AM/Prabhupada 0056 - በሻስትራ የቬዳ ሥነፅሁፎች ውስጥ አስራ ሁለት መንፈሳዊ ባለሥልጣኖች ተገልፀዋል፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on SB 7.6.1 -- Madras, January 2, 1976

”ሽሪ ፕራህላዳ ኡቫቻ:ኮማራ አቻሬት ፕራግኖ ዳሃርማን ባሃጋቫታት ኢሃ“® ”ዱርላብሃም ማኑሻም ጃንማ ታድ አፒ አድህሩቫም አርትሃዳም (ሽብ 7 6 1) ይህ ፕራላድ ማሃራጃ ነው: እርሱም ለክርሽና ንቃት: አንዱ በጣም ትልቅ የሆነ: ባለ ሥልጣን ነው: በሻስትራ ቅዱስ ማጻህፍት ውስጥ: 12 አይነት ባለስልጣኖች ይገኛሉ: “ሽቫያምቡሃ ናራዳህ ሻምቡህ ኩማራሃ ካፒሎ ማኑህ” “ፕራህላዶ ጃናኮ ብሂሽሞ ባሊር ቫያሳኪር ቫያም” (ሽብ 6 3 20) እነዚህም በያመራጅ የተሰጠው:የድሃርማ (ሃይማኖት) ባለስልጣኖች ናቸው: ድሃርማ ማለት “ብሃጋቫድ ድሃርማ” ትላንትና እንደገለጽኩት ሁሉ:ድሃርማ ማለት ብሃጋቫታ ማለት ነው: “ድሃርማም ቱ ሳክሳድ ብሃገቫት ፕራኒታም” (ሽብ 6 3 19) ለምሳሌ ዋነኛው ዳኛ:ህግን ተከትሎ: ፍርዱን እንደሚሰጥ ሁሉ: እንደዚሁም:የመንግስት ህግጋት:በአንድ ሰው ወይንም በነጋዴ የሚደነገጉ አይደሉም: ህግ የሚደነገገው በመንግስት ብቻ ነው: ማንም ሰው ህግ መደንገግ አይችልም: በከፍተኛ ፍርድ ቤትም:አንድ ሰው ለዳኛው:እኔ የራሴ ህግ አለኝ ቢለውም:ዳኛው ሊቀበለው አይችልም: እንደዚሁም ሁሉ ድሃርማ (ሃይማኖት) እራሳችሁ ልትፈጥሩት አትችሉም: ትልቅ ሰው ብትሆኑ እንኳን: የፍትህ ሁሉ ዋና መሪ እንኳን ብትሆኑ:ህግ እራሳችሁ መደንገግ አትችሉም:ህግ የሚደነገገው በመንግስት ብቻ ነው: እንደዚሁም ሁሉ ድሃርማ (ሃይማኖት)ማለት“ብሃጋቫታ ድሃርማ” ወይንም በፈጣሪ የተደነገገ ማለት ነው: ሌሎችም ድሃርማ የሚሏቸው:ድሃርማ ሊሆኑ አይችሉም:ተቀባይነትም የላቸውም: በቤታችን የተደነገገ ህግ ሁሉ በመንግስት ተቀባይነት የለውም: ስለዚህ እንዲህ ተብሏል:“ድሃርማ ቱ ሳድሻድ ብሃጋቫት ፕራኒታም” (ሽብ6 3 19) እና ይህ “ብሃገቫት ፕራኒታም ድሃርማ” ምንድን ነው? ይህም በብሃገቨድ ጊታ ተገልጿል:እንደምናውቀውም: ክርሽና የመጣበትም አላማ:“ድሃርማ ሳምስትሃ ፓናርትሃያ” የሃይማኖትን መመሪያዎች ለማቋቋም እና:እንደገና ለማስተዋወቅ ነበር: “ድሃርማስያ ግላኒር ብሃቨቲ ብሃራታ” “ያዳ ያዳ ሂ ድሃርማስያ ግላኒር ብሃቨቲ ብሃረታ” (ብጊ4 7) አንዳንድ ግዜ በምድር ላይ “ግላኒ” ይኖራል:ይህም ሃይማኖትን ሲከተሉ እንከን ያለባቸው መንገዶችን ሲይዙ ነው: ያንንም ግዜ ክርሽና እዚህ ምድር ላይ ይመጣል:“ፓሪትራናያ ሳድሁናም ቪናሻያ ቻ ዱስክርታም” (ብጊ4 8) “ዩጌ ዩጌ ሳምብሃቫሚ” ክርሽና ሃሰታዊ የሆኑትን ድሃርማዎች ከፍ ለማድረግ አለመጣም: ሂንዱ ድሃርማ:ሙስሊም ድሃርማ:ክርስቲያን ድሃርማ:ቡድሃ ድሃርማ:አይደለም: በሽሪማድ ብሃገቨታም እንደተጠቀሰውም ሁሉ:“ድሃርማ ፕሮጂሂታ ካይታቮ” (ሽብ 1 1 2) ድሃርማ (ሃይማኖት)የማታለል ፈለግ ያለው ከሆነ: እንደዚህ የማታለል ባህርይ ያለው ድሃርማ “ፕሮጂታ” ይባላል: “ፕራክርስታ ሩፔና ኡጂታ” ማለትም ይህ መጣል አለበት ወይንም ማስወገድ አለብን: ትክክለኛ ድሃርማ:“ብሃጋቫድ ድሃርማ” ነው: ትክክለኛ ድሃርማ: ስለዚህም ፕራላድ ማሃራጃ እንዲህ አለ:“ኮማራ አቻሬት ፕራግኖ ድሃርማን ብሃጋቫታን ኢሃ” (ሽብ 7 6 1) ድሃርማ ማለት:አምላክ እና የእኛም ከአምላክ ጋር ያለን ግኑኝነት ማለት ነው: እንደዚሁም ሁሉ: በዚያ ግኑኝነት መቀጠል እና: የህይዋታችንን አላማ ማሳካት ማለት ነው: ይን ድሃርማ ይባላል: