሰብ ስለሆነ ነው: ነብርም ወጣ ወይንም ዝሆንም ወጣ:ሁሉም እንስሳዎች ናቸው: ነገር ግን እናንተ እንደ እንስሳ እንዳትሆኑ:ይህንን መቃረን አለባችሁ: ይህ አስፈላጊ ነው: የሰው ልጅ አስተዋይ እና ብልሃተኛ እንስሳ ነው: ይህ አስተዋይ እና ብልሃተኛነት ያስፈልጋል: ነገር ግን:እናንተም ለየት ያለ እንስሳ ብትሆኑ:ይህ ሊረዳችሁ አይችልም: መሆን ያለባችሁም ትክክለኛ:አስተዋይ እና ብልህ የሰው ልጅ መሆን ነው: ነገር ግን:እንዲህ ተብሏል:“ዱርላባም ማኑሻም ጃንማ ታድ አፒ አድህሩቫም አርትሃዳም” እነዚህ ሰዎች ለህይወታቸው አላማ የሌላቸው ናቸው:የሰው ልጅ የህይወቱ አላማ ምን እንደሆነ እውቀቱ የላቸውም: የእንስሳነት አዝማሚያቸውም ወደየ አይነቱ እያዘነበለ ነው:ወደ እዚህ እና ወደ እዛ: ልክ ሂደው ራቁትዋን የሆነች የሴት ልጅ ዳንስ እንደሚያዩት: ይህ የእንስሳ ጠባይ ነው:ሚስቱን በቀን በቀን ራቁቷን ያያታል: ይህም አልፎ ተርፎ ግን:ሌላ ሴትን ገንዘቡን ከፍሎ: ራቁቷን ለማየት ይሄዳል: ምክንያቱም በሌላ መንፈሳዊ አገልግሎት ስለአልተሰማሩ:በዚሁ የእንስሳ ኑሮ አይነት ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ: አይደለምን? እና ሌላ ሴት ራቁቷን ሂዶ ለማየት ጥቅሙ ምንድን ነው? የራስህን ሚስት በቀን በቀን እና ማታ ማታ ራቁትዋን እያየሃት ነው: ታድያ ለምን? ምክንያቱም ሌላ የተሻለ ስራ ላይ ስለአልተሰማራህ ነው: እንስሶች:“ፑናህ ፑናስ ቻርቪታ ቻርቫናናም” (ሽብ 7 5 30) ውሻ የአጥንትን ጣእም አያውቀውም: ዝም ብሎ ግን: አጥንቱን በዚህም በዚያም እየጋጠ ይገኛል: ምክንያቱም እንስሳ ስለሆነ ነው:ሌላ ስራ የለውም: እንደዚሁም ይህ ህብረተሰባችን:እንደ እንስሳ ነው:በተለይ ምእራባውያን: የፈጠሩትም ህብረተሰብ:በእንስሳ አስተሳሰብ ዝንባሌ የተመሰረተ ነው: ይህም ማለት “እኔ ይህ ገላ ነኝ:ህይወቴን በደንብ የምጠቀምባት:ስሜቶቼን ሁሉ ሙሉ በሙሉ በማስደሰት ነው” ይህም የእንስሳ አስተሳሰብ ነው:“እኔ ይህ ገላ ነኝ” ገላ ማለት ስሜቶቻችን ማለት ነው: እንዲህም ያስባሉ: “ከፍተኛ የህይወታችን መሳካት ማለት:ስሜቶቻችንን ማስደሰት ነው” ብለው ይኖራሉ: ይህ ነው የእነርሱ ስልጣኔ: ስለዚህ እናንተ:ትክክለኛውን የሰው ልጅ ስልጣኔን ማስተዋወቅ አለባችሁ: በተለያዩ የእንስሳዎች አቀራረብ:አትገረሙ: ይህም በተለያየ ሃይል ይወጣል: ዞሮ ዞሮ ግን:ሁሉም እንሰሳ ነው: መሰረታዊ ደረጃው እንስሳነት ነው: ምክንያቱም “እኔ ይህ ገላ ነኝ” ብሎ ስለሚያስብ ነው: ልክ ውሻም እንደሚያስበው “እኔ ውሻ ነኝ:የዳበርኩ እና ጠንካራ ውሻ ነኝ” ሌላም ሰው እንደዚሁ ያስባል “እኔ የትልቅ አገር ሰው ነኝ” ነገር ግን ዋና የዚህ መሰረቱ ምንድን ነው? ውሻም ማንነቱን የሚያስበው ከውሻ አንጻር ነው: ይህም ትልቅ ህብረተሰብ:የሚያስበው ከገላው ምቾት አንጻር ነው: ስለዚህም ከዚህ ውሻ እና ከዚህ ትልቅ ህብረተሰብ ልዩነት የለም: ያለውም ልዩነት ቢኖር:የሰው ልጅ በተፈጥሮ አማካኝነት የተሻለ ስሜቶች አሉት: ነገር ግን ለመጠቀሙ ጥሩ ሃይል የለውም:እንዚህንም ስሜቶች በአግባቡ ለመጠቀም እውቀቱ እና ትምህርቱም የለውም: ይህም የሚያስፈልገው እውቀት:እንዴት በመንፈሳዊ ኑሮ ለመዳበር እንደሚቻል እና:እንዴት ከዚህ አለማዊ ኑሮ ለመውጣት እንደሚቻል ነው: ስለዚህም ምንም የተገለፀለት ነገር የለም: ያለውንም አእምሮ እንስሳዊ ለሆነ ኑሮ እየተጠቀመበት ይገኛል: ይህ ነው ትርጉሙ: ጥሩውንም አእምሮው እንዴት መጠቀም እንዳለበት ትምህርቱ የለውም: ስለዚህም እውቀቱን ለእንስሳዊ ኑሮ በመጠቀም ላይ ይገኛል: በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ ደግሞ:ምእራባውያንን ሲያዩ “እነዚህ በጣም የሰለጠኑ ናቸው” ብለው ያስባሉ: ይህ ምንድን አይነት ስልጣኔ ነው?በእንስሳነት መበልፀግ? መሰረታዊ ኑሮአቸው:ግን እንስሳዊ መሆኑን አይረዱም:ስለዚህም ተገርመው ያዩዋቸዋል: እነርሱንም መምሰል ይፈልጋሉ:ይህንንም የእንስሳዊ ኑሮ ያሰፋፉታል:የእንስሳ የስልጣኔ አለምም እንዲሁ ይቀጥላል: ታድያም እኛ ይህንን አይነት ኑሮ ተቃውመን ማስተካከል አለብን:ይህም የሚጠቅመው የሰውን ልጅ ስልጣኔ ለማስፋፋት ይሆናል: