AM/Prabhupada 0060 - ሕይወት ከቁሳዊ ነገር ሊመጣ አይችልም፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Room Conversation with Svarupa Damodara -- February 28, 1975, Atlanta

ፕራብሁፓዳ: ”ሁላችንም እንደምናውቀው: ህይወት በሲመን ውስጥ ከአለ“ ”ሲመንም በሴት ልጅ ማህፀን ውስጥ ሲገባ:የልጅ ገላ ማደግ ይጀምራል“ መጀመሪያው ግን:ህይወት ነው:ይህ ተግባራዊ እውቀት ነው: ይህ ህይወት:የፈጣሪ የታላቁ ህይወት:ቅንጣፊ አካል ነው ስለዚህም መጀመሪያው:ፈጣሪ አምላክ ነው:”ጃንማዲ አስያ ያታሃ (ሽብ 1 1 1 )“አትሃትሆ ብራህማ ጂግናሳ” ስለዚህ ይህንንም ፍጹም እውቀት በዚህ በተሳሳተ አለም ላይ:እንደገና መመስረት እና ማስተማር አለብን: ከዚህስ አልፎ ለምንድን ነው ከንጥረ ነገር ህይወት መፍጠር የማይችሉት? የገለፃቸውም ጥቅም ምንድን ነው?”ህይወት መፍጠር አልቻልንም“ ከንጥረ ነገር ህይወት መምጣቱስ መረጃው የታለ? ”ስሩ እና አሳዩን“ ስቫሩፕ ዳሞዳር:”መረጃው በምርምር ላይ ነው“ ፕራብሁፓድ:”ምን? ያ ትርኪ ምርኪ አስተሳሰብ ነው:የማይረባ አስተሳሰብ ነው“ ህይወት ግን ከህይወት ስለመምጣቱ:ብዙ መረጃ አለ: የሰው ልጅ:ዛፎች: ሁሉም ህይወት ከህይወት ነው የሚመጣው: እስከአሁን ድረስ:የሰው ልጅ ከድንጋይ መወለዱን ያየ የለም: ማንም አላየም:አንዳንድ ግዜ እንዲህ ይባላል “ቭርሺካ ታንዱላ ንያያ” ይህን ታውቃላችሁ? “ቭርሺካ ታንዱላ ንያያ” “ቭርሺካ” ማለት ጊንጥ “ታንዱላ” ማለት ደግሞ ሩዝ ማለት ነው: አንዳንድ ግዜ የተከመረ ሩዝ ውስጥ:ጊንጥ ሲወጣ እናያለን: ይህም ማለት ሩዝ ጊንጥን ወለደች ማለት አይደለም: እዚህ አገር አላያችሁት ይሆናል: እኛ አገር ግን አይተናቸዋል: ከተከመረውም ሩዝ:አንድ ትንሽ ጊንጥ ስትወጣ ትታያለች: የዚህም እውነተኛው ሂደት:የጊንጥዋ እናት: በሩዙ ውስጥ እንቁላልዋን ጥላ:ከግዜም በኋላ በሩዙ ውስጥ:ጊንጥዋ ተፈልፍላ ትወጣለች: እንደዚህ ነው እንጂ:ጊንጥ ከሩዝ ተፈጥራ አይደለም: ስለዚህም ይህ “ቭርሽካ ታንዱላ ንያያ” ይባላል:ቭርሺካ ማለት ጊንጥ ሲሆን ታንዱላ ማለት ደግሞ ሩዝ ማለት ነው: ስለዚህ “ህይወት ከንጥረ ነገር መጣ” የሚለው ፍልስፍና የ “ቭርሺካ ታንዱላ ንያያ” ፊሎሶፊ ነው: ህይወት ከንጥረ ነገር ሊመጣ አይችልም: ለምሳሌ:ህይወት ካለ:ነፍስ ካለ:ገላው ያድጋል:ይቀያየራል:ያድጋል: ነገር ግን:ህፃኑ ነፍስ ሳይኖረው ከተወለደ ግን:ገላው ሊያድግ አይችልም: ስለዚህ ንጥረ ነገር ገላ ሁኖ ለማደግ የሚችለው ህይወት ካለ ብቻ ነው: