AM/Prabhupada 0061 - ይህ ገላ የቆዳ የአጥንት እና የደም ቃልቻ ነው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Northeastern University Lecture -- Boston, April 30, 1969

ውድ ልጆች እና ልጃገረዶች፤ ወደ እዚህ ስብሰባ ለማዳመጥ አክብራችሁ በመምጣታችሁ አመሰግናችኋለሁ፡፡ እኛም የክርሽና ንቃት የማስፋፋት እንቅስቃሴ ላይ እንገኛለን፡፡ ምክንያቱም ይህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡ ይህም መስፋፋት ለመላው ዓለም ሲሆን ስርዓቱም በጣም ቀላል ነው፡፡ እርባናውም ወይንም ጠቀሜታውም ይኅው ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ይህ መንፈሳዊ እርካብ ወይንም ደረጃ ምን እንደሆነ መረዳት ይገባናል፡፡ በዚህ ቁሳዊው ዓለም ላይ ያለን ኑሮ በተለያየ እርካብ ላይ ይገኛል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በመንፈሳዊ እርካብ ላይ መቆም ይኖርብናል፡፡ ከዚህም በኋላ በመንፈሳዊ ንቃት ተመስጠን ጥልቅ ትኩረት ማድረግ ይገባናል፡፡ በብሀገቨድ ጊታ በሶስተኞው ምእራፍ ላይ እንደተገለፀው፤ የተለያየ ውስን ኑሮ በዚህ ዓለም ላይ ይዘን እንደምንገኝ ተጠቅሶልን ይገኛል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ “ኢንድሪያኒ ፓራኒ አሁር ....” (ብጊ፡ 3.42) በሳንስክሪት ቋንቋ “ኢንድሪያኒ” ተብሏል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ያለን ውስን ህይወታችን በቁሳዊ ገላ አስተሳሰብ የተሞላ ነው፡፡ በዚህ ምድር ላይ የምንገኝ ሁሉ በዚህ ዓይነቱ የቁሳዊ ገላ አስተሳሰብ የተሞላ ህይወት የተወሳሰብን ነን፡፡ እኔ ህንድ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡፡ “እኔ ህንዳዊ ነኝ” አንተ ደግሞ አሜሪካዊ ነኝ ብለህ ታስባለህ፡፡ ሌላው ደግሞ “እኔ የሩስያዊ ነኝ” ብሎ ያስባል፡፡ ሌላውም እንድሁ “እኔ እንደዚህ ነኝ” ብሎ ያስባል፡፡ በዚህም ዓይነት መንገድ ሁሉም ሰው ይህ ቁሳዊው ገላ እኔው ነኝ ብሎ ያስባል፡፡ ይህም አንዱ የምንገኝበት እርካብ ነው፡፡ ይህም ያለንበት ደረጃ የስሜታዊ ደስታ እርካብ ነው፡፡ ምክንያቱም በቁሳዊው ገላ አስተሳሰብ እስከተደናገርን ድረስ፤ ደስታ ማለት ስሜትን ማርካት ብቻ ይመስለናል፡፡ ይኅው ነው፡፡ “ደስታ ማለት ስሜቶቻችንን ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ገላችንን ማርካት ስሜቶቻችንን ማርካት ማለት ነው፡፡” በማለት እናስባለን፡፡ ስለዚህ እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ “ኢንድሪያኒ ፓራኒ አሁር ኤንድሪብህያህ ፓራም ማናሀ” (ብጊ፡ 3.42) አብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና እንደገለፀልንም በዚህ በቁሳዊው ዓለም ኑሮ ውስጥ፤ ወይም በቁሳዊ ገላ አስተሳሰብ በተበከለ አስተሳሰብ ላይ እያለን ዓለማዊ ስሜቶቻችን በጣም የሚገፋፉ እና ሀይል ያላቸው ሆነው ይገኛሉ፡፡ በዚህ በአሁኑ ወቅትም ይህ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ማለትም በአሁኑ ወቅት ብቻ ሳይሆን ይህ ቁሳዊ ዓለም ከተፈጠረበት ግዜ ጀምሮ ነው ማለት ነው፡፡ በሽታችንም ይህ ነው፡፡ “ይህ ቁሳዊ ገላ እኔ ነኝ፡፡” ብሎ ማሰብን ማለት ነው፡፡ ሽሪማድ ብሀገቨታም እንዲህ የሚል ጥቅስ አቅርቦልናል፡፡ “ያስያትማ ቡድሂህ ኩናፔ ትሪ ድሀቱኬ ስቫ ድሂህ ካላትራዲሱ ብሆማ ኢጅያ ድሂህ” (ሽብ፡ 10.84.13) ይህም ማለት “ይህ ቁሳዊ ገላ እኔ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው ሁሉ፤ ማለትም “አትማ ቡድሂህ ኩናፔ ትሪ ድሃቱ” “አትማ ቡድሂ” ማለት ይህ በቆዳ የተሸፈነው አጥንት እና ስጋ እኔ ነኝ ብሎ ማሰብ ማለት ነው፡፡ ይህም ገላ እንደ ቦርሳ ይቆጠራል፡፡ ገላችን በቆዳ የተሸፈነ ደም፣ ሽንት፣ ሰገራ፣ እና ብዙ የተለያዩ ነገሮች የሚገኝበት እና እንደ ቦርሳ የሚቆጠር ነው፡፡ አያችሁን? እኛ ግን በስህተት “እኔ ይህ በቆዳ የተሸፈነ የአጥንት፣ የሰገራ እና የሽንት ቦርሳ ነን ብለን እናስባለን፡፡” ይህም የእኛ ቁንጅና እና ሁለመናችን ነው ብለን በስህተት እናስባለን፡፡ ይህን የመሳሰሉ ብዙ ታሪካዊ ምሳሌዎችንም ለመስጠት ይቻላል፡፡ ቢሆንም ግን ያለን ግዜ በጣም አጭር ነው፡፡ ቢሆንም ግን አንድ አጠር ያለች ምሳሌ ለመስጠት እወዳለሁ፡፡ ይህም ልቡ በቆንጆ ልጃገረድ ፍቅር ሰለተወሰደ ልጅ ነው፡፡ ልጃገረዷ ፈቃደኛ አልነበረችም፡፡ ልጁ ግን ፈጽሞ ሊለቃት አልቻለም፡፡ እንደሚታወቀውም በሕንድ አገር ውስጥ ብዙዎቹ ልጃገረዶች ድንግልነታቸውን በጥብቅ የሚጠባበቁ ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህችም ልጃገረድ ከልጁ ጋር ለመስማማት ፈቃደኛ አልነበረችም፡፡ ከዚያ በኋላ ግን “እሺ እስማማለሁ እና ከአንድ ሳምንት በኋላ እንድትመጣ እጠይቅሀለሁ፡፡” ብላ ነገረችው፡፡ ለዚሁም “በዚህ ሰዓት እና ወደ እዚህ ስፍራ እንድትመጣ፡፡” ብላ አዘዘችው፡፡ በዚህም ልጁ በጣም ደስተኛ ሆነ፡፡ ይህችም ልጃገረድ ለሰባት ቀን ያህል የተቅማጥ መድሀኒት ወሰደች፡፡ በቀን በቀንም ሰገራ እና ትውከት ማከማቸት ጀመረች፡፡ ያከማቸችውንም ሰገራ እና ትውከት በእቃ ውስጥ አስቀመጠችው፡፡ የቀጠሮውም ግዜ እና ሰዓት ሲደርስ ልጁ ቀጠሮውን አክብሮ መጣ፡፡ ልጅቷም በበሩ አጠገብ ተቀምጣ ጠበቀችው፡፡ በዚህም ግዜ ልጁ የሚፈልጋት ልጃገረድ የት እንዳለች ጠየቀ፡፡ እርሷም እኔው ነኝ በማለት መለሰችለት፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፡፡ "ኧረ በፍፁም አንቺ አይደለሽም፡፡ አንቺ በጣም አስጠሊታ ነሽ፡፡ ያች ልጅ ግን በጣም ቆንጆ ናት፡፡ አንቺ ፈፅሞ ልትሆኚ አትችይም“ ብሎ ነገራት፡፡ እርሷም እንዲህ አለችው፡፡ “ተሳስተሀል፡፡ እኔ ትክክለኛዋ ልጅ ነኝ፡፡ ቢሆንም ግን ቁንጅናዬን ከእኔ ለይቼ በእቃ ውስጥ አስቀምቼዋለሁ፡፡“ አለችው፡፡ እርሱም ”ታድያ ይህ እቃ የታለ?" ብሎ ጠየቃት፡፡ እርሷም እንዲህ አለችው፡፡ “የምትፈልገው ቁንጅና ወይንም ያለኝ ሰገራ እና ትውከት በዚህ እቃ ውስጥ ተከማችቶልሀል፡፡ ቁንጅና የምትለው የተገነባውም በእነዚህ ንጥረ ነገሮች ነው፡፡” ማናቸውም ሰው ቢሆን በጣም ጠንካራ እና በጣም ቆንጆ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰገራ ሶስት ወይንም አራት ግዜ ቢወጣ ሁሉም ነገር መቀያየር ይጀምራል፡፡

ስለዚህ በሽሪማድ ብሀገቨታም እንደተገለፀልን፤ ይህ የቁሳዊ ገላ አስተሳሰብ የተሞላበት ሕይወት ምንም የፈካ ሕይወት አይደለም፡፡ ያስያትማ ቡድሂህ ኩናፔ ትሪ ድሃቱኬ (ሽብ፡ 10.84.13)፡፡