AM/Prabhupada 0083 - የሀሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም በመዘመር ብቻሁሉም ነገር ሊመጣ ይችላል፡፡



Lecture on SB 7.9.11-13 -- Hawaii, March 24, 1969

ፕራላድ መሀራጅ እንዲህ ብሏል፡፡ ይህንንም ቀደም ብለን ተወያይተንበታል፡፡ ይህም መንፈሳዊ አገልግሎት ምንም ዓይነት የቀድሞ ሙያ አያስፈልገውም፡፡ ይህም ማለት የዓብዩ ጌታን ልብ ለማርካት ወይም ለማስደሰት ምንም ዓይነት ቀደም ብሎ የተያዘ ሙያ ወይም ልምምድ አያስፈልጋችሁም፡፡ ይህንንም ለማድረግ ፈተናችሁን በዩኒቨርስቲ ደረጃ ተምራችሁ ማለፍ እንደሚያስፈልጋችሁ አይደለም፡፡ ወይንም እንደነ ሮክፌለር እና እንደነ ፎርድ በጣም ሀብታም መሆነ አያስፈልጋችሁም፡፡ ወይም እንዲህ እና እንዲያ መሆን አያስፈልጋችሁም፡፡ ምንም የተወሰነለት ነገር የለውም፡፡ ”አሆይቱኪ አፕረቲያታ“ የሽሪ ክርሽናን ፍቅር ለማዳበር ከፈለጋችሁ ምንም አይነት ወደኋላ የሚያስቀራችሁ ነገር አይኖርም፡፡ መንገዱ ክፍት ነው፡፡ መሆን የሚያስፈልጋችሁ ግን በቀላሉ ትሁት እና ከልብ ቅን መሆን ነው፡፡ እንደዚህም ስትሆኑ ሽሪ ክርሽና መንገዱን ቀና ሊያደርግላችሁ ይችላል፡፡ ትሁትነት እና ቅንነት ከሌለ ግን በክርሽና ማያ ወጥመድ እንጠመዳለን፡፡ እንዲህም ከሆንን ማያ የሚያደናቅፈን ነገርን ከፊታችን ታደርግብናለች፡፡ “ይህንን አታድርግ፣ ይህንን አታድርግ” በማለት ታሳስተናለች፡፡ ስለዚህ ፕራላድ መሀራጅ እንዲህ ብሎ ወሰነ፡፡ “ ምንም እንኳን ልጅ ብሆንም” “ምንም እንኳን ትምህርት ባይኖረኝም፣ ምንም እንኳን የቬዲክን እውቀት ያጠናሁ ባልሆንም” “ምንም እንኳን ከከሀድያን ቤተሰብ የተወለድኩ ብሆንም፣ ከረከሰ ቤተሰብ የተወለድኩ ብሆንም እና እነዚህ ሁሉ ያልተስተካከሉ ሆነው ቢገኙም” አምላክን ለማስደሰት እችላለሁ፡፡ “አብዩ ጌታ በረከት በተሞላባቸው አዋቂያን የሚሰገድለት ነው፣ እነርሱም የተለያየ የቬዲክን መዝሙር የሚዘምሩለት ናቸው፡፡ በባህላቸውም በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቀሳውስት ናቸው፡፡ እኔ ግን ይህንን የመሰለ ሙያ እና እውቀት የለኝም፡፡ ቢሆንም ግን እንዲህ የመሳሰሉት ታላላቅ መላእክቶች እና ባህታውያን ሁሉ ምንም እንኳን በመንፈሳዊ ደረጃቸው በጣም ከፍ ያሉ ቢሆኑም እኔን ዓብዩ አምላክን ከቁጣው ቀዝቅዞ እንዳስተስተው ሲጠይቁኝ ይታያሉ፡፡ ይህም ማለት ዓብዩ ጌታ እኔን በመሰለ ሰው እንኳን ለመደሰት እንዲሚችል ያሳየናል ማለት ነው፡፡ ይህ የማይቻል ቢሆንማ እነዚህ ታላላቅ መንፈሳውያን እኔን እንዳስተስተው አይጠይቁኝም ነበር፡፡ ስለዚህ ምንም አይነት እውቀትም ሆነ ሙያ ቢኖረኝ ያለኝን ለሽሪ ክርሽና በፍቅር በማቅረብ ላስደስተው እችላለሁ፡፡ ይህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴያችን የተመሰረተው በዚህ መንፈስ ነው፡፡ ማናቸውም ዓይነት ያለን እውቀት እና ሙያ ሽሪ ክርሽናን ለማስደሰት በቂ ነው፡፡ መጀመር ያለብን ባለን ሙያ እና እውቀት ነው፡፡ ባለን እውቀት እና ሙያ ሽሪ ክርሽናን በትሁትነት ለማገልገል መጣር አለብን፡፡ ትክክለኛው እውቀት እና ሙያ ማለት ዓብዩ አምላክን በትሁትነት እና በቅንነት የማገልገል መንፈስ መያዝ ማለት ነው፡፡ ትክክለኛ እና ብቁ መሆን ማለት ይኅው ነው፡፡ ይህንን ዓይነት መንፈስ ማዳበር ይገባናል፡፡ በውጪ ዝናን ለማግኘት የምናዳበርውን ሙያ ሳይሆን ማለት ነው፡፡ ይህም ቁንጅናን በማግኘት፣ ሀብትን በመያዝ፣ ዓለማዊ እውቀትን በማዳበር ወዘተ አይደለም፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለነፍሳችን ጠቀሜታ የላቸውም፡፡ ለሽሪ ክርሽና አገልግሎት የምንጠቀምባቸው ከሆነ ግን በጣም አስፈላጊ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ሀብታም ከሆናችሁ ሀብታችሁን ለክርሽና አገልግሎት ማዋል ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን አብዩ ጌታን ለማገልገል የግድ ሀብታም መሆን አያስፈልጋችሁም፡፡ ስለዚህ በማናቸውም ደረጃ ላይ ሆናችሁ ዓብዩ ጌታን ማገልገል ትችላላችሁ፡፡ ስለዚህ ፕራላድ መሀራጅ እንዲህ ብሎ ገልፆልናል፡፡ “ኒቾ አጃያ ጉና ቪሳርጋም አኑፕራቪስታሀ ፑዬታ ዬና ፑማን አኑቫርኒቴና” ፕራላድ ከከሀዲያን ቤተሰብ እና መንፈሱ ከተበከለ አባት የተወለደ ነው ተብሎ የሚታማበት ግዜ የለም፡፡ ነጋሪ እሴቱም ይኀው ነው፡፡ ፕራህላድ መንፈሱ የተበከለ አይደለም፡፡ ቢሆንም ግን የተወለደው መንፈሱ ከተበከለ ከሀዲ አባት ነው፡፡ ሰዎች ይህን የመሰለ ሌላ አጃቢ ድምፅ ሊያሰሙ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ፕራላድ መሀራጅ እንዲህ ብሎ ገልፆልናል፡፡ “ዓብዩ ጌታን በትሁት ልቦና በማወደስ ብቻ መንፈሳችን ንፁህ ለመሆን ይችላል፡፡” የሀሬ ክርሽና ቅዱስ ስምን ደጋግመን በቅንነት በመዘመር መንፈሳችንን የፀዳ ለማድረግ እንችላለን፡፡ ስርዓቱም ቅዱስ ስምን መዘመር ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ መንፈሴን የፀዳ አድርጌ ከዚያ በኋላ መዘመር እጀምራለሁ ማለት አይገባንም፡፡ መዘመር ያለብን ወዲያውኑ ባለንበት ደረጃ ነው፡፡ ይህንንም ስርዓት በመከተል መንፈሳችንን የፀዳ ለማድረግ እንችላለን፡፡ መዘመርን ወዲያውኑ ጀምሩ፡፡ ይህም በምንም ዓይነት ደረጃ ላይ ያለንም ቢሆን እንኳን ነው፡፡ በእውነቱ ይህንን የክርሽና ንቃተ ማህበር ስጀምር ተከታዮቼ ሁሉ መንፈሳቸው የፀዳ ሆኖ አይደለም፡፡ እያንዳንዳችሁ እንደምታውቁት ወደ እኔ የቀረቡት ሰዎች ሁሉ ምንም እንኳን ከልጅነታቸው ጀምሮ የሰለጠኑ እና የተማሩ ቢሆኑም እንኳን ነው፡፡ ከህንድ አገር የቬዲክ ባህል ጋር ስናወዳድራቸው የንፅህና ወይም የሀይጂን መመሪያን እንኳን የተቀበሉ አይመስሉም፡፡ ታድያ በዚህ ዓይነት ሁኔታ መንፈሳችን እንዴት ንፁህ ሊሆን ይችላል? በህንድ አገር ያለው ስልጠና የሚጀምረው ከልጅነት ነው፡፡ ልጆችም ለልጅነታቸው ጀምሮ ገላቸውን እንዲታጠቡ እና ጥርሳቸውን እንዲቦርሹ ልምዱ ይሰጣቸዋል፡፡ ትዝ እንደሚለኝም ሁለተኛው ልጄ አራት ዓመት ሲሆነው ቁርሱን ከመመገቡ በፊት “ጥርስህን አሳየኝ” ብዬ እጠይቀው ነበር፡፡ እርሱም ሲያሳየኝ “በጣም ጥሩ ጥርስህን በደንብ አፅድተሀል፡፡ ይህም ትክክል ነው“ በማለት አበረታታው ነበር፡፡ ከዚያም ”አሁን ቁርስህን መብላት ትችላለህ“ ብዬ እነግረው ነበር፡፡ ስለዚህ እንዲህ ዓየነት ልምምድ ከልጅነት ይሰጣል፡፡ በዚህ አገር ግን እንደምናየው ልምድ መስጠቱ አለ፡፡ ነገር ግን ልምድ መስጠቱ ጥብቅ ሆኖ አይታይም፡፡ በቀድሞ ግዜ የሆነው ሆኗል አሁን ግን ቅዱስ ስምን ወይም የሀሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም ለመዘመር መጀመር አለብን፡፡ በዚህም ስርዓት ሁሉም ነገር ሊመጣልን ይችላል፡፡