AM/Prabhupada 0082 - ክርሽና በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡



Lecture on BG 4.24 -- August 4, 1976, New Mayapur (French farm)

ዲቮቲ:ክርሽና በመንፈሳዊ አለም እና በእያንዳንዱ ህይወት ያለው ፍጡር ልብ ውስጥ ይገኛል ብለናል: ፕራብሁፓዳ:ክርሽና ሁሉም ቦታ ይገኛል:ድቮቲ:እንደ ሰው ወይንስ እንደ ሃይል? ፕራብሁፓዳ:በሃይሉ:በተጨማሪም እንደ ሰው:ነገር ግን በዚህ አለማዊ አይናችን ልናየው አንችልም: ሃይሉ ግን ሊታወቀን ይችላል:ይህንን ነጥብም አስረዳልን: በደንብም ስንረዳ:ይህ ጥቅስ እንደሚለው ሁሉም ነገር ”ብራህማ ሳርቫም ክሃልቭ ኢዳም ብራምማ“ ወደፊት የተራመደ ድቮቲ:ከክርሽና በቀር ሌላ ምንም ነገር አያይም: ድቮቲ:ሽሪላ ፕራብሁፓድ:በአለማዊ ሃይል እና በመንፈሳዊ ሃይል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ፕራብሁፓዳ:አዎን የተለያዩ ልዩነቶች አሉ:ልክ እንደ ኤሌትሪክ ምሳሌ: ብዙ የተለያዩ ነገሮች በአንድ በኤሌክትሪች ሃይል ይሰራሉ: ዲክታፎኑ እንኳን በዚሁ ሃይል ይሰራል: ክርሽናም እንዲህ ይላል:”አሃም ሳርቫስያ ፕራብሃቮ (ብጊ 10.8) ክርሽና የሁሉም ነገር ሁሉ መነሻ ነው: ድቮቲ:በብሃገቨድ ጊታ እንደተገለፀው:አንድ ሰው በህይውቱ ላይ እያለ ገላውን እየቀየረ ነው: ነገር ግን ጥቁር ሰው ነጭ ሲሆን አይታይም:ወይንስ አንድ አንድ የማይቀየሩ ነገሮች አሉ? ገላችን ይቀያየር እንጂ:አንድ የማይቀየር ነገር በገላችን አለ: ይህ ምንድን ነው? ይህ እንዴት እየሆነ ነው?የሰው ልጅ ገላ ይቀያየራል ነገር ግን ከልጅነት ጀምሮ እስከ እርጅና ድረስ ሰዎችን እናውቃለን: ፕራብሁፓዳ: በመንፈሳዊ እውቀት እየዳበርክ ስትመጣ:በጥቁር እና በነጭ ምንም ልዩነት እንደሌለ ለመረዳት ትበቃለህ: ልክ እንደ አበባ:ሲያድግ ብዙ አበባ ይወጣዋል: የሚያፈራውም ከአንድ ስር ነው: እንደዚሁም ምንም ልዩነት የለም:ነገር ግን ቆንጆ ለማድረግ አበባው የተለያዩ ቀለሞች አሉት: ፀሃይ ስታንፀባርቅ 7 ቀለሞች አሏት:ከእነዚህም ቀለሞች: የተለያዩ ቀለሞች ይወጣሉ:መነሻው አንድ ነጭ ከለር ሁኖ የተለያዩ ቀለሞች ይወጣሉ: ይህ ግልፅ ነውን? ድቮቲ:ሽሪላ ፕራብሁፓዳ ክርሽና ሁሉን ነገር ከፈጠረ እና ሁሉም ነገር የክርሽናን ምኞት ለሟሟላት ከቀረበ: ጥሩ እና መጥፎ በምድር ላይ አለ ለማለት እንችላለን? ፕርብሁፓዳ:ጥሩ እና መጥፎ ብሎ የለም:ይህ የአእምሮአችን ግምት ነው: ነገር ግን አለማዊ በጠቅላላ መለት መጥፎ ማለት ነው: