AM/Prabhupada 0048 - የአርያን ስልጣኔ፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 2.2-6 -- Ahmedabad, December 11, 1972

“አናርያ ጁስታም” “የህይወትን ብልጽግና ለተረዳ ሰው:ይህ ተገቢ አይደለም” ኤርያን:ኤርያን ማለት:የበለጸገ ማለት ነው: ስለዚህም:የአርጁና በጦርነቱ ላይ አልዋጋም ማለቱ:የአርያን ያልሆነ ባህርይ ነው: በብሃጋቨድ ጊታ እንደተገለጸው:እና እንደ ኤርያኖች ስልጣኔ ከሆነ: 4 የህብረተ ሰብ ክፍሎች: በፈጣሪ በከፍተኛው አምላክ: ተከፋፍለዋል: ከዚህም ቀደም ብሎ እንደተገለጸው:“ድሃርማም ቱ ሳክሳድ ብሃጋቫት ፕራኒታም” (ሽብ 6 3 19) ማንኛውም የሃይማኖት መንገድ ልንረዳ የምንችለው:“በፈጣሪ ሲሰጥ ነው” የሰው ልጅ:ሃይማኖትን ሊፈጥር አይችልም: ይህም የኤርያን ሲስተም:የበለጸገ ሲስተም: “ቻቱር ቫርንያም ማያ ስርስታም ጉና ካርማ ቪብሃጋሻሃ” ነው:(ብጊ4 13) ክርችናም እንዲህ አለ:“ይህም የህብረተሰብ በእኔ የተከፋፈለው:የህብረተሰቡ አመራር በደንብ እንዲስተዳደር ነው” ብራህማ: ክሻትርያ:ቫይሻ:ሹድራ: አርጁናም ከሻትርያ ቤተሰብ የመጣ ነበር: ስለዚህም በጦር ሜዳ ላይ እያለ:ለመዋጋት ጥርጣሬ ስለአደረበት:ይህ የአርያን ባህርይ ነው ማለት አንችለም: የክቡር ሰራዊት ለመዋጋት ካላዘነበለ:ይህ ተገቢ ሁኖ አይታይም: ክሻትርያዎች: በጦር ሜዳ ላይ ሲዋጉ: ሰው ከገደሉ:ይህም እንደ ሃጥያት አይቆጠርም: እንደዚህም ሁሉ:ብራህመናም እንስሳ ለመስዋእት ሲያቀርብ:(በጥንት ግዜ እንስሶች ለመስዋእት ይቀርቡ ነበር) እንዚህም ብራህመናዎች በመስዋእቱ ግዜ ሃጥያት ገቡ ማለት አይደለም: የእንስሳም መስዋእት እንስሳዎቹን ለመብላት ተብሎ አልነበረም: ይህም የቬዲክ ማንትራውን ለመሞከር ተብሎ ነበር: በመስዋእት ሴረሞኒ የሚሳተፉትን ብራህመናዎችንም ለመሞከር: እንዚህም ብራህመናዎች የሚዘምሩት የቬዳ ማንትራ በትክክል መሆኑንም ለመሞከር ነበር: ይህም የሚሞከረው አንድ እንስሳን መስዋእት በማድረግ እና ለእንስሳውም ህይወት እና አዲስ የወጣት ህይወት ለመስጠት ነበር: ይህ ነበር የእንስሳዎች መስዋእት:አንዳንድ ግዜም ፈረስ:አንዳንዴም ላሞች ይቀርቡ ነበር: ነገር ግን በአሁኑ የካሊ ዩጋ ዘመን ይህ የተከለከለ ነው: ምክንያቱም በደንብ የሰለጠኑ ”ያጅኒካ ብራህማናዎች“ አይገኙም: ሁሉም የተለያዩ አይነት መስዋእቶች ሁሉ ተከልክለዋል: “አሸቫሜድሃም ጋቫላምብሃም ሳንያሳም ፓላ ፓይትርካም ዴቫሬና ሱቶትፓቲም ካላዉ ፓንቻ ቪቫርጃዬት” (ቼቻ አዲ 17 164) አሽቫሜድሃ መስዋእት:ጎሜድሃ መስዋእት:ሳንያሳ እና ልጅ በዴቫራ ለማግኘት መሞከር: ማለትም የባል ታናሽ ወንድም:እነዚህ ሁሉ በዚህ ዘመን ተከልክለዋል: