AM/Prabhupada 0079 - ምንም አይነት ክፍያ ለእኔ አያስፈልግም፡፡



Lecture on SB 1.7.6 -- Hyderabad, August 18, 1976

እነዚህ የውጭ አገር ሰዎች:ሂንዱ አይደሉም:ወይንም ህንዳውያን አይደሉም ወይንም ብራህማናዎች አይደሉም: እንዴት ነው ይህንን መንፈሳዊ ንቃት የወሰዱት?ሞኞች እና ተንኮለኞችም አይደሉም: የመጡትም ከተከበረ እና ከተማሩ ቤተሰቦች ነው: አሁን ኢራን ውስጥም ቅርንጫፎች አቋቋቁመናል:በቴህራን ውስጥ:ከዚያ ነው አሁንም የመጣሁት: ከሞሃመዳን ቤተሰቦችም የመጡ ብዙ ተማሪዎች አሉን:እነርሱም እየተከተሉ ነው: አፍሪካዊያንም እየተከተሉ ነው:አውስትራሊያዎችም እየተከተሉ ነው: በአለም ዙርያ ሁሉ:ይህ ነው የጌታ ቼይታንያ ሚሽን: “ፕሪትሂቪቴ አቼ ያታ ናጋራዲ ግራም ሳርቫትራ ፕራቻራ ሃይቤ ሞራ ናም” ይህ ይጌታ ቼይታንያ ትንቢት ነው: በአለም ላይ በሚገኙ:በእያንዳንዱ ከተማ እና መንደር: ይህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ:ይሰራጫል: ስለዚህ ለእኔ ነጥብ የለኝም:ይህ የእኔ ትንሿ መዋጮ እና በትህትና የቀረበች ናት: ስለዚህ አንድ ሰው ይህን የሚያስፈፅም ከሆነ:ለምን ሁላችንም እንዲህ አናደርግም? ቼይታንያ ማሃፕራብሁ:ስልጣን እና ሃይል ለሁሉም ህንዳውያን ሰጥቷል: ብሃረታ ብሁሚቴ ሆይላ ማኑስያ ጃንማ ያራ (ቼቻ አዲ 9.41) እርሱም የተናገረው ለሰው ዘር እንጂ ለድመቶች እና ለውሾች አይደለም: “ማኑሻ ጃንማ ያራ ጃንማ ሳርትሃካ ካሪ” በመጀመሪያ:የህይወታችን አላማ ምን እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል: ይህም እንዲህ ይባላል “ጃንማ ሳርትሃካ:ጃናማ ሳርትሃካ ካሪ ካራ ፓራ ኡፓካራ” ስለዚህ ሁሉም ቦታ ሂዱ: ይህም የክርሽና ንቃት በጣም የሚፈለግበት ደረጃ ላይ ነው ያለው: