AM/Prabhupada 0049 - ሁላችንም በተፈጥሮ ህግጋት ተጠምደን እንገኛለን፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Arrival Talk -- Aligarh, October 9, 1976

ይህ ሳንኪርታን በጣም ሞገስ ያለው ነው: ይህም የጌታ ቼይታንያ ምርቃት ነው: “ፓራም ቪጃያቴ ሽሪ ክርሽና ሳንኪርታናም” ይህ ነው የእርሱ ምርቃት:ይህም ሳንኪርታንን በዚህ ዘመን ስለፈጠረልን ነው: ይህም በቬዲክ መፃህፍቶች የተረጋገጠ ነው:ይህም በቬዳንታ ሱትራ ነው: “ሻብዳድ አናቭርቲ” አናቭርቲ:ነፃነት: የአሁኑ ደረጃችን:በዚህ አለም ላይ መወተብን ነው: በተፈጥሮ ህግጋት ታስረናል: በሞኝነታችን ነፃ ወተናል ብለን እናውጅ ይሆናል:ያም ሞኝነታችን ነው: ነገር ግን:በተፈጥሮ ህግጋት: ታስረን እንገኛለን: “ፕራክርቴ ክሪያማናኒ ጉኔይህ ካርማኒ ሳርቫሻሃ አሃንካራ ቪሙድሃትማ ካትታሃም” (ብጊ3 27) በተፈጥሮ ህግጋት ታስረን እንገኛለን: ነገር ግን እነዛ ሞኝ የሆኑት:“ቪሙድሃትማ” በስህተተኛ ክብር: እነዚህ ሰዎች ነፃ የወጡ ይመስላቸዋል:ይህም ትክክል አይደለም: ይህም በትክክል ስለማይረዱ ነው: ይህም አላዋቂነት መቀየር አለበት : ይህ ነው የኑሮአችን አላማ: ስለዚህም ሽሪ ቼይታንያ ማሃፕራብሁ:የሃሬ ክርሽናን ማሃ ማንትራ እንድንዘምር ትእዛዝ ሰጥቶናል: የመጀመሪያውም ጥቅም "ቼቶ ዳርፓና ማርጃናም (ቼቻ አንትያ 20 12) ምክንያቱም አላዋቂነት የተመሰረተው በልባችን ነው: ልባችን የጠራ ከሆነ:ሃሳባችንም የጠራ ይሆናል:እንደዚህም አላዋቂነት ሊኖር አይችልም: አእምሮአችን እና ሃሳባችንም ንጹህ መሆን አለበት: ይህም የሃሬ ክርሽና መዘመር የመጀመሪያው ውጤት ነው: “ኪርታናድ ኤቫ ክርሽናስያ ሙክታ ሳንጋ ፓራም ቭራጄት (ሽብ 12 3 51) የክርሽናን ስም በመዘመር:ክርሽናስያ:የቅዱስ ክርሽና ስም:ሃሬ ክርሽና: ሃሬ ክርሽና: ሃሬ ራማ:ይህ ሁሉ አንድ ነው:በራማ እና ክርሽና ስም ልዩነት የለም: ራማዲ ሙርቲሹ ካላ ኒያሜና ቲስትሃን (ብሰ 5 39) ይህም ይስፈልጋል:የአሁኑ ደረጃ አላዋቂነት ነው: ይህም ”እኔ የአለማዊ ፍጥረት ውጤት ነኝ“ ብሎ ማሰብ ”እኔ ይህ ገላ ነኝ“ ብሎ ማሰብ:ነው: እንደዚሁም ሁሉ:”እኔ አሜሪካዊ ነኝ" "እኔ ብራህመና ነኝ“ ”እኔ ሻትርያ ነኝ“ ቡሎ ማሰብ: ብዙ የተለያዩ ሹመቶች ወይንም ውክልናዎች ይኖሩናል:ነገር ግን እኛ አንዱም አደለንም: ይህ አላዋቂነት መጽዳት አለበት:”ቼቶ ዳርፓና“ እንዲህም ብለን ስንረዳ ”እኔ ህንድ አይደለሁም“ ”እኔ አሜሪካዊ አይደለሁም“ ”ብራህማና አይደለሁም“ ”ሻትርያ አይደለሁም“ ብለን ስንረዳ ”እኔ ይህ ገላ አይደለሁም“ ብለን ተረዳን ማለት ነው: በዚህም ግዜ አእምሮአችን ”አሃም ብራህማስሚ“ ይሆናል: ”ብራህማ ብሁታ ፕራሳናትማ ና ሾቻቲ ና ካንክሳቲ“ (ብጊ 18 54) ይህም ይፈለጋል: ይህም የህይወታችን መሳካት ይሆናል: