AM/Prabhupada 0062 - ክርሽናን ለሀያ አራት ሰዓት ለማየት ሞክሩ፡፡

Revision as of 06:06, 29 November 2017 by Sahadeva (talk | contribs) (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on SB 1.8.18 -- Chicago, July 4, 1974

ፕራብሁፓዳ:”አራድሂቶ ያዲ ሃሪስ ታፓሻ ታታሃ ኪም“ ክርሽናን የማምለክ ደረጃ ከደረስን:አውስተሪቲ እና የንስሃ ቅጣት አያስፈለገንም: ምክንያቱም የእራሳችን መንፈሳዊ ማንነትን እና አምላክን ለማወቅ ብዙ መንገዶች አሉ:አውስተሪቲዎች:የንሰሃ ቅጣት ወዘተ አንዳንድ ግዜ አምላክን ለመፈለግ ወይንም ለማየት ወደ ጫካ እንሄዳለን: የተለያዩም መንገዶች አሉ:ቢሆንም ሻስትራ ቅዱስ መጽሃፎች እንደሚሉን ከሆነ:ክርሽናን ማወደስ ከጀመርን: ”አራድሂቶ ያዲ ሃሪስ ታፓሳ ታታሃ ኪም“ ክርሽናን ማገልገል ከጀመርን:ሌላ አውስተሪቲ እና ንስሃ ማድረግ አያስፈልገንም: ”ናራድሂቶ ናራድሂቶ ያዲ ሃሪስ ታፓሳ ታታህ ኪም“ ዞሮ ዞሮ ብዙ አውስተሪቲ እና ንስሃ ከገባችሁ በኋላ: ክርሽናን ለማወቅ ካልቻላችሁ ጥቅሙስ ምንድን ነው? ጥቅመ ቢስ ነው: ”ናራድሂቶ ያዲ ሃሪስ ታፓሳ ታታሃ ኪም አንታር ባሂር ያዲ ሃሪስ ታፓሳ ታታሃ“ ቢሆንም ግን: ክርሽናን 24 ሰአት ለማየት የምትችሉ ከሆነ:በውስጥም በውጪም: ይህ የ”ታፓስያዎች“ ሁሉ መድረሻ ነው: እዚህም ክርሽና እንዲህ ይላል:ኩንቲም እንዲህ ትላለች: ምንም እንኳን ክርሽና ከውስጥም ከውጪም ቢሆንም: እኛ ክርሽናን በአጠገባችን የሚያይልን አይን የለንም:”አላክሻያም“ ”የማይታይ“ ለምሳሌ ክርሽና በኩሩክሼትራ ጦር ሜዳ ላይ ነበረ: ነገር ግን አምስቱ ፓንዳቫስ:እንዲሁም እናታቸው ኩንቲ እነዚህም ብቻ ናቸው:የክርሽናን ጌትነት እና የሁሉ የበላይ አምላክ መሆኑን የተረዱ የነበሩት: ሌሎቹም አልፎ አልፎ የክርሽናን ማንነት የተረዱ ነበሩ:የተረፉት ግን ክርሽናን እንደ ተራ ሰው አድርገው ያዩት ነበረ: ”አቫጃ“ ”አቫጃናንቲ ማም ሙድሃ ማኑሺም ታኑም አሽሪታም“ ክርሽና ለሰው ልጅ ዘር ትሁት በመሆኑ:በፈቃዱ እዚህ አለም ላይ መጣ: ቢሆንም ግን ብዙዎች:የመንፈሳዊ ዓይን ስለአልነበራቸው:የክርሽናን ማንነት ሊረዱ አልቻሉም: ስለዚህም ኩንቲ "አላክሻያም“ ብላ ተናገረች:ይህም ማለት ከአይን የሚሰወር ማለት ነው: ምንም እንኳን አንተ ”አናንታህ ባሂህ ሳርቫ ብሁታናም“ ብትሆንም ”አንታሃ ባሂህ“ የሆነውም ለአገልጋዮቹ ብቻ ሳይሆን:ለሁሉም ነው: ክርሽና በሁሉም ልብ ውስጥ ሰፍሮ ይገኛል:“ኢሽቫራ ሳርቫ ብሁታናም ህር ዴሼ” ህር ዴሼ:እዚህ በልባችን ውስጥ:ክርሽና ሰፍሮ ይገኛል: ስለዚህም በሜዲቴሽን እና በዮጋ መመሪያዎች:ክርሽና በልባችን ውስጥ መስፈሩንም ልንረዳ እንችላለን: ይህም ሜዲቴሽን ይባላል:የክርሽና ስፍራ ሁልግዜ መንፈሳዊ ነው: እኛም ይህንን የመንፈሳዊ መንገድ ብንከተል:የክርሽናን ንቃት ብንከተል: የስነ ስርአት መመሪያዎችን ብንከተል:ከሃጥያታዊ ተግባርም ብንወገድ:ክርሽናን ማየት እንችላለን: ምክንያቱም በሃጥያታዊ ተግባር ላይ እየተሰማራችሁ:ክርሽናን ለመረዳት አትችሉም: ይህም አይቻልም:“ናማም ዱስክርቲኖ ሙድሃ ፕራፓድያንቴ ናራድሃማሃ” እነዚህ “ዱስክርቲና” የሆኑ ሰዎች:“ክርቲ” ማለት ምስጋና:የሚመሰገን ማለት ነው ነገር ግን “ዱስክርቲ” ሃጥያታዊ ለሆነ ሰው ነው: ስለዚህም እኛ የምንጠይቀው: መጠየቅም ሳይሆን:ይህ የእኛ መመሪያ ነው: አንድ ሰው ከሃጥያታዊ ስራዎች ነፃ መሆን አለበት: አራቱም የሃጥያታዊ ስራ ምሰሰዎች እነዚህ ናቸው:“ማመንዘር:ስጋ መብላት:መስከር እና ቁማር መጫወት” ስለዚህም የእኛ ተማሪዎች ከዚህ እንዲቆጠቡ እና ትእዛዙን እንዲከተሉ ይጠበቅባቸዋል: ምክንያቱም ሃጥያታዊ ሰው:አምላክን ሊረዳ አይችልም: በአንድ በኩል የስነ ስርአት መመሪያችንን እና የመንፈሳዊ ሂደቶችን መከተል አለብን: በሌላ በኩል ደግሞ:ሀጥያት ከሆኑ ነገሮች መቆጠብ አለብን: በዚህም ሁኔታ:ክርሽና ከእኛ ጋር ይሆናል:መናገር እንችላለን እንዲሁም ከእርሱ ጋር እንሆናለን: ክርሽና ሩህሩህ ነው: ልክ እንደ ኵንቲ ከክርሽና ጋር ልክ እንደ ወንድሟ ልጅ አድርጋው ታጫውተው ነበር: እንደዚሁም ሁሉ ከክርሽና ጋር እንደ ልጃችሁ ወይንም እንደ ባለቤት ማነጋገር ከተፈለገ ይቻላል: እንደ ወዳጃችሁ:እንደ ጓደኛችሁ ወይንም እንደ አለቃችሁ: እንደ ምኞታችሁ ክርሽናን መቅረብ ይቻላል: እኔ ይህን የቺካጎ ቤተ መቅደስ በማየቴ በጣም ደስ ብሎኛል: በጣም ጥሩ እያደረጋችሁ ነው:አዳራሹም በጣም ቆንጆ ነው: በእንደዚህም ጥሩ አገልግሎታችሁ ቀጥሉ:ክርሽናንም ለመረዳት ቀጥሉ: በእንደዚህም መንገድ ህይወታችሁ የተሳካ ይሆናል:አመሰግናለሁ: ድቮቲዎች: ጃያ! ሃሪ ቦል!