AM/Prabhupada 0064 - ሲድሂ ማለት የሕይወት መሳካት ማለት ነው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on SB 6.1.15 -- Denver, June 28, 1975

ኬቺት ማለት “አንድ ሰው” ማለት ነው: “አልፎ አልፎ” “አንድ ሰው” ማለቴም “አልፎ አልፎ” “ቫሱዴቫ ፓራያናሃ” መሆን ቀላል ነገር አይደለም: ትላንት እንዳስረዳሁት ሁሉ:ብሃገቫን ክርሽና:እንዲህ ይላል: “ያታታም አፒ ሲድሃናም ካሽቺድ ቬቲ ማም ታትቫታሃ ማኑስያናም ሳሃሽሬሹ ካሽቺድ ያያቲ ሲድሃዬ” ሲድሂ ማለት በአንድ ነገር ፍጹም ችሎታ መያዝ ማለት ነው: ለዚህም “አስታ ሲድሂ” የሚባል ዮጋ የሚለማመዱ ዮጊዎች አሉ: እነዚህም አስታ ሲድሂዎች:“አኒማ:ላግሂማ:ማሂማ:ፕራፕቲ:ሲድሂ:ኢሽትቫ:ቫሺትቫ:ፕራካምያ” ተብለው ይጠራሉ: እነዚህም “ሲድሂ” ዮጋ ሲድሂ ይባላሉ: ዮጋ ሲድሂ ማለት ከትንሹ ነገር ሁሉ ያነሰ መሆን ትችላላችሁ ማለት ነው: የእኛ መጠን ለነገሩ:ትንሽ ነው: በዮጋ ሲድሂ ደግሞ:ምንም እንኳን ይህ መጠነኛ ገላ ቢኖረንም: አንድ ዮጊ መጠኑን በጣም ትንሽ ሊያደር ገው ይችላል: የትም ቦታ ብትሸፍኑት የመውጣት ሃይል ይኖረዋል: ይህ አኒማ ሲድሂ ይባላል: እንደዚህም ሁሉ ማሂማ ሲድሂ እና ላግሂማ ሲድሂ የሚባሉ አሉ: እንደ ጥጥ ክር እራሱን ለማቅለልም ይችላል: አንዳንዶቹ እነዚህ ዮጊዎች:የእራሳቸውን ክብደት በጣም ቀላል ሊያደርጉት ይችላሉ:አሁንም ቢሆን በህንድ አገር ውስጥ እንዲህ አይነት ዮጊዎች ይገኛሉ: በልጅነታችንም ይህንን አይነት ዮጊ አይተናል:እኛም ቤት አባቴን ለማየት ይመጣ ነበር: እንዲህም አለ:“እኔ ወደ ፈለግሁበት ቦታ በሰኮንድ ውስጥ መሄድ እችላለሁ” አለ: አንዳንድ ግዜም በጥዋት ተነስተው:ወደ ጃገናት ፑሪ:ወደ ራሜሽቫራም:ወደ ሃሪድዋር ይሄዳሉ: ገላቸውንም በተለያዪ ቅዱስ ወንዞች እንደ ጋንጀስ እና ሌሎች ወንዞች ውስጥ ሂደው ይጠመቃሉ: ይህም ላግሂማ ሲድሂ ይባላል:ክብደታችሁን በጣም ቀላል ማድረግ ትችላላችሁ ማለት ነው: እንዲህም ይለን ነበር:“አንዳንድ ግዜ ከመንፈሳዊ አባታችን ጋር አንድ ላይ ተቀራርበን ተቀምጠን እያለ“ ”ከተቀመጥንበት ጠፍተን ደግሞ:በሴኮንድ ውስጥ:ሌላ ቦታ እንሄዳለን“ ይህ ላግሂማ ሲድሂ ይባላል: እንዲሁም ብዙ የተለያዩ የዮጋ ችሎታዎች አሉ:ብዙም ሰዎች ይህንን እያዩ በጣም ግር የሚል ደረጃ ላይ ይደርሱ ነበር: ነገር ግን ክርሽና እንዲህ ይላል:”ያታናም አፒ ሲድሃናም (ብጊ7 3) “ከእነዚህ ሁሉ የዮጋ ሲድሂ ችሎታ ያላቸው ሲድሃዎች ” “ያታታም አፒ ሲድሃናም ካሽቺድ ቬቲ ማም ታትቫታሃ” (ብጊ7 3) አንድ ሰው የእነዚህን ሁሉ የዮጋ ሲድሂዎች ችሎታ ሊኖረው ይችላል: ነገር ግን ይህም ሁሉ ችሎታ ተይዞ ክርሽናን ለመረዳት አይቻልም: ይህ የማይቻል ነው: ክርሽናን ለመረዳት የሚቻለው:ፍላጎታቸውን ወደ ክርሽናን ለማገለገል ለወሰኑ ሰዎች ብቻ ነው: ስለዚህም ክርሽና የሚፈልገውን እና የሚያዘውን ሰምተናል:“ሳርቫ ድሃርማም ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሸረናም” (ብጊ18 66) ክርሽና ሊታወቅ የሚችለው በንጹህ አጋልጋዮቹ ነው:በማንም ሌላ ሰው ሊታወቅ አይችልም: